YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 15

15
ዕዳ የሚ​ሠ​ረ​ዝ​በት ዓመት
(ዘሌ. 25፥1-7)
1“በየ​ሰ​ባቱ ዓመት የዕዳ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ። 2ለም​ሕ​ረ​ቱም የሚ​ገባ ትእ​ዛዝ ይህ ነው፤ ባል​ን​ጀ​ራህ ወይም ወን​ድ​ምህ የሚ​ከ​ፍ​ል​ህን ገን​ዘብ ሁሉ አት​ከ​ፈል፤ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ተብ​ላ​ለ​ችና። 3ከባ​ዕድ ግን በእ​ርሱ ዘንድ ያለ​ህን ሁሉ መቀ​በል ትች​ላ​ለህ፤ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ ያለ​ውን ሁሉ ግን ተው​ለት። 4አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ ርስት አድ​ርጎ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና በመ​ካ​ከ​ልህ ድሃ አይ​ኖ​ርም፤ 5አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ታደ​ር​ጋ​ትም ዘንድ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ 6አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረህ ይባ​ር​ክ​ሃል፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም ብዙ ታበ​ድ​ራ​ለህ፤ አንተ ግን አት​በ​ደ​ርም፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ትገ​ዛ​ለህ፤ አን​ተን ግን አይ​ገ​ዙ​ህም።
7“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ካሉ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ከሚ​ኖሩ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ አንዱ ቢቸ​ገር ልብ​ህን አታ​ጽና፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ከመ​ስ​ጠት እጅ​ህን አት​መ​ልስ። 8ነገር ግን እጅ​ህን ለእ​ርሱ ዘርጋ፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ሁሉ ስጠው።#ዕብ. “አበ​ድ​ረው” ይላል። 9ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የም​ሕ​ረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አል​ሰ​ጠ​ው​ምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በል​ብህ እን​ዳ​ታ​ስብ ለራ​ስህ ዕወቅ። ወን​ድ​ም​ህም ዐይ​ኑን በአ​ንተ ላይ ያከ​ፋል፤ እር​ሱም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንተ ላይ ይጮ​ሃል፤ ኀጢ​አ​ትም ይሆ​ን​ብ​ሃል። 10እጅ​ህን በም​ት​ጥ​ል​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ዚህ በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና ፈጽ​መህ ስጠው፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ያህል አበ​ድ​ረው፤ በሰ​ጠ​ኸ​ውም ጊዜ በል​ብህ አት​ጸ​ጸት። 11ድሃ ከም​ድ​ርህ ላይ አይ​ታ​ጣ​ምና ስለ​ዚህ እኔ፦ በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ላለው ድሃ፥ ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ወን​ድ​ምህ እጅ​ህን ዘርጋ ብዬ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።
ባሮች ነጻ የሚ​ወ​ጡ​በት ዓመት
(ዘፀ. 21፥1-11)
12“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን ዕብ​ራ​ዊ​ዉን ወይም ዕብ​ራ​ዊ​ቱን ብት​ገዛ ስድ​ስት ዓመት ያገ​ል​ግ​ሉህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከአ​ንተ ዘንድ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ልቀ​ቀው። 13ከአ​ን​ተም ዘንድ አር​ነት አው​ጥ​ተህ በለ​ቀ​ቅ​ኸው ጊዜ ባዶ​ውን አት​ል​ቀ​ቀው። 14ነገር ግን ከበ​ጎ​ችህ፥ ከእ​ህ​ል​ህም፥ ከወ​ይ​ን​ህም መጭ​መ​ቂያ ስንቅ ትሰ​ን​ቅ​ለ​ታ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ባረ​ከህ መጠን ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ። 15አን​ተም በግ​ብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ። 16እርሱ ግን አን​ተ​ንና ቤት​ህን ስለ ወደደ፥ በአ​ን​ተም ዘንድ መኖር መል​ካም ስለ​ሆ​ነ​ለት፦ ‘አል​ወ​ጣም’ ቢል፥ 17አንተ ወስፌ ወስ​ደህ በቤ​ትህ በር ላይ ጆሮ​ውን#ግእዙ “አፍ​ን​ጫ​ውን” ይላል። ትበ​ሳ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪያ ይሆ​ን​ል​ሃል። በሴት ባሪ​ያ​ህም ደግሞ እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ። 18እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።
የእ​ን​ስ​ሳት በኵ​ራት
19“ላም​ህና በግህ የወ​ለ​ዱ​ትን ተባት የሆ​ነ​ውን በኵ​ራት ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ በበ​ሬህ በኵ​ራት አት​ሥ​ራ​በት፤ የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት አት​ሸ​ልት። 20አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ አን​ተና ቤተ ሰብህ በየ​ዓ​መቱ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብላው። 21ነው​ረኛ ወይም አን​ካሳ ወይም ዕውር ቢሆን፥ ወይም አን​ዳች ክፉ ነውር ቢኖ​ረው፥ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠ​ዋው። 22በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ትበ​ላ​ዋ​ለህ፤ ንጹሕ ሰው፥ ንጹ​ሕም ያል​ሆነ፥ ሚዳ​ቋ​ንና ዋሊ​ያን እን​ደ​ሚ​በሉ ይበ​ሉ​ታል። 23ነገር ግን ደሙን በም​ድር ላይ እንደ ውኃ አፍ​ስ​ሰው እንጂ አት​ብ​ላው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in