YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 5

5
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል#“በባ​ሕር በኩል” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ።
የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በጌ​ል​ጌላ እንደ ተገ​ረዙ
2በዚ​ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን፥ “ከሻፎ ድን​ጋይ የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠር​ተህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዳግ​መኛ ግረ​ዛ​ቸው” አለው። 3ኢያ​ሱም የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠርቶ የግ​ር​ዛት ኮረ​ብታ በተ​ባለ ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ገረዘ። 4ኢያሱ ሕዝ​ቡን ሁሉ የገ​ረ​ዘ​በት ምክ​ን​ያት ይህ ነው፤ ከግ​ብፅ የወጡ ወን​ዶች ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ ላይ በም​ድረ በዳ ሞቱ፤ የወ​ጡ​ትም ወን​ዶች ሁሉ ተገ​ር​ዘው ነበር። 5ነገር ግን ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ፥ በም​ድረ በዳ የተ​ወ​ለዱ ሕዝብ ሁሉ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና፥ ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ገረ​ዛ​ቸው። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ለእኛ ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር እን​ደ​ማ​ያ​ሳ​ያ​ቸው የማ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከግ​ብፅ የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያል​ሰሙ፥ እነ​ዚያ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አርባ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አርባ ሁለት” ይላል። ዓመት በመ​ድ​በራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር። 7ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ አስ​ነሣ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ኢያሱ ገረ​ዛ​ቸው፤ በመ​ን​ገድ ስለ​ተ​ወ​ለዱ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና። 8በተ​ገ​ረ​ዙም ጊዜ እስ​ኪ​ድኑ ድረስ በሰ​ፈር ውስጥ ተቀ​መጡ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ዛሬ የግ​ብ​ፅን ተግ​ዳ​ሮት ከእ​ና​ንተ ላይ አስ​ወ​ግ​ጃ​ለሁ” አለው፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌል​ገላ ተብሎ ተጠራ።
10የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤#“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ጌላ ሰፈሩ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ። 11#ዕብ. “ከፋ​ሲ​ካው በኋላ በነ​ጋው” የሚል ይጨ​ም​ራል።ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ። 12በነ​ጋ​ውም ከም​ድ​ሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዳግ​መኛ መና አላ​ገ​ኙም፤ በዚ​ያው ዓመት የፊ​ኒ​ቆ​ንን ምድር ፍሬ ሰበ​ሰቡ።
ኢያ​ሱና ባለ ሰይፉ ሰው
13እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢ​ያ​ሪኮ አጠ​ገብ ሳለ ዐይ​ኑን አን​ሥቶ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ የተ​መ​ዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያ​ሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ወገን ነህ?” አለው። 14እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው። 15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ኢያ​ሱን፥ “አንተ የቆ​ም​ህ​በት ስፍራ የተ​ቀ​ደሰ ነውና ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ” አለው። ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ።#“ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in