YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 31

31
ኢያሱ በሙሴ ፋንታ እንደ ተተካ
1ሙሴም ይህን ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ተና​ግሮ ጨረሰ። 2አላ​ቸ​ውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖ​ኛል፤ ከዚህ በኋላ እወ​ጣና እገባ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ርም’ ብሎ​ኛል። 3አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ በፊ​ትህ ያል​ፋል፤ እርሱ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ትወ​ር​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ኢያሱ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ባጠ​ፋ​ቸው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሚ​ኖሩ በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት በሴ​ዎ​ንና በዐግ፥ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም እን​ዳ​ደ​ረገ እን​ዲሁ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋል። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊ​ታ​ችሁ አሳ​ልፎ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም ሁሉ ታደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ። 6ጽና፤ በርታ፤ አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ድ​ከም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህ​ምም። 7ሙሴም ኢያ​ሱን ጠርቶ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት፦ ‘አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ሰጥ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ትገ​ባ​ለ​ህና፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለእ​ነ​ርሱ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ። 8በፊ​ት​ህም የሚ​ሄድ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህም፤ አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ’ ” አለው።
ሕጉ በየ​ሰ​ባት ዓመት መነ​በብ እን​ደ​ሚ​ገ​ባው
9ሙሴም ይህ​ችን ሕግ ጻፈ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ይሸ​ከሙ ለነ​በ​ሩት ለሌዊ ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰጣት። 10ሙሴም በዚ​ያች ቀን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት መጨ​ረሻ በም​ሕ​ረት ዓመት በዳስ በዓል፥ 11እስ​ራ​ኤል ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታይ ዘንድ እርሱ በመ​ረ​ጠው ቦታ በአ​ን​ድ​ነት በሚ​ሄ​ድ​በት ጊዜ፥ ይህን ሕግ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በጆ​ሮው አን​ብ​በው። 12ይሰ​ሙና ይማሩ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ዘንድ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ሰም​ተው ያደ​ርጉ ዘንድ ሕዝ​ቡን ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችን፥ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ በሀ​ገ​ራ​ችሁ ደጅ ያለ​ው​ንም መጻ​ተኛ ሰብ​ስብ። 13የማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ሄ​ዱ​ባት ምድር በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይስሙ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ይማሩ።”
ሙሴና ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ሪያ መቀ​በ​ላ​ቸው
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የም​ት​ሞ​ት​በት ቀን እነሆ ቀረበ፤ ኢያ​ሱን ጠር​ተህ እር​ሱን አዝ​ዘው ዘንድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ቁም” አለው። ሙሴና ኢያ​ሱም ሄደው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ቆሙ። 15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በደ​መና ዐምድ ወረደ፤ የደ​መ​ና​ውም ዐምድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ላይ ቆመ። 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ታን​ቀ​ላ​ፋ​ለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነ​ሣል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ዘንድ በሚ​ሄ​ድ​ባት ምድር መካ​ከል ያሉ​ትን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ እኔ​ንም ይተ​ወ​ኛል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ያፈ​ር​ሳሉ። 17በዚ​ያም ቀን ቍጣዬ ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እተ​ዋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መብል ይሆ​ናሉ፤ በዚ​ያም ቀን፦ በእ​ው​ነት አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ና​ልና፥ በእ​ኛም መካ​ከል የለ​ምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገ​ኘን እስ​ኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት ይደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋል። 18ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና ስላ​ደ​ረ​ጉት ክፋት ሁሉ እኔ በዚያ ቀን ፈጽሜ ፊቴን እሰ​ው​ራ​ለሁ። 19አሁ​ንም ይህ​ችን መዝ​ሙር ለእ​ና​ንተ ጻፉ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ ይህ​ችም መዝ​ሙር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምስ​ክር ትሆ​ን​ልኝ ዘንድ በአ​ፋ​ቸው አድ​ር​ጓት። 20ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ካገ​ባ​ኋ​ቸው በኋላ፥ ከበ​ሉም፥ ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ይስ​ታሉ፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ወደ ማም​ለክ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እኔ​ንም ያስ​ቈ​ጡ​ኛል፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ። 21ዛሬ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ገና ሳላ​ገ​ባ​ቸው ክፋ​ታ​ቸ​ውን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ከአ​ፋ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም አፍ አት​ረ​ሳ​ምና ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት በደ​ረ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይህች መዝ​ሙር ምስ​ክር ሆና በፊ​ታ​ቸው ትቆ​ማ​ለች።”#ዕብ. “ትመ​ሰ​ክ​ራ​ለች” ይላል። 22ሙሴም በዚያ ቀን ይህ​ችን መዝ​ሙር ጻፈ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ማ​ራት። 23የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ታገ​ባ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ፤ እር​ሱም ከአ​ንተ #ዕብ. ምዕ. 31 ቍ. 23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባለ​ቤት አድ​ርጎ በአ​ን​ደኛ መደብ ይጽ​ፋል። ጋር ይሆ​ናል” ብሎ አዘ​ዘው።
24እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች እስከ መጨ​ረሻ በመ​ጽ​ሐፍ ጽፎ ከፈ​ጸመ በኋላ፥ 25የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦ 26“ይህን የሕግ መጽ​ሐፍ ውሰዱ፤ በዚ​ያም በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር እን​ዲ​ሆን በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠ​ገብ አኑ​ሩት። 27እኔ ዐመ​ፃ​ች​ሁ​ንና የአ​ን​ገ​ታ​ች​ሁን ድን​ዳኔ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እኔም ዛሬ ከእ​ና​ንተ ጋር ገና በሕ​ይ​ወት ሳለሁ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋል፤ ይል​ቁ​ንስ ከሞ​ትሁ በኋላ እን​ዴት ይሆ​ናል? 28ይህን ቃል በጆ​ሮ​አ​ቸው እነ​ግር ዘንድ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንም አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸው ዘንድ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁን አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ፥ ሹሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ጻፎ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሰብ​ስ​ቡ​ልኝ፤ 29ከሞ​ትሁ በኋላ ፈጽ​ማ​ችሁ እን​ድ​ት​ረ​ክሱ፥ ካዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም መን​ገድ ፈቀቅ እን​ድ​ትሉ አው​ቃ​ለ​ሁና። በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ታስ​ቈ​ጡት ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገ​ኛ​ች​ኋል።”
የሙሴ መዝ​ሙር
30ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚ​ህ​ችን መዝ​ሙር ቃሎች እስከ መጨ​ረ​ሻው ድረስ ተና​ገረ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in