YouVersion Logo
Search Icon

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 28

28
ጳው​ሎስ በመ​ላ​ጥያ ደሴት
1ከዚ​ህም በኋላ በደ​ኅና በደ​ረ​ስን ጊዜ ደሴ​ቲቱ መላ​ጥያ እን​ደ​ም​ት​ባል ዐወ​ቅን። 2በዚያ የሚ​ኖ​ሩት አረ​ማ​ው​ያ​ንም አዘ​ኑ​ልን፤ መል​ካም ነገ​ር​ንም አደ​ረ​ጉ​ልን፤ ከቍ​ሩም ጽና​ትና ከዝ​ናሙ ብዛት የተ​ነሣ እሳት አን​ድ​ደው እን​ድ​ን​ሞቅ ሁላ​ች​ን​ንም ሰበ​ሰ​ቡን። 3ጳው​ሎ​ስም ብዙ ጭራሮ ሰብ​ስቦ በእ​ሳቱ ላይ ጨመ​ረው፤ እፉ​ኝ​ትም ከእ​ሳቱ ወላ​ፈን የተ​ነሣ ወጥታ ጳው​ሎ​ስን እጁን ነደ​ፈ​ችው። 4አረ​ማ​ው​ያ​ንም እፉ​ኝቱ በጳ​ው​ሎስ እጅ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመ​ስ​ላል፤ ከባ​ሕር እንኳ በደ​ኅና ቢወ​ጣም በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ አል​ተ​ወ​ውም” አሉ። 5ጳው​ሎስ ግን እጁን አራ​ግፎ እፉ​ኝ​ቱን በእ​ሳት ውስጥ ጣላት፤ ጕዳ​ትም አላ​ገ​ኘ​ውም። 6እነ​ርሱ ግን ወዲ​ያ​ውኑ የሚ​ያ​ብጥ ወይም ሞቶ የሚ​ወ​ድቅ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር። እያ​ዩ​ትም ብዙ ሰዓት ቆሙ፤ አን​ዳ​ችም እንደ አል​ጐ​ዳው በአዩ ጊዜም፥ “ይህስ አም​ላክ ነው” ብለው ቃላ​ቸ​ውን ለወጡ።
7በዚያ ቦታም አጠ​ገብ ስሙን ፑፕ​ል​ዮስ የሚ​ሉት የደ​ሴ​ቲቱ አለቃ መሬት ነበር፤ እር​ሱም ሦስት ቀን ሙሉ በደ​ስታ በቤቱ ተቀ​ብሎ አስ​ተ​ና​ገ​ደን። 8የፑ​ፕ​ል​ዮ​ስም አባት በን​ዳ​ድና በተ​ቅ​ማጥ ታሞ ተኝቶ ይኖር ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም እርሱ ወዳ​ለ​በት ገብቶ ጸለ​የ​ለት፤ እጁ​ንም በላዩ ጭኖ ፈወ​ሰው። 9ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ይህን ተአ​ምር ባዩ ጊዜ በዚ​ያች ደሴት ያሉ​ትን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ፈወ​ሳ​ቸ​ውም። 10እጅግ ታላቅ ክብ​ርም አከ​በ​ሩን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ለመ​ሄድ በተ​ነ​ሣን ጊዜ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንን ስንቅ ሰጡን።
ከመ​ላ​ጥያ ወደ ሮም ስለ መጓ​ዛ​ቸው
11ከሦ​ስት ወር በኋ​ላም በዚ​ያች ደሴት ወደ ከረ​መ​ችው ወደ እስ​ክ​ን​ድ​ርያ መር​ከብ ወጣን፤ በዚ​ያች መር​ከብ ላይም የዲ​ዮ​ስ​ቆ​ሮስ ምል​ክት ነበ​ረ​ባት፤ ይኸ​ውም “የመ​ር​ከ​በ​ኞች አም​ላክ”#“የመ​ር​ከ​በ​ኞች አም​ላክ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። የሚ​ሉት ነው። 12ከዚ​ያም ሄደን ወደ ሰራ​ኩስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥን። 13ከዚ​ያም ሄደን ሬቅ​ዩን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረ​ስን፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጣን፤ ከአ​ንድ ቀንም በኋላ ከጐ​ንዋ ነፋስ በነ​ፈሰ ጊዜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ፑቲ​ዮ​ሉስ#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ፑቲ​ዮ​ሉስ እንተ ሀገረ ኢጣ​ልያ” ይላል። ደረ​ስን። 14በዚ​ያም ወን​ድ​ሞ​ችን አግ​ኝ​ተን ተቀ​በ​ሉን፤ በእ​ነ​ርሱ ዘን​ድም ሰባት ቀን እን​ድ​ን​ቀ​መጥ ለመ​ኑን፤ ከዚ​ያም በኋላ ሄደን ወደ ሮሜ ደረ​ስን። 15በዚ​ያም ያሉት ወን​ድ​ሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ፤ አፍ​ዩስ ፋሩስ እስ​ከ​ሚ​ባ​ለው ገበ​ያና እስከ ሦስ​ተ​ኛው ማረ​ፊያ ድረስ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉን፤ ጳው​ሎ​ስም ባያ​ቸው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ልቡም ተጽ​ናና። 16ወደ ሮሜም በገ​ባን ጊዜ የመቶ አለ​ቃው እስ​ረ​ኞ​ችን ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አስ​ረ​ከበ፤ ጳው​ሎስ ግን ከሚ​ጠ​ብ​ቀው አንድ ወታ​ደር ጋር ለብ​ቻው ይቀ​መጥ ዘንድ ፈቀ​ደ​ለት።
ጳው​ሎስ ከአ​ይ​ሁድ ሊቃ​ው​ንት ጋር ስለ መነ​ጋ​ገሩ
17ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጳው​ሎስ የአ​ይ​ሁ​ድን ታላ​ላቅ ሰዎች ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ቢሆን፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ታሰ​ርሁ ለሮም ሰዎች አሳ​ል​ፈው ሰጡኝ። 18እነ​ር​ሱም መር​ም​ረው ለሞት የሚ​ያ​በቃ በደል ስለ​አ​ላ​ገ​ኙ​ብኝ ሊፈ​ቱኝ ወደዱ። 19#የሐዋ. 25፥11። አይ​ሁድ ግን ሊቃ​ወ​ሙኝ በተ​ነሡ ጊዜ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ለማ​ለት ግድ ሆነ​ብኝ፤ ነገር ግን ወገ​ኖ​ችን የም​ከ​ስ​በት ነገር ኖሮኝ አይ​ደ​ለም። 20ስለ​ዚ​ህም ላያ​ችሁ፥ ልነ​ግ​ራ​ች​ሁና ላስ​ረ​ዳ​ችሁ ወደ እኔ እን​ድ​ት​መጡ ማለ​ድ​ኋ​ችሁ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ተስፋ በዚህ ሰን​ሰ​ለት ታስ​ሬ​አ​ለ​ሁና።” 21የአ​ይ​ሁድ ታላ​ላቅ ሰዎ​ችም እን​ዲህ አሉት፥ “ለእ​ኛስ ከይ​ሁዳ ሀገር ስለ አንተ መል​እ​ክት አል​ደ​ረ​ሰ​ንም፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም#“ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ ዘር የለም። ከመ​ጡት ወን​ድ​ሞ​ችም ቢሆን አንድ ስንኳ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ ስለ አንተ ክፉ ነገር ያወ​ራን፥ የነ​ገ​ረ​ንም የለም። 22ነገር ግን በዚህ ነገር በየ​ስ​ፍ​ራው ሁሉ እን​ዲ​ጣሉ በእኛ ዘንድ ታው​ቋ​ልና የአ​ን​ተን ዐሳብ ደግሞ ከአ​ንተ እን​ሰማ ዘንድ እን​ወ​ድ​ዳ​ለን።” 23ከዚ​ህም በኋላ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጡ​በ​ትን ቀን ቀጠ​ሩ​ትና ብዙ​ዎች ወዳ​ረ​ፈ​በት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥ​ዋ​ትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እየ​መ​ሰ​ከረ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከሙሴ ኦሪ​ትና ከነ​ቢ​ያት እየ​ጠ​ቀሰ ነገ​ራ​ቸው። 24ከእ​ነ​ር​ሱም እኩ​ሌ​ቶቹ የተ​ና​ገ​ረ​ውን አመኑ፤ እኩ​ሌ​ቶቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም። 25እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ባል​ተ​ስ​ማሙ ጊዜ ጳው​ሎስ አን​ዲት ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ ከእ​ርሱ ተመ​ለሱ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ አን​ደ​በት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ው​ነት እን​ዲህ ብሎ መል​ካም ነገር ተና​ግ​ሮ​አል። 26‘ወደ​ዚህ ሕዝብ ሂድና እን​ዲህ በላ​ቸው፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፤ ግን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፤ ግን አት​መ​ለ​ከ​ቱም። 27#ኢሳ. 6፥9-10። በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና ይቅር እን​ዳ​ል​ላ​ቸው#በግ​ሪኩ “እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው” ይላል። የዚህ ሕዝብ ልባ​ቸው ደን​ድ​ኖ​አ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ውም ደን​ቁ​ሮ​አ​ልና፥ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና’። 28እን​ግ​ዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገ​ኘች ይህቺ ድኅ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ እን​ደ​ም​ት​ሆን ዕወቁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ሙ​ታል።” 29ይህ​ንም በተ​ና​ገ​ራ​ቸው ጊዜ አይ​ሁድ እርስ በር​ሳ​ቸው እጅግ እየ​ተ​ከ​ራ​ከሩ ወጥ​ተው ሄዱ። 30ጳው​ሎ​ስም በገ​ን​ዘቡ በተ​ከ​ራ​የው ቤት ሁለት ዓመት ተቀ​መጠ፤ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​በል ነበር። 31ማንም ሳይ​ከ​ለ​ክ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ይሰ​ብክ ነበር፤ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም እጅግ ገልጦ ያስ​ተ​ምር ነበር። 32ጳው​ሎ​ስም በመ​ጀ​መ​ሪያ ጊዜ ወደ ኔሮን ቄሣር ገብቶ ነበ​ርና ረትቶ በሰ​ላም ሄደ፤ ከዚ​ህም በኋላ ሁለት ዓመት ኖሮ ከሮም ወጣ። 33ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሮም ተመ​ልሶ የኔ​ሮን ቄሣር ዘመ​ዶ​ችን አጠ​መቀ፤ በኔ​ሮን ትእ​ዛ​ዝም በሰ​ይፍ ተመ​ትቶ መከ​ራ​ው​ንም ታግሦ ሰማ​ዕት ሆነ።#ምዕ. 28 ቍ. 32 እና 33 በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ ብቻ የሚ​ገኝ ነው።
ወን​ጌ​ላ​ዊው ሉቃስ የጻ​ፈው የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ መጽ​ሐፍ ተፈ​ጸመ።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 28