YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 22

22
1“የወ​ን​ድ​ምህ በሬ ወይም በግ በመ​ን​ገድ ጠፍቶ ብታይ ቸል አት​በል፤ እነ​ር​ሱን መል​ሰህ ለወ​ን​ድ​ምህ ስጥ። 2ወን​ድ​ም​ህም በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያህ ባይ​ሆን ወይም ባታ​ው​ቀው ይዘ​ሃ​ቸው ወደ ቤትህ ትገ​ባ​ለህ፤ ወን​ድ​ምህ እስ​ኪ​ሻ​ቸው ድረስ በአ​ንተ ዘንድ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ለእ​ር​ሱም ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ። 3አህ​ያ​ውም ቢሆን፥ በሬ​ውም ቢሆን፥#“በሬ” የሚ​ለው በግ​እዙ እንጂ በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። ወይም ልብሱ ቢሆን እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እን​ዲ​ሁም በወ​ን​ድ​ምህ በጠ​ፋ​በት ነገር ሁሉ ባገ​ኘ​ኸው ጊዜ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቸል ልት​ለው አይ​ገ​ባ​ህም። 4የወ​ን​ድ​ምህ አህ​ያው ወይም በሬው በመ​ን​ገድ ወድቆ ብታይ ቸል አት​በ​ላ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ጋር ሆነህ አነ​ሣ​ሣው።
5“ሴት የወ​ንድ ልብስ አት​ል​በስ፤ ወን​ድም የሴት ልብስ አይ​ል​በስ፤ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።
6“በመ​ን​ገድ በማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ ላይ ወይም በመ​ሬት ላይ ከጫ​ጭ​ቶ​ችና ከእ​ን​ቍ​ላል ጋር እና​ቲቱ በእ​ነ​ዚህ ላይ ተቀ​ምጣ የወፍ ጎጆ ብታ​ገኝ እና​ቲ​ቱን ከጫ​ጭ​ቶ​ችዋ ጋር አት​ው​ሰድ። 7ነገር ግን መል​ካም ይሆ​ን​ልህ ዘንድ፥ ዕድ​ሜ​ህም ይረ​ዝም ዘንድ እና​ቲ​ቱን ልቀቅ፤ ጫጭ​ቶ​ች​ንም ለአ​ንተ ውሰድ።
8“አዲስ ቤት በሠ​ራህ ጊዜ ማንም ከእ​ርሱ ወድቆ በቤ​ትህ ግድያ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ለሰ​ገ​ነ​ትህ መከታ አድ​ር​ግ​ለት።
9“ፍሬ​ው​ንና የዘ​ራ​ኸ​ውን ዘር ከወ​ይ​ንህ ፍሬ ጋር እን​ዳ​ት​ለ​ቅም#ዕብ. “የዘ​ራ​ኸው ዘርና ከወ​ይኑ የወ​ጣው አንድ ሆነው እን​ዳ​ይ​ረ​ክ​ሱ​ብህ” ሲል አን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ዘርዕ ደግሞ “እን​ዳ​ይ​ቀ​ደ​ሱ​ብህ” ይላል። በወ​ይ​ንህ ቦታ ላይ የተ​ለ​ያየ ዓይ​ነት ተክል አት​ት​ከል። 10በአ​ህ​ያ​ህና በበ​ሬህ በአ​ን​ድ​ነት አት​ረስ። 11ከተ​ልባ እግ​ርና ከበግ ጠጕር በአ​ን​ድ​ነት የተ​ሠራ ልብስ አት​ል​በስ።
12“በም​ት​ለ​ብ​ሰው በል​ብ​ስህ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ዘርፍ አድ​ርግ።
ድን​ግ​ል​ናን ስለ መጠ​በቅ
13“ማና​ቸ​ውም ሰው ሚስት ቢያ​ገባ፥ አብ​ሮ​አ​ትም ከኖረ በኋላ ቢጠ​ላት፥ 14የነ​ውር ነገ​ርም ቢያ​መ​ጣ​ባት፥ እኔ ይህ​ችን ሴት ሚስቴ አድ​ርጌ አገ​ባ​ኋት፤ በደ​ረ​ስ​ሁ​ባ​ትም ጊዜ ድን​ግ​ል​ና​ዋን አላ​ገ​ኘ​ሁ​ባ​ትም ብሎ ክፉ ስም ቢያ​ወ​ጣ​ባት፥ 15የብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባ​ትና እናት የል​ጃ​ቸ​ውን የድ​ን​ግ​ል​ና​ዋን ልብስ ወስ​ደው በበሩ አደ​ባ​ባይ ወደ ተቀ​መጡ ወደ ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ያም​ጡት፤ 16የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን፦ እኔ ለዚህ ሰው ልጄን ዳር​ሁ​ለት፤ እር​ሱም ጠላት፤ 17እነ​ሆም፦ በል​ጅህ ድን​ግ​ልና አላ​ገ​ኘ​ሁ​ባ​ትም ብሎ የነ​ውር ነገር አወ​ራ​ባት፤ የል​ጄም የድ​ን​ግ​ል​ናዋ ልብስ ይኸው ይላ​ቸ​ዋል። በከ​ተ​ማም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ፊት ልብ​ሱን ይዘ​ረ​ጋሉ። 