YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 45

45
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቂሮ​ስን ለን​ጉ​ሥ​ነት እንደ መረጠ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ለቀ​ባ​ሁት፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በፊቱ አስ​ገዛ ዘንድ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮ​ቹም እን​ዳ​ይ​ዘጉ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በፊቱ እከ​ፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ​ዝ​ሁት ለቂ​ሮስ እን​ዲህ ይላል፦ 2“በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ዝቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የና​ሱ​ንም ደጆች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ 3በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ። 4ስለ አገ​ል​ጋዬ ስለ ያዕ​ቆብ፥ ስለ መረ​ጥ​ሁ​ትም ስለ እስ​ራ​ኤል ብዬ በስ​ምህ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ተቀ​በ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም። 5እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ አጸ​ና​ሁህ፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም። 6በፀ​ሐይ መው​ጫና በም​ዕ​ራብ ያሉ ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ያውቁ ዘንድ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም ሌላ አም​ላክ የለም። 7ብር​ሃ​ንን ፈጠ​ርሁ፤ ጨለ​ማ​ው​ንም ፈጠ​ርሁ፤ ሰላ​ም​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፋ​ት​ንም አመ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ያደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።
8“ሰማይ በላይ ደስ ይበ​ለው፤ ደመ​ና​ትም ጽድ​ቅን ያዝ​ንቡ፤ ምድ​ርም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታብ​ቅል፤ ጽድ​ቅም በአ​ን​ድ​ነት ይብ​ቀል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ፈጥ​ሬ​ሃ​ለሁ።
9“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድ​ርጌ ሠራ​ሁህ፤ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን፦ ምን ትሠ​ራ​ለህ? እጅ የለ​ህ​ምና መሥ​ራት አት​ች​ልም ይለ​ዋ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን ይከ​ራ​ከ​ረ​ዋ​ልን? 10አባ​ቱን፦ ለምን ወለ​ድ​ኸኝ? እና​ቱ​ንም፦ ለምን አም​ጠሽ ወለ​ድ​ሽኝ? ለሚል ወዮ!
11“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም የፈ​ጠረ#ዕብ. “የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ ሠሪ​ውም፥ እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ሚ​መ​ጣው ነገር ጠይ​ቁኝ ...” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ጠይ​ቁኝ፤ ስለ እጄም ሥራ እዘ​ዙኝ። 12እኔ ምድ​ርን ሠር​ቻ​ለሁ፤ ሰው​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማ​ያ​ትን አጽ​ን​ቼ​አ​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም#ዕብ. “ሰራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም” ይላል። ሁሉ አዝ​ዣ​ለሁ። 13እኔ ቂሮ​ስን በጽ​ድቅ አስ​ነ​ሥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ አቀ​ና​ለሁ፤ እርሱ ከተ​ማ​ዬን ይሠ​ራል፤ በዋ​ጋም ወይም በጉቦ ሳይ​ሆን ምር​ኮ​ኞ​ችን ያወ​ጣል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”
14የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል። 15አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መድ​ኀ​ኒት አም​ላክ እንደ ሆንህ አላ​ወ​ቅ​ን​ህም።#ዕብ. “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ መድ​ኀ​ኒት ሆይ በእ​ው​ነት አንተ ራስ​ህን የም​ት​ሰ​ውር አም​ላክ ነህ” ይላል። 16የሚ​ቃ​ወ​ሙት ሁሉም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ አፍ​ረ​ውም ይሄ​ዳሉ። 17ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ እና​ን​ተም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ፍ​ሩ​ምና አቷ​ረ​ዱም።”
18ሰማ​ይን የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እር​ሱም ምድ​ርን የሠ​ራና ያደ​ረገ ያጸ​ና​ትም፥ መኖ​ሪ​ያም ልት​ሆን እንጂ ለከ​ንቱ እን​ድ​ት​ሆን ያል​ፈ​ጠ​ራት አም​ላክ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም። 19በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ። 20እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም። 21የሚ​ና​ገሩ ከሆነ ከጥ​ንት ጀምሮ ይህን ምስ​ክ​ር​ነት ያደ​ረገ ማን እንደ ሆነ በአ​ን​ድ​ነት ያውቁ ዘንድ ይቅ​ረቡ። ያሳ​የ​ሁም የተ​ና​ገ​ር​ሁም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አም​ላ​ክና መድ​ኀ​ኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም። 22እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ። 23ቃሌ ከአፌ በጽ​ድቅ ወጥ​ታ​ለች፤ አት​መ​ለ​ስ​ምም፤ ጕል​በት ሁሉ ለእኔ ይን​በ​ረ​ከ​ካል፤ ምላ​ስም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይም​ላል ብዬ በራሴ ምያ​ለሁ።” 24ክብ​ርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ርቁ ሁሉ ያፍ​ራሉ። 25የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ድ​ቃሉ፤ ይከ​ብ​ራ​ሉም ይባ​ላል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 45