መዝሙረ ዳዊት 22
22
የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ይጠብቀኛል፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤
በዕረፍት ውኃ ዘንድ አሳደገኝ።
3ነፍሴን መለሳት፥
ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ፥
አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤
በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል።
5በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፥
በሚያሠቃዩኝ ሰዎች፤ ፊት ለፊት
ራሴን በዘይት ቀባህ፥
ጽዋህም የተትረፈረፈ ነው፥ ያረካልም።
6ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተለኝ፤
በእግዚአብሔር ቤት ለረዥም ዘመን እኖር ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 22: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in