መዝሙረ ዳዊት 32
32
የዳዊት መዝሙር።
1ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤
ለቅኖችም ክብር ይገባል።
2እግዚአብሔርንም በመሰንቆ አመስግኑት፥
ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።
3አዲስ ምስጋናንም አመስግኑት፥
በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩለት፤
4የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነውና
ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።
5እግዚአብሔር ጽድቅንና#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍርድን” ይላል። ምጽዋትን ይወድዳል፤
የእግዚአብሔር ይቅርታው ምድርን ሞላ።
6በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥
ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤
7የባሕሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው፥
በቀላዮችም መዝገቦች የሚያኖረው።
8ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፈራዋለች፥
በዓለም የሚኖሩ ሁሉም ከእርሱ የተነሣ ይደነግጣሉ።
9እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑ፤
እርሱ አዘዘ፤ ተፈጠሩም።
10እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል፥
የሕዝቡንም ዐሳብ ይመልሳል።
የአለቆችን ምክራቸውን ያስረሳቸዋል።
11የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥
የልቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
12እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ብፁዕ ነው፥
እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።
13እግዚአብሔር ከሰማይ ተመለከተ፥
የሰውንም ልጆች ሁሉ አየ።
14ከተዘጋጀው የመቅደሱ አዳራሽ ሆኖ
በምድር ወደሚኖሩ ሁሉ ተመለከተ፤
15እርሱ ብቻውን ልባቸውን የሠራ፥
ሥራቸውንም ሁሉ የሚያውቅ እርሱ ነው።
16ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥
ኀያልም በኀይሉ ብዛት አይድንም።
17ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፤
በኀይሉም ብዛት አያመልጥም።
18እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፤
በምሕረቱም ወደሚታመኑ፥
19ነፍሳቸውን ከሞት ያድናታል፥
በራብም ጊዜ ይመግባቸዋል።
20ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥
ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና።
21ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥
በቅዱስ ስሙም ታምነናልና።
22አቤቱ፥ በአንተ እንደ ታመንን፥
ምሕረትህ በላያችን ትሁን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 32: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in