YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 28

28
ከድ​ን​ኳን በመ​ው​ጣት ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1የአ​ማ​ል​ክት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአ​ም​ላክ ልጆች” ይላል። ልጆች ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥
የጊ​ደ​ሮ​ችን ጥጃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ።#“የጊ​ደ​ሮ​ችን ጥጃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ” የሚ​ለው በዕብ. የለም።
ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥
2የስ​ሙን ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥
በቅ​ድ​ስ​ናው ስፍራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ።
3የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በው​ኆች ላይ ነው።
የክ​ብር አም​ላክ አን​ጐ​ደ​ጐደ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ውኆች ላይ ነው።
4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በኀ​ይል ነው፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በታ​ላቅ ክብር ነው።
5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዝግ​ባን ይሰ​ብ​ራል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሊ​ባ​ኖ​ስን ዝግባ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል።
6እንደ ሊባ​ኖስ ላም ያከ​ሳ​ዋል።#ዕብ. “እንደ ጥጃ ሊባ​ኖ​ስን ያዘ​ል​ለ​ዋል” ይላል።
ተወ​ዳጅ ግን አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ርኤም ልጅ ነው።
7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ሳ​ቱን ነበ​ል​ባል ይቈ​ር​ጣል።
8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ምድረ በዳ​ውን ያና​ው​ጣል፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ዴ​ስን ምድረ በዳ ያና​ው​ጣል።
9የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዋሊ​ያ​ዎ​ችን ያጠ​ነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል፥
ዛፎ​ች​ንም ይገ​ል​ጣል፤ ሁሉም በመ​ቅ​ደሱ፦ ምስ​ጋና ይላል።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​ፋት ውኃን ሰብ​ስ​ቦ​አል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ ሆኖ ይቀ​መ​ጣል።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በሰ​ላም ይባ​ር​ካ​ቸ​ዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in