YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 26

26
ስለ ቀዳ​ም​ያ​ትና ዐሥ​ራት
1“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም፥ በኖ​ር​ህ​ባ​ትም ጊዜ፥ 2አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ። 3በዚ​ያም ወራት ወደ​ሚ​ሆ​ነው ካህን መጥ​ተህ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አስ​ታ​ው​ቃ​ለሁ’ በለው። 4ካህ​ኑም ዕን​ቅ​ቡን ከእ​ጅህ ወስዶ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ያኑ​ረው፤ 5በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ። 6ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ክፉ ነገር አደ​ረ​ጉ​ብን፤ አስ​ጨ​ነ​ቁ​ንም፤ በላ​ያ​ች​ንም ከባድ ሥራን ጫኑ​ብን፤ 7ወደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃላ​ች​ንን ሰማ፤ ጭን​ቀ​ታ​ች​ን​ንም፥ ድካ​ማ​ች​ን​ንም፥ ግፋ​ች​ን​ንም አየ፤ 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ፥ በታ​ላቅ ተአ​ም​ራ​ትም፥ በድ​ን​ቅም ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤ 9ወደ​ዚ​ህም ስፍራ አገ​ባን፤ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ው​ንም ይህ​ችን ምድር ሰጠን። 10አሁ​ንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ማርና ወተት የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን የም​ድ​ሪ​ቱን ፍሬ ቀዳ​ም​ያት አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ። 11አን​ተም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አኑ​ረው፥#“አን​ተም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አኑ​ረው” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስገድ። አን​ተም፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያለ ሌዋ​ዊና መጻ​ተኛ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ በሰ​ጠው ቸር​ነት ሁሉ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።
12“ዐሥ​ራት በም​ታ​ወ​ጣ​በት በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ሁሉ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ፥ ሁለ​ተኛ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ#“ሁለ​ተኛ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። በከ​ተ​ሞ​ችህ ውስጥ ይበሉ ዘንድ፥ ይጠ​ግ​ቡም ዘንድ ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሃ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ስጣ​ቸው። 13በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ በል፦ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር ከቤቴ ለይች ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሀ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸኝ ትእ​ዛዝ ሁሉ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ምንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ሁም፤ አል​ረ​ሳ​ሁ​ምም፤ 14በኀ​ዘ​ኔም ጊዜ እኔ ከእ​ርሱ አል​በ​ላ​ሁም፤ ለር​ኩ​ስም ነገር ከእ​ርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አል​ሠ​ዋ​ሁም፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች ለሞተ ሰው አል​ሰ​ጠ​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ኬ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ኝ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ። 15ከቅ​ዱስ ማደ​ር​ያህ ከሰ​ማይ ጐብኝ፤ ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን፥ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ትሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን እንደ ማል​ህ​ላ​ቸው የሰ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ንም ምድር ባርክ።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ሕዝብ
16“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ዛሬ አዝ​ዞ​ሃል፤ አን​ተም በፍ​ጹም ልብ​ህና በፍ​ጹም ነፍ​ስህ ጠብ​ቀው፤ አድ​ር​ገ​ውም። 17አን​ተም በመ​ን​ገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን፥ ፍር​ዱ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ትሰማ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላ​ክህ እን​ዲ​ሆን ዛሬ መር​ጠ​ሃል። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ርስ​ቱና ሕዝቡ ትሆን ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ሁሉ ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ዛሬ መር​ጦ​ሃ​ልና፤ 19ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ትሆን ዘንድ፥ እር​ሱም እንደ ተና​ገረ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ታላቅ ስምን፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ር​ንም አደ​ረ​ገ​ልህ።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in