መዝሙረ ዳዊት 4
4
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔርን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጽድቄን አምላክ” ይላል። በጠራሁት ጊዜ ጽድቄን ሰማኝ፥
ከጭንቀቴም አሰፋልኝ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በጭንቀቴ አሰፋህልኝ” ይላል።
ይቅር አለኝ፥ ጸሎቴንም ሰማኝ።#ዕብ. 2ኛ መደብ።
2እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ
ልባችሁን ታከብዳላችሁ?
ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?
3እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ ዕወቁ፤
እግዚአብሔር ወደ እርሱ በጮኽሁ ጊዜ ይሰማኛል።
4ተቈጡ፥ ነገር ግን አትበድሉ፤
በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ።
5የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በእግዚአብሔርም ታመኑ።
6“በጎውን ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው።
አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።
7በልባችን ደስታን ጨመርህ፤
ከስንዴ ፍሬና ከወይን፥ ከዘይትም ይልቅ በዛ።
8በእርሱ በሰላም እተኛለሁ፥ አንቀላፋለሁም፤
አቤቱ፥አንተ ብቻህን በተስፋ አሳድረኸኛልና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 4: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መዝሙረ ዳዊት 4
4
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔርን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጽድቄን አምላክ” ይላል። በጠራሁት ጊዜ ጽድቄን ሰማኝ፥
ከጭንቀቴም አሰፋልኝ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በጭንቀቴ አሰፋህልኝ” ይላል።
ይቅር አለኝ፥ ጸሎቴንም ሰማኝ።#ዕብ. 2ኛ መደብ።
2እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ
ልባችሁን ታከብዳላችሁ?
ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?
3እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ ዕወቁ፤
እግዚአብሔር ወደ እርሱ በጮኽሁ ጊዜ ይሰማኛል።
4ተቈጡ፥ ነገር ግን አትበድሉ፤
በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ።
5የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በእግዚአብሔርም ታመኑ።
6“በጎውን ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው።
አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።
7በልባችን ደስታን ጨመርህ፤
ከስንዴ ፍሬና ከወይን፥ ከዘይትም ይልቅ በዛ።
8በእርሱ በሰላም እተኛለሁ፥ አንቀላፋለሁም፤
አቤቱ፥አንተ ብቻህን በተስፋ አሳድረኸኛልና።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in