የማቴዎስ ወንጌል 9
9
ኢየሱስ ሽባውን እንደፈወሰ
(ማር. 2፥1-12፤ ሉቃ. 5፥17-26)
1በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ። 2እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው። 3እነሆም ከጻፎቹ አንዳንዶቹ በልባቸው “ይህስ ይሳደባል፤” አሉ። 4ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ? 5‘ኀጢአትህ ተሰረየችልህ’ ከማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ከማለት ማናቸው ይቀላል? 6ነገር ግን በምድር ላይ ኀጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” በዚያን ጊዜ ሽባውን “ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው። 7ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ። 8ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፤ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።
ኢየሱስ ማቴዎስን እንደ ጠራ
(ማር. 2፥13-17፤ ሉቃ. 5፥27-35)
9ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።
10በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ። 11ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው። 12ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤነኞች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ 13ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።
ስለ ጾም የቀረበ ጥያቄ
(ማር. 2፥18-22፤ ሉቃ. 5፥33-39)
14በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው?” አሉት። 15ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ። 16በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። 17በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፤ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።”
ስለ ምኵራብ አለቃ ልጅና ደም ስለሚፈሳት ሴት
(ማር. 5፥21-43፤ ሉቃ. 8፥40-56)
18ይህንም ሲነግራቸው አንድ መኰንን መጥቶ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” እያለ ሰገደለት። 19ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው። 20እነሆም ከዐሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ 21በልብዋ “ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ፤” ትል ነበረችና። 22ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና “ልጄ ሆይ! አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል፤” አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች። 23ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ 24“ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ፤” አላቸው። በጣምም ሳቁበት። 25ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፤ ብላቴናይቱም ተነሣች። 26ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ።
ኢየሱስ ሁለት ዐይነ ስውሮችን እንደ አዳነ
27ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት። 28ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ኢየሱስም “ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን?” አላቸው። “አዎን፥ ጌታ ሆይ!” አሉት። 29በዚያን ጊዜ “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ፤” ብሎ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ። 30ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ኢየሱስም “ማንም እንዳያውቅ ተጠንቀቁ፤” ብሎ በብርቱ አዘዛቸው። 31እነርሱ ግን ወጥተው በዚያ አገር ሁሉ ስለ እርሱ አወሩ።
ኢየሱስ አንድ ድዳ ሰው እንደ ፈወሰ
32እነርሱም ሲወጡ እነሆ ጋኔን ያደረበትን ድዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። 33ጋኔኑንም ካወጣው በኋላ ድዳው ተናገረ። ሕዝቡም “እንዲህ ያለ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልታየም፤” እያሉ ተደነቁ። 34ፈሪሳውያን ግን “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ።
35ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር። 36ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው። 37በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “መከሩስ ብዙ ነው፤ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ 38እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፤” አላቸው።
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 9: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: