የማቴዎስ ወንጌል 8
8
ኢየሱስ ለምጻሙን ሰው እንደፈወሰ
(ማር. 1፥40-45፤ ሉቃ. 5፥12-16)
1ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። 2እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ “ጌታ ሆይ! ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” እያለ ሰገደለት። 3እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ። 4ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።
ኢየሱስ የመቶ አለቃውን ልጅ እንደፈወሰ
(ሉቃ. 7፥1-10)
5ወደ ቅፍርናሆምም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ 6“ጌታ ሆይ!ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል” ብሎ ለመነው። 7ኢየሱስም “እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው። 8የመቶ አለቃውም መልሶ “ጌታ ሆይ! በቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል። 9እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፤ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም ‘ሂድ’ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና’ ብለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም ‘ይህን አድርግ’ ብለው ያደርጋል” አለው። 10ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም። 11እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤ 12የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” 13ኢየሱስም ለመቶ አለቃ “ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።
ጌታ ብዙዎችን ከደዌ እንደፈወሰ
(ማር. 1፥29-34፤ ሉቃ. 4፥38-41)
14ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤ 15እጅዋንም ዳሰሰ፤ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለቻቸው። 16-17በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃኣሉ አወጣ፤ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።
ጌታን ለመከተል ስለጠየቁ ሰዎች
(ሉቃ. 9፥57-62)
18ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። 19አንድ ጸሐፊም ቀርቦ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው። 20ኢየሱስም “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤” አለው። 21ከደቀ መዛሙርቱም ሌላው “ጌታ ሆይ! አስቀድሜ እንድሄድ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለው። 22ኢየሱስ “ተከተለኝ፤ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤” አለው።
ጌተ ማዕበሉን ጸጥ እንዳደረገ
(ማር. 4፥35-41፤ ሉቃ. 8፥22-25)
23ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። 24እነሆም ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። 25ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! አድነን፤ ጠፋን፤” እያሉ አስነሡት። 26እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። 27ሰዎቹም “ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” እያሉ ተደነቁ።
ጌታ በአጋንንት የተያዙ ሁለት ሰዎችን እንደ አዳነ
(ማር. 5፥1-20፤ ሉቃ. 8፥26-29)
28ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ። 29እነሆም “ኢየሱስ ሆይ! የእግዚአብሔር ልጅ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?” እያሉ ጮኹ። 30ከእነርሱም ርቆ የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር። 31አጋንንቱም “ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። “ሂዱ፤” አላቸው። 32እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ፤ በውሃም ውስጥ ሞቱ። 33እረኞችም ሸሹ፤ ወደ ከተማይቱም ሄደው ነገሩን ሁሉ አጋንንትም በአደሩባቸው የሆነውን አወሩ። 34እነሆም ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት።
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 8: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: