YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ሮሜ ሰዎች 1

1
ስለ መጠ​ራቱ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ለማ​ስ​ተ​ማር ተለ​ይቶ ከተ​ጠራ ሐዋ​ርያ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ከሚ​ሆን ከጳ​ው​ሎስ፥ 2በነ​ቢ​ያቱ ቃልና በቅ​ዱ​ሳት መጻ​ሕ​ፍት አስ​ቀ​ድሞ በተ​ስፋ ያና​ገ​ረው፥ 3ከዳ​ዊት ዘር ሰው ሆኖ በሥጋ ስለ ተወ​ለደ ስለ ልጁ፥ 4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀ​ይ​ሉና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ በመ​ነ​ሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥ 5በስሙ እን​ዲ​ያ​ምኑ አሕ​ዛ​ብን ልና​ስ​ተ​ምር ሐዋ​ር​ያት ተብ​ለን የተ​ሾ​ም​ን​በ​ትና ጸጋን ያገ​ኘ​ን​በት፥ 6እና​ን​ተም ዛሬ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለማ​መን እንደ ተጠ​ራ​ችሁ። 7በሮሜ ላላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዳ​ችሁ፥ ለመ​ረ​ጣ​ች​ሁና ላከ​በ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።
8አስ​ቀ​ድሜ ስለ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ማመ​ና​ችሁ በዓ​ለም ሁሉ ተሰ​ም​ታ​ለ​ችና። 9ባለ​ማ​ቋ​ረጥ በም​ጸ​ል​የው ጸሎት እን​ደ​ማ​ስ​ባ​ችሁ ልጁ በአ​ስ​ተ​ማ​ረው ወን​ጌል በፍ​ጹም ልቡ​ናዬ የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው። 10ወደ እና​ንተ እመጣ ዘን​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃዱ መን​ገ​ዴን ያቃ​ና​ልኝ ዘንድ ዘወ​ትር እጸ​ል​ያ​ለሁ። 11ትጸኑ ዘንድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ስጦታ እን​ድ​ታ​ገኙ ላያ​ችሁ እወ​ዳ​ለ​ሁና፤ 12ይህ​ንም ማለቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ባለች በእ​ና​ን​ተና በእኔ እም​ነት አብ​ረን በእ​ና​ንተ እን​ድ​ን​ጽ​ናና ነው። 13#የሐዋ. 19፥21። ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በሌ​ሎች አሕ​ዛብ እንደ ሆነ በእ​ና​ን​ተም ዋጋ​ዬን አገኝ ዘንድ ሁል​ጊዜ ወደ እና​ንተ ልመጣ እንደ ወደ​ድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረ​ስም እንደ ተሳ​ነኝ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ። 14ለአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንና ላል​ተ​ማሩ፥ ለጥ​በ​በ​ኞ​ችና ለማ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ሁሉ አስ​ተ​ምር ዘንድ ዕዳ አለ​ብኝ። 15ይል​ቁ​ንም በሮሜ ላላ​ችሁ ለእ​ና​ንተ ወን​ጌ​ልን ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ እተ​ጋ​ለሁ።
16 # ማር. 8፥38። ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር አላ​ፍ​ር​ምና፤ አስ​ቀ​ድሞ አይ​ሁ​ዳ​ዊን፥ ደግ​ሞም አረ​ማ​ዊን፥ የሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትን ሁሉ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይሉ ነውና። 17#ዕን. 2፥4። “ጻድቅ በእ​ም​ነት ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከእ​ም​ነት ወደ እም​ነት በእ​ርሱ ይገ​ለ​ጣ​ልና።
በኃ​ጥ​ኣን ላይ ስለ​ሚ​መ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት
