መዝሙረ ዳዊት 3
3
የዳዊት መዝሙር፥ ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ።
1አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ!
በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
2ብዙ ሰዎች ነፍሴን አልዋት፦
“አምላክሽ አያድንሽም።”
3አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፤
ክብሬና ራሴን ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።
4በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤
ከተቀደሰ ተራራውም ሰማኝ።
5እኔ ተኛሁ፤ አንቀላፋሁም፤
እግዚአብሔርም አንሥቶኛልና ተነሣሁ።
6ከሚከብቡኝና በእኔ ላይ ከሚነሡ#“በእኔ ላይ ከሚነሡ” የሚለው በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ከአእላፍ አሕዛብ አልፈራም።
7ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤
አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥
የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና።
8ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥
በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 3: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መዝሙረ ዳዊት 3
3
የዳዊት መዝሙር፥ ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ።
1አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ!
በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
2ብዙ ሰዎች ነፍሴን አልዋት፦
“አምላክሽ አያድንሽም።”
3አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፤
ክብሬና ራሴን ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።
4በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤
ከተቀደሰ ተራራውም ሰማኝ።
5እኔ ተኛሁ፤ አንቀላፋሁም፤
እግዚአብሔርም አንሥቶኛልና ተነሣሁ።
6ከሚከብቡኝና በእኔ ላይ ከሚነሡ#“በእኔ ላይ ከሚነሡ” የሚለው በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ከአእላፍ አሕዛብ አልፈራም።
7ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤
አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥
የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና።
8ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥
በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in