መዝሙረ ዳዊት 6
6
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ ስምንተኛ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥
በመቅሠፍትህም አትገሥጸኝ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመዓትህ” ይላል።
2ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤
አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።
3ነፍሴም እጅግ ታወከች፤
አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?
4አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥
ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
5በሞት የሚያስብህ የለምና፥
በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
6በጭንቀቴ ደክሜአለሁ፤
ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥
በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።
7ዐይኔ ከቍጣ የተነሣ ታወከች፤
ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ አረጀሁ።
8ዐመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥
እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።
9እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤
እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።
10ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ፥ ይጐስቁሉም፤
ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ በፍጥነትም እጅግ ይፈሩ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 6: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in