18የዚ​ያች ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ያን ሰው ወስ​ደው ይገ​ሥ​ጹት፤ 19በእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ላይ ክፉ ስም አም​ጥ​ቶ​አ​ልና መቶ የብር ሰቅል ያስ​ከ​ፍ​ሉት፤ ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ይስ​ጡት፤ እር​ስ​ዋም ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።
20“ነገሩ ግን እው​ነት ቢሆን፥ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ድን​ግ​ል​ናዋ ባይ​ገኝ፥ 21ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።
22“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመ​ን​ዝ​ራ​ውና አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ሁለ​ታ​ቸው ይገ​ደሉ፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።
23“ለወ​ንድ የታ​ጨች ድን​ግል ልጅ ብት​ኖር፥ ሌላ ሰውም በከ​ተማ ውስጥ አግ​ኝቶ ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለ​ቱን ወደ​ዚ​ያች ከተማ በር አው​ጡ​አ​ቸው፤ 24ብላ​ቴ​ና​ዪቱ በከ​ተማ ውስጥ ሳለች አል​ጮ​ኸ​ች​ምና፥ ሰው​የ​ውም የባ​ል​ጀ​ራ​ውን ሚስት አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አ​ቸው፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ነገር ከው​ስ​ጥህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።
25“ነገር ግን ሰው የታ​ጨ​ች​ውን ልጃ​ገ​ረድ በሜዳ ቢያ​ገ​ኛት፥ በግድ አሸ​ን​ፎም ቢደ​ር​ስ​ባት፥ ያ የደ​ረ​ሰ​ባት ሰው ብቻ​ውን ይገ​ደል። 26በብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ ላይ ግን ምንም አታ​ድ​ርጉ፤ በብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ ላይ ለሞት የሚ​ያ​በቃ ኀጢ​አት የለ​ባ​ትም፤ ሰው በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ተነ​ሥቶ እን​ደ​ሚ​ገ​ድ​ለው ይህ ነገር ደግሞ እን​ደ​ዚሁ ነውና፤ 27በሜዳ ባገ​ኛት ጊዜ የታ​ጨ​ችው ልጃ​ገ​ረድ ጮኻ​ለ​ችና፥ የሚ​ታ​ደ​ጋ​ትም አል​ነ​በ​ረ​ምና። 28ማና​ቸ​ውም ሰው ድን​ግ​ልና ያላ​ትን ያል​ታ​ጨች ልጃ​ገ​ረድ ቢያ​ገኝ፥ በግድ አሸ​ንፎ ቢደ​ፍ​ራት፥ ቢያ​ገ​ኙ​ትም፥ 29ያ የደ​ፈ​ራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት ይስጥ፤ አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።
30“ማና​ቸ​ውም ሰው የእ​ን​ጀራ እና​ቱን አይ​ው​ሰድ፤ የአ​ባ​ቱ​ንም ኀፍ​ረት አይ​ግ​ለጥ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in