18እው​ነ​ትን ዐው​ቀው በክ​ፋ​ታ​ቸው በሚ​ለ​ው​ጡ​አት በዐ​መ​ፀ​ና​ውና በኀ​ጢ​አ​ተ​ናው ሰው ሁሉ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት ከሰ​ማይ ይመ​ጣል። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ገለ​ጠ​ላ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። 20የማ​ይ​ታ​የው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሕ​ርይ እር​ሱም የዘ​ለ​ዓ​ለም ኀይ​ሉና ጌት​ነቱ ከዓ​ለም ፍጥ​ረት ጀምሮ የፈ​ጠ​ረ​ውን ፍጥ​ረት በማ​ሰ​ብና በመ​መ​ር​መር ይታ​ወ​ቃል፤ መልስ የሚ​ሰ​ጡ​በ​ትን ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ያ​ገኙ። 21#ኤፌ. 4፥17-18። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሲያ​ው​ቁት እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ነቱ አላ​ከ​በ​ሩ​ትም፤ አላ​መ​ሰ​ገ​ኑ​ት​ምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአ​ሳ​ባ​ቸ​ውም ረከሱ፤ ልቡ​ና​ቸ​ውም ባለ​ማ​ወቅ ጨለመ። 22ጥበ​በ​ኞች ነን ሲሉ አላ​ዋ​ቆች ሆኑ። 23#ዘዳ. 4፥16-18። የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር በሚ​ሞት ሰውና በዎ​ፎች፥ አራት እግር ባላ​ቸ​ውም፥ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም መልክ መስ​ለው ለወጡ።
24ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ቸው ሥጋ​ቸ​ውን ሊያ​ዋ​ርዱ በል​ባ​ቸው ፍት​ወት ወደ ርኵ​ሰት አሳ​ልፎ ተዋ​ቸው። 25የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እው​ነት ሐሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ታ​ልና፤ ተዋ​ር​ደ​ውም ፍጥ​ረ​ቱን አም​ል​ከ​ዋ​ልና፤ ሁሉን የፈ​ጠ​ረ​ውን ግን ተዉት፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።
26ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የሚ​ገ​ባ​ውን ትተው ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ሠሩ። 27ወን​ዶ​ችም እን​ዲሁ ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የሚ​ገ​ባ​ውን ሴቶ​ችን ትተው በፍ​ት​ወት ተቃ​ጠሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እየ​ተ​መ​ላ​ለሱ፥ ወን​ዶች በወ​ን​ዶች ላይ የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ውን ነውር ሠሩ፤ ነገር ግን ፍዳ​ቸ​ውን ያገ​ናሉ፤ ፍዳ​ቸ​ውም በራ​ሳ​ቸው ይመ​ለ​ሳል። 28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው። 29እነ​ር​ሱም ዐመ​ፅን ሁሉ፥ ክፋ​ት​ንም፥ ምኞ​ት​ንም፥ ቅሚ​ያ​ንም፥ ቅና​ት​ንም የተ​መሉ ናቸው፤ ምቀ​ኞች፥ ነፍሰ ገዳ​ዮች፥ ከዳ​ተ​ኞች፥ ተን​ኰ​ለ​ኞች፥ ኩሩ​ዎች፥ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንና ግብ​ራ​ቸ​ው​ንም ያከፉ ናቸው። 30ሐሜ​ተ​ኞች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ጠሉ፥ ተሳ​ዳ​ቢ​ዎች፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞች፥ ትም​ክ​ሕ​ተ​ኞች፥ ክፋ​ትን የሚ​ፈ​ላ​ለጉ፥ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም የማ​ይ​ታ​ዘዙ ናቸው። 31የማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ዝን​ጉ​ዎች፥ ፍቅ​ርም፥ ምሕ​ረ​ትም የሌ​ላ​ቸው ናቸው። 32ይህን እን​ዲህ ላደ​ረገ ሞት እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እነ​ርሱ ራሳ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ እያ​ወቁ፥ እነ​ርሱ ብቻ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ያነ​ሣ​ሡ​ታል፤ ያሠ​ሩ​ታ​ልም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for ወደ ሮሜ ሰዎች 1