YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 13

13
ገና ያል​ተ​ያዙ ግዛ​ቶች
1ኢያ​ሱም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ ዘመ​ንህ አለፈ፤ ያል​ተ​ወ​ረ​ሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀር​ታ​ለች፤ 2የቀ​ረ​ች​ውም ምድር ይህች ናት፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ የጌ​ሴ​ር​ያ​ው​ያ​ንና የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሀገር ሁሉ፥ 3በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤ 4ከደ​ቡብ ጀምሮ በጋ​ዛና በሲ​ዶና ፊት ያለ​ውን የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ እስከ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥ 5በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ያለው የጌ​ባ​ላ​ው​ያን ምድር ሁሉ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ከአ​ር​ሞ​ን​ዔም ተራራ በታች ካለ​ችው ጌል​ገላ#ዕብ. “በአ​ል​ጋድ” ይላል። ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ ያለ​ችው ሊባ​ኖስ ሁሉ፥ 6በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከሊ​ባ​ኖስ ጀምሮ እስከ ማሴ​ሬ​ት​ሜ​ም​ፎ​ማ​ይም መያ​ያዣ ድረስ ሲዶ​ና​ው​ያን ሁሉ፤ እነ​ዚ​ህን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ር​ገህ አካ​ፍ​ላ​ቸው። 7አሁ​ንም ይህን ምድር ለዘ​ጠኙ ነገድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገህ ክፈ​ለው። ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በም​ዕ​ራብ እስ​ካ​ለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል።”#“ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በም​ዕ​ራብ እስ​ካ​ለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል” የሚ​ለው በዕብ. የለም።
በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምሥ​ራቅ ያለው ግዛት አከ​ፋ​ፈል
8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ ሰጣ​ቸው ከእ​ርሱ ከም​ናሴ ጋር የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ። 9በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ካለ​ችው ከተማ ጀምሮ የሚ​ሶር ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥ 10በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገሠ የአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተ​ሞ​ችን ሁሉ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥ 11ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥ 12በባ​ሳን የነ​በ​ረ​ውን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የነ​ገ​ሠ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ሁሉ፤ እር​ሱም ከረ​ዓ​ይት የቀረ ነበረ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሙሴ አወ​ጣ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም። 13የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን ጌሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ንን፥ መከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ን​ንና ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴ​ሪና መከጢ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይኖ​ራሉ። 14ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አል​ተ​ሰ​ጠም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና፥ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ሜዳ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዳ​ካ​ፈ​ላ​ቸው እን​ዲሁ ተካ​ፈሉ።
ለሮ​ቤል ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
15ሙሴም ለሮ​ቤል ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ርስ​ትን ሰጣ​ቸው። 16ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ በሸ​ለ​ቆው መካ​ከል ያለ​ችው ከተማ፥ ሜሶ​ርም ሁሉ፥ 17ሐሴ​ቦን፥ በሜ​ሶ​ርም ያሉት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞ​ት​በ​ዐል፥ ቤት​በ​አ​ል​ም​ዖን፥ 18ባሳን፥ ቀዲ​ሞት፥ ሜፍዓ፥ 19ቂር​ያ​ታ​ይም፥ ሴባማ፥ ሲራ​ዳት፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም ተራራ ያለ​ችው ሲዮን፥ 20ቤተ ፌጎር፥ ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤት​ሲ​ሞት፥ 21የሚ​ሶር ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገ​ሠው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እር​ሱ​ንና በም​ድ​ሪቱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን የሴ​ዎ​ንን መሳ​ፍ​ንት፥ የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ኤዊን፥ ሮቦ​ቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲ​ዮን የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ገደ​ላ​ቸው። 22ሟር​ተ​ኛ​ውን የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ም​ንም በአ​ን​ድ​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት። 23የሮ​ቤ​ልም ልጆች ድን​በር የዮ​ር​ዳ​ኖስ ወን​ዝና ዳር​ቻው ነበረ። የሮ​ቤል ልጆች ርስት ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።
ለጋድ ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
24ሙሴም ለጋድ ነገድ ለጋ​ድም ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ሰጣ​ቸው። 25ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥ 26ከሐ​ሴ​ቦን ጀምሮ እስከ አራ​ቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣ​ኒም ድረስ፥ ከማ​ኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥ 27በሸ​ለ​ቆ​ውም ቤት​ሀ​ራም፥ ቤት​ን​ምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ቅሬታ ነበረ። ድን​በ​ሩም ዮር​ዳ​ኖ​ስና በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የኬ​ኔ​ሬት ባሕር ወዲ​ያ​ኛው ዳርቻ ነበረ። 28የጋድ ልጆች ርስት ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት ጀር​ባ​ቸ​ውን መል​ሰው ሸሹ፤ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ሆነ​ዋ​ልና።
ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ሰጠ ርስት
29ሙሴም ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ርስት ሰጣ​ቸው፤ 30ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ና​ይም ጀምሮ የባ​ሳን ንጉሥ የዐግ መን​ግ​ሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባ​ሳ​ንም ያሉት የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ሁሉ ስድ​ሳው ከተ​ሞች፥ የገ​ለ​ዓ​ድም እኩ​ሌታ፥ 31በባ​ሳ​ንም ያሉት የዐግ መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች፥ አስ​ጣ​ሮ​ትና ኤድ​ራ​ይን ነበረ። እነ​ዚ​ህም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች ሆኑ፤ ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች እኩ​ሌ​ታም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።
32ሙሴ በም​ሥ​ራቅ በኩል በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ሜዳ ሳለ ርስት ያካ​ፈ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።#ዕብ. የግ​እ​ዙና የግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 13 ቍ. 14ን ቍ. 33ኛ ያደ​ር​ጋል ፤ ግእ​ዙና ግሪክ ሰባ. ሊ. ደግሞ የዕብ. ምዕ. 13 ቍ. 14ን አይ​ጽ​ፍም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in