YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 3

3
የገ​ላ​ት​ያን ሰዎች ስለ መገ​ሠጹ
1እና​ንተ ሰነ​ፎች የገ​ላ​ትያ ሰዎች ሆይ፥ ለዐ​ይን በሚ​ታ​የው እው​ነት#ግሪኩ “እና​ንተ ሰነ​ፎች የገ​ላ​ትያ ሰዎች ሆይ ለጽ​ድቅ እን​ዳ​ት​ታ​ዘዙ ማን አታ​ለ​ላ​ችሁ ቀድ​ሞስ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት እንደ ተሰ​ቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር” ይላል። እን​ዳ​ታ​ምኑ ማን አታ​ለ​ላ​ችሁ? እር​ሱም እን​ዲ​ሰ​ቀል አስ​ቀ​ድሞ የተ​ጻ​ፈ​ለት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው። 2በእ​ና​ንተ ዘንድ ይህን ብቻ ላውቅ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት? 3እን​ዲ​ህን ሰነ​ፎች ናች​ሁን? የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ሥራ ከጀ​መ​ራ​ችሁ በኋላ የሥ​ጋን ሕግ ልት​ሠሩ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ች​ሁን? 4ይህን ያህል መከራ ተቀ​ብ​ላ​ችሁ፥ ለከ​ንቱ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት።#ግሪኩ “በውኑ ከንቱ ከሆነ እን​ደ​ዚህ ያለ መከራ በከ​ንቱ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁን” ይላል። 5እርሱ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የሚ​ሰ​ጣ​ችሁ፥ ኀይ​ል​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት ነው?
ስለ አብ​ር​ሃም እም​ነ​ትና ተስ​ፋው
6 # ዘፍ. 15፥6፤ ሮሜ 4፥3። አብ​ር​ሃም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አመነ፥ ጽድ​ቅም ሆኖ እንደ ተቈ​ጠ​ረ​ለት፥ 7#ሮሜ 4፥16። እን​ግ​ዲህ ያመ​ኑት የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች እንደ ሆኑ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 8#ዘፍ. 12፥3። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሕ​ዛ​ብን በእ​ም​ነት እን​ደ​ሚ​ያ​ጸ​ድ​ቃ​ቸው መጽ​ሐፍ አስ​ቀ​ድሞ ገል​ጦ​አ​ልና፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ በእ​ርሱ እን​ዲ​ባ​ረኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ብ​ር​ሃም ተስፋ ሰጠው።#ግሪኩ “በአ​ንተ አሕ​ዛብ ሁሉ ይባ​ረ​ካሉ ብሎ ወን​ጌ​ልን ለአ​ብ​ር​ሃም አስ​ቀ​ድሞ ሰበከ” ይላል። 9አሁ​ንም የሚ​ያ​ምኑ ከአ​መ​ነው ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ይባ​ረ​ካሉ።
10 # ዘዳ. 27፥26። በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።” 11#ዕን. 2፥4። የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራ​ትስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቁ ይታ​ወ​ቃል፤ “ጻድቅ ግን በእ​ም​ነት ይድ​ናል” ተብሎ ተጽ​ፎ​አል። 12#ዘሌ. 18፥5። ኦሪ​ትስ ሠርቶ የፈ​ጸመ ይኖ​ር​በ​ታል እንጂ በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ አይ​ደ​ለም። 13#ዘዳ. 21፥23። እኛ​ንስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እኛ የኦ​ሪ​ትን መር​ገም በመ​ሸ​ከሙ ከኦ​ሪት መር​ገም ዋጅ​ቶ​ናል፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ ሁሉ ርጉም ነው።” 14እኛ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነን የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ እን​ድ​ና​ገኝ የአ​ብ​ር​ሃም በረ​ከት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለስ ዘንድ።
ስለ ኦሪ​ትና ስለ ተስ​ፋው
15ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ሰውም እን​ኳን የጸ​ና​ውን ኪዳን አይ​ን​ቅም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ት​ምም። 16#ዘፍ. 12፥7። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም፥ “ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ” ብሎ ተስፋ ሰጠው፤ ለብ​ዙ​ዎች እን​ደ​ሚ​ና​ገር አድ​ርጎ ለአ​ን​ተና ለዘ​ሮ​ችህ አላ​ለ​ውም፤ ለአ​ንድ እን​ደ​ሚ​ና​ገር አድ​ርጎ፥ “ለዘ​ርህ” አለው እንጂ ይኸ​ውም ክር​ስ​ቶስ ነው። 17#ዘፀ. 12፥40። እን​ግ​ዲህ እን​ዲህ እላ​ለሁ፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጠ ይህ ኪዳን ጽኑዕ ነው፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኦሪት መጣች፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ልት​ከ​ለ​ክል አይ​ደ​ለም። 18#ሮሜ 4፥14። መው​ረስ የኦ​ሪ​ትን ሕግ በመ​ሥ​ራት ከሆነ እን​ግ​ዲህ በሰ​ጠው ተስፋ አይ​ደ​ለማ፤ እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ብ​ር​ሃም ተስ​ፋ​ውን ሰጠው። 19ታዲያ ኦሪት ለምን ተሠ​ራች? ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ፥ ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለት ያ ዘር እስ​ኪ​መጣ ድረስ፥ በመ​ላ​እ​ክት በኩል በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው እጅ ወረ​ደች። 20መካ​ከ​ለ​ኛው ግን ማንም አይ​ደ​ለም፤ አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ።#ግሪኩ “መካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ለአ​ንድ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አንድ ነው” ይላል።
21እን​ግ​ዲህ ኦሪት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ልት​ከ​ለ​ክል መጣ​ችን? አይ​ደ​ለም፤ ማዳን የሚ​ቻ​ለው ሕግ ተሠ​ርቶ ቢሆ​ንማ፥ በእ​ው​ነት በዚያ ሕግ ጽድቅ በተ​ገኘ ነበር። 22ነገር ግን ተስፋ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ይሆን ዘንድ፥ ያመ​ኑ​ትም ያገ​ኙት ዘንድ፥ መጽ​ሐፍ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ዘግ​ቶ​ታል።
ስለ ሃይ​ማ​ኖት መም​ጣት
23እም​ነት ሳይ​መጣ ኦሪት ጠበ​ቀ​ችን፤ ወደ​ሚ​መ​ጣ​ውም እም​ነት መራ​ችን።#ግሪኩ “እም​ነ​ትም ሳይ​መጣ ይገ​ለጥ ዘንድ ላለው እም​ነት ተዘ​ግ​ተን ከሕግ በታች እን​ጠ​በቅ ነበር” ይላል። 24እን​ግ​ዲህ ኦሪት በእ​ርሱ በማ​መን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ ወደ ክር​ስ​ቶስ መሪ ሆነ​ችን። 25እን​ግ​ዲህ እም​ነት ከመ​ጣች መሪ አን​ሻም። 26በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ሁላ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሆነ​ና​ልና። 27በክ​ር​ስ​ቶስ የተ​ጠ​መ​ቃ​ችሁ እና​ን​ተማ ክር​ስ​ቶ​ስን ለብ​ሳ​ች​ኋል። 28በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና። 29#ሮሜ 4፥13። ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ና​ች​ሁም እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋ​ውን የም​ት​ወ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እና​ንተ ናችሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in