መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 13
13
ገና ያልተያዙ ግዛቶች
1ኢያሱም ሸመገለ፤ ዘመኑም አለፈ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፥ “እነሆ ዘመንህ አለፈ፤ ያልተወረሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርታለች፤ 2የቀረችውም ምድር ይህች ናት፤ የፍልስጥኤማውያን፥ የጌሴርያውያንና የከነዓናውያን ሀገር ሁሉ፥ 3በግብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአምስቱ የፍልስጥኤም ግዛቶች ለጋዛ፥ ለአዛጦን፥ ለአስቀሎና፥ ለጌት፥ ለአቃሮን፥ እንዲሁም ለኤዌዎናውያን በተቈጠረችው በከነዓን ግራ በኩል እስካለችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤ 4ከደቡብ ጀምሮ በጋዛና በሲዶና ፊት ያለውን የከነዓናውያን ምድር ሁሉ እስከ አሞሬዎናውያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥ 5በፍልስጥኤም ያለው የጌባላውያን ምድር ሁሉ፥ በምሥራቅም በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው ጌልገላ#ዕብ. “በአልጋድ” ይላል። ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥ 6በተራራማውም ሀገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሬትሜምፎማይም መያያዣ ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ፤ እነዚህን ከእስራኤል ልጆች ፊት አጠፋቸዋለሁ፤ እንዳዘዝሁህም ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ አካፍላቸው። 7አሁንም ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ ክፈለው። ከዮርዳኖስ ጀምሮ በምዕራብ እስካለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰጣቸዋለህ፤ ድንበራቸውም ታላቁ ባሕር ይሆናል።”#“ከዮርዳኖስ ጀምሮ በምዕራብ እስካለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰጣቸዋለህ ፤ ድንበራቸውም ታላቁ ባሕር ይሆናል” የሚለው በዕብ. የለም።
በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለው ግዛት አከፋፈል
8የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከእርሱ ከምናሴ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ። 9በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር፥ በሸለቆውም መካከል ካለችው ከተማ ጀምሮ የሚሶር ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥ 10በሐሴቦንም የነገሠ የአሞሬዎን ንጉሥ የሴዎን ከተሞችን ሁሉ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥ 11ገለዓድንም፥ የጌሴሪያውያንንና የመከጢያውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳንንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥ 12በባሳን የነበረውን፥ በአስታሮትና በኤንድራይን የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ከረዓይት የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ አወጣቸው፤ ገደላቸውም። 13የእስራኤል ልጆች ግን ጌሴሪያውያንን፥ መከጢያውያንንና ከነዓናውያንን አላጠፉአቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴሪና መከጢ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ። 14ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልተሰጠም፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ርስታቸው ነውና፥ በኢያሪኮ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች እንዳካፈላቸው እንዲሁ ተካፈሉ።
ለሮቤል ነገድ የተሰጠ ርስት
15ሙሴም ለሮቤል ነገድ በየወገናቸው ርስትን ሰጣቸው። 16ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ ሜሶርም ሁሉ፥ 17ሐሴቦን፥ በሜሶርም ያሉት ከተሞች ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞትበዐል፥ ቤትበአልምዖን፥ 18ባሳን፥ ቀዲሞት፥ ሜፍዓ፥ 19ቂርያታይም፥ ሴባማ፥ ሲራዳት፥ በሸለቆውም ተራራ ያለችው ሲዮን፥ 20ቤተ ፌጎር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤትሲሞት፥ 21የሚሶር ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞሬዎናውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቦቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲዮን የሚኖሩትንም ገደላቸው። 22ሟርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በአንድነት በሰይፍ ገደሉት። 23የሮቤልም ልጆች ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝና ዳርቻው ነበረ። የሮቤል ልጆች ርስት ከተሞቻቸውም መንደሮቻቸውም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ለጋድ ነገድ የተሰጠ ርስት
24ሙሴም ለጋድ ነገድ ለጋድም ልጆች በየወገኖቻቸው ርስት አድርጎ ሰጣቸው። 25ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በራባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥ 26ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ አራቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣኒም ድረስ፥ ከማኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥ 27በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትንምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኬኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበረ። 28የጋድ ልጆች ርስት ከተሞቻቸውም፥ መንደሮቻቸውም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። በጠላቶቻቸውም ፊት ጀርባቸውን መልሰው ሸሹ፤ መንደሮቻቸውና ከተሞቻቸው በየወገናቸው ሆነዋልና።
ለምናሴ ነገድ እኩሌታ የተሰጠ ርስት
29ሙሴም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በየወገኖቻቸው ርስት ሰጣቸው፤ 30ድንበራቸውም ከመሐናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥ የገለዓድም እኩሌታ፥ 31በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስጣሮትና ኤድራይን ነበረ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች እኩሌታም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
32ሙሴ በምሥራቅ በኩል በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሳለ ርስት ያካፈላቸው እነዚህ ናቸው።#ዕብ. የግእዙና የግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 13 ቍ. 14ን ቍ. 33ኛ ያደርጋል ፤ ግእዙና ግሪክ ሰባ. ሊ. ደግሞ የዕብ. ምዕ. 13 ቍ. 14ን አይጽፍም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 13: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: