ኦሪት ዘዳግም 22
22
1“የወንድምህ በሬ ወይም በግ በመንገድ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፤ እነርሱን መልሰህ ለወንድምህ ስጥ። 2ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘሃቸው ወደ ቤትህ ትገባለህ፤ ወንድምህ እስኪሻቸው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣሉ፤ ለእርሱም ትመልስለታለህ። 3አህያውም ቢሆን፥ በሬውም ቢሆን፥#“በሬ” የሚለው በግእዙ እንጂ በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። ወይም ልብሱ ቢሆን እንዲሁ ታደርጋለህ፤ እንዲሁም በወንድምህ በጠፋበት ነገር ሁሉ ባገኘኸው ጊዜ ታደርጋለህ፤ ቸል ልትለው አይገባህም። 4የወንድምህ አህያው ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ቸል አትበላቸው፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ሆነህ አነሣሣው።
5“ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።
6“በመንገድ በማናቸውም ዛፍ ላይ ወይም በመሬት ላይ ከጫጭቶችና ከእንቍላል ጋር እናቲቱ በእነዚህ ላይ ተቀምጣ የወፍ ጎጆ ብታገኝ እናቲቱን ከጫጭቶችዋ ጋር አትውሰድ። 7ነገር ግን መልካም ይሆንልህ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ እናቲቱን ልቀቅ፤ ጫጭቶችንም ለአንተ ውሰድ።
8“አዲስ ቤት በሠራህ ጊዜ ማንም ከእርሱ ወድቆ በቤትህ ግድያ እንዳታደርግ ለሰገነትህ መከታ አድርግለት።
9“ፍሬውንና የዘራኸውን ዘር ከወይንህ ፍሬ ጋር እንዳትለቅም#ዕብ. “የዘራኸው ዘርና ከወይኑ የወጣው አንድ ሆነው እንዳይረክሱብህ” ሲል አንዳንድ የግሪክ ሰባ. ሊ. ዘርዕ ደግሞ “እንዳይቀደሱብህ” ይላል። በወይንህ ቦታ ላይ የተለያየ ዓይነት ተክል አትትከል። 10በአህያህና በበሬህ በአንድነት አትረስ። 11ከተልባ እግርና ከበግ ጠጕር በአንድነት የተሠራ ልብስ አትልበስ።
12“በምትለብሰው በልብስህ በአራቱ ማዕዘን ዘርፍ አድርግ።
ድንግልናን ስለ መጠበቅ
13“ማናቸውም ሰው ሚስት ቢያገባ፥ አብሮአትም ከኖረ በኋላ ቢጠላት፥ 14የነውር ነገርም ቢያመጣባት፥ እኔ ይህችን ሴት ሚስቴ አድርጌ አገባኋት፤ በደረስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም ብሎ ክፉ ስም ቢያወጣባት፥ 15የብላቴናዪቱ አባትና እናት የልጃቸውን የድንግልናዋን ልብስ ወስደው በበሩ አደባባይ ወደ ተቀመጡ ወደ ከተማ ሽማግሌዎች ያምጡት፤ 16የብላቴናዪቱም አባት ሽማግሌዎቹን፦ እኔ ለዚህ ሰው ልጄን ዳርሁለት፤ እርሱም ጠላት፤ 17እነሆም፦ በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም ብሎ የነውር ነገር አወራባት፤ የልጄም የድንግልናዋ ልብስ ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ። 18የዚያች ከተማ ሽማግሌዎችም ያን ሰው ወስደው ይገሥጹት፤ 19በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል ያስከፍሉት፤ ለብላቴናዪቱም አባት ይስጡት፤ እርስዋም ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።
20“ነገሩ ግን እውነት ቢሆን፥ የብላቴናዪቱም ድንግልናዋ ባይገኝ፥ 21ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
22“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመንዝራውና አመንዝራዪቱ ሁለታቸው ይገደሉ፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከእስራኤል ታስወግዳለህ።
23“ለወንድ የታጨች ድንግል ልጅ ብትኖር፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ 24ብላቴናዪቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውየውም የባልጀራውን ሚስት አስነውሮአልና በድንጋይ ወግረው ይግደሉአቸው፤ እንዲሁ ክፉውን ነገር ከውስጥህ ታስወግዳለህ።
25“ነገር ግን ሰው የታጨችውን ልጃገረድ በሜዳ ቢያገኛት፥ በግድ አሸንፎም ቢደርስባት፥ ያ የደረሰባት ሰው ብቻውን ይገደል። 26በብላቴናዪቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉ፤ በብላቴናዪቱ ላይ ለሞት የሚያበቃ ኀጢአት የለባትም፤ ሰው በባልንጀራው ላይ ተነሥቶ እንደሚገድለው ይህ ነገር ደግሞ እንደዚሁ ነውና፤ 27በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ጮኻለችና፥ የሚታደጋትም አልነበረምና። 28ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ያልታጨች ልጃገረድ ቢያገኝ፥ በግድ አሸንፎ ቢደፍራት፥ ቢያገኙትም፥ 29ያ የደፈራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናዪቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።
30“ማናቸውም ሰው የእንጀራ እናቱን አይውሰድ፤ የአባቱንም ኀፍረት አይግለጥ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 22: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in