YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 46

46
የባ​ቢ​ሎን አማ​ል​ክት
1ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰ​ባ​በረ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የተ​ቀ​ረጹ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸው በእ​ን​ስ​ሳና በከ​ብት ላይ ተጭ​ነ​ዋል እንደ ደካማ ሸክም አስ​ራ​ችሁ ውሰ​ዱ​አ​ቸው” ይላል። ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራ​ዊ​ትና እን​ስ​ሳም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ እንደ ፋን​ድ​ያም ሸክም የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና አያ​ነ​ሡ​አ​ቸ​ውም። 2ደካ​ሞች ናቸው፤ ኀይ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ከጦ​ር​ነ​ትም ራሳ​ቸ​ውን ለማ​ዳን አል​ቻ​ሉም፤ ራሳ​ቸው ግን ተማ​ረኩ።
3እና​ንተ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ጀምሮ የተ​ሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትም ጀምሮ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ ስሙኝ። 4እስከ ሽም​ግ​ልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበ​ትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ሠር​ቻ​ለሁ፤ እኔም ይቅር እላ​ለሁ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ። 5እን​ግ​ዲህ በማን ትመ​ስ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የም​ት​ሳ​ሳቱ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ እዩ፤ አስ​ተ​ው​ሉም። 6ወር​ቁ​ንና ብሩን ከኮ​ሮጆ የሚ​ያ​ወ​ጡና በሚ​ዛን የሚ​መ​ዝኑ እነ​ርሱ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን ይቀ​ጥ​ራሉ፤ እር​ሱም ጣዖት አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ዋል፤ ለዚ​ያም ይጐ​ነ​በ​ሱ​ለ​ታል፤ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ት​ማል። 7በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።
8ይህን ዐስ​ቡና አል​ቅሱ፤ የተ​ሳ​ሳ​ታ​ችሁ ሆይ፥ ንስሓ ግቡ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም መልሱ። 9እኔ አም​ላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለ​ምና የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የጥ​ን​ቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም። 10በመ​ጀ​መ​ሪያ መጨ​ረ​ሻ​ውን፥ ከጥ​ን​ትም ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ምክሬ ትጸ​ና​ለች፤ የመ​ከ​ር​ሁ​ት​ንም ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ እላ​ለሁ። 11ከም​ሥ​ራ​ቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከ​ር​ሁት ምክር ዎፍን እጠ​ራ​ለሁ፤ ተና​ገ​ርሁ፤ አመ​ጣ​ሁም፤ ፈጠ​ርሁ፤ አደ​ረ​ግ​ሁም፤ አመ​ጣ​ሁት፤ መን​ገ​ዱ​ንም አቀ​ና​ሁ​ለት።
12እና​ንተ ከጽ​ድቅ የራ​ቃ​ችሁ ልበ ጥፉ​ዎች፥ ስሙኝ፤ 13ጽድ​ቄን አመ​ጣ​ኋት፤ ከእኔ ዘንድ የም​ት​ገኝ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም አላ​ዘ​ገ​ይም፤ ከጽ​ዮን ለክ​ብር እን​ዲ​ሆን መድ​ኀ​ኒ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጥ​ቻ​ለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 46