YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ሮሜ ሰዎች 11

11
ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት
1 # ፊል. 3፥5። እን​ግ​ዲህ እላ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጣላ​ቸ​ውን? አይ​ደ​ለም፤ እኔ ደግሞ ከአ​ብ​ር​ሃም ዘር ከብ​ን​ያም ወገን የሆ​ንሁ እስ​ራ​ኤ​ላዊ ነኝ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ውን ሕዝ​ቡን አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያስ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በከ​ሰ​ሳ​ቸው ጊዜ መጽ​ሐፍ ያለ​ውን አታ​ው​ቁ​ምን? 3#1ነገ. 19፥10፤ 14። “አቤቱ፥ ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፈ​ረሱ፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀረሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም ይሿ​ታል።” 4#1ነገ. 19፥18። የተ​ገ​ለ​ጠ​ለ​ትስ ምን አለው? “ለጣ​ዖት ያል​ሰ​ገዱ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስ​ቀ​ር​ቻ​ለሁ።” 5እን​ዲ​ሁም ዛሬ በዚህ ዘመን በጸጋ የተ​መ​ረ​ጡና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመኑ#“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመኑ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ቅሬ​ታ​ዎች አሉ። 6በጸጋ ከጸ​ደቁ ግን በሥ​ራ​ቸው አይ​ደ​ለማ፤ በሥ​ራም የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ ጸጋ ጸጋ አይ​ባ​ልም።
7እን​ግ​ዲህ ምን​ድን ነው? እስ​ራ​ኤል የፈ​ለ​ገ​ውን አላ​ገ​ኘም። የተ​መ​ረ​ጠው ግን አግ​ኝ​ቶ​አል፤ የቀ​ሩ​ትም ታወሩ። 8#ዘዳ. 29፥4፤ ኢሳ. 29፥10። መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደን​ዛዛ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።” 9ዳዊ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ወጥ​መ​ድና አሽ​ክላ፥ መሰ​ና​ከ​ያና ፍዳም ትሁ​ን​ባ​ቸው። 10#መዝ. 68፥22-23። እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ይጨ​ልሙ፤ ዘወ​ት​ርም ጀር​ባ​ቸው ይጕ​በጥ።” 11እን​ግ​ዲህ እላ​ለሁ፤ ሊወ​ድቁ ተሰ​ና​ከ​ሉን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል ይቀኑ ዘንድ እነ​ርሱ በመ​ሰ​ና​ከ​ላ​ቸው ለአ​ሕ​ዛብ ድኅ​ነት ሆነ። 12የእ​ነ​ርሱ መሰ​ና​ከል ለዓ​ለም ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በደ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ባለ​ጸ​ግ​ነት ከሆነ ፍጹ​ም​ነ​ታ​ቸ​ውማ እን​ዴት በሆነ ነበር?
ስለ አሕ​ዛብ መዳን
13ለእ​ና​ንተ ለአ​ሕ​ዛብ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እኔ ለአ​ሕ​ዛብ ሐዋ​ር​ያ​ቸው እንደ መሆኔ መጠን መል​እ​ክ​ቴን አከ​ብ​ራ​ታ​ለሁ። 14ይህም በዚህ ዘመ​ዶ​ችን አስ​ቀ​ና​ቸው እንደ ሆነ፥ ከእ​ነ​ርሱ ወገን የሆ​ኑ​ት​ንም አድን እንደ ሆነ ነው። 15የእ​ነ​ርሱ መው​ጣት ለዓ​ለም ዕርቅ ከሆነ ይል​ቁ​ንም መመ​ለ​ሳ​ቸው ምን ይሆን? ከሙ​ታን በመ​ነ​ሣት የሚ​ገኝ ሕይ​ወት ነው። 16እር​ሾው ቅዱስ ከሆነ ቡሆ​ውም እን​ዲሁ ቅዱስ ነው፤ ሥርዋ ቅዱስ ከሆ​ነም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ እን​ዲሁ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናሉ። 17ከቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ አን​ዳ​ን​ዶቹ ቢሰ​በሩ የዱር ወይራ የሆ​ንህ አን​ተን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ተከሉ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም ሥር​ነት አገ​ኘህ፤ እንደ እነ​ር​ሱም ዘይት ሆንኽ። 18በቅ​ር​ን​ጫ​ፎች ላይ አት​ኵራ፤ ብት​ኰራ ግን ሥሩ አን​ተን ይሸ​ከ​ም​ሃል እንጂ አንተ ሥሩን የም​ት​ሸ​ከ​መው አይ​ደ​ለም። 19ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ተሰ​በሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ “እኔ የዘ​ይት ቅር​ን​ጫፍ ሆንሁ” ትል ይሆ​ናል። 20አላ​መ​ኑ​ምና ተሰ​በሩ፤ አንተ ግን ስለ አመ​ንህ ቆመ​ሃል፤ እን​ግ​ዲህ ፈር​ተህ ኑር እንጂ ራስ​ህን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርግ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ፈ​ጥ​ሮ​አ​ቸው ቅር​ን​ጫ​ፎች ለነ​በሩ ለእ​ነ​ዚያ ከአ​ል​ራ​ራ​ላ​ቸው ለአ​ን​ተም አይ​ራ​ራ​ል​ህም፤ 22እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርኅ​ራ​ኄ​ው​ንና ጭካ​ኔ​ውን አስ​ተ​ውል፤ የወ​ደ​ቁ​ትን ቀጣ​ቸው፤ አን​ተን ግን ይቅር እን​ዳ​ለህ ብት​ኖር ማረህ፤ ያለ​ዚያ ግን አን​ተም ትቈ​ረ​ጣ​ለህ። 23እነ​ር​ሱም ባለ​ማ​መ​ና​ቸው ጸን​ተው ባይ​ኖሩ ይተ​ከ​ላሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳግ​መና ሊተ​ክ​ላ​ቸው ይች​ላ​ልና። 24አንተ የዱር ወይራ፥ አን​ተን ስንኳ ከበ​ቀ​ል​ህ​በት ቈርጦ ባል​በ​ቀ​ል​ህ​በት በመ​ል​ካሙ ዘይት ስፍራ ከተ​ከ​ለህ፥ ይል​ቁን ጥን​ቱን ዘይት የነ​በ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ያን በበ​ቀ​ሉ​በት ስፍራ እን​ዴት አብ​ልጦ ሊተ​ክ​ላ​ቸው አይ​ች​ልም?
ስለ እስ​ራ​ኤል መመ​ለስ
25ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና። 26#ኢሳ. 59፥20። ከዚህ በኋ​ላም መላው እስ​ራ​ኤል ይድ​ናሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፥ “አዳኝ ከጽ​ዮን ይወ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያስ​ወ​ግ​ዳል። 27#ኤር. 31፥33-34። ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ባራ​ቅ​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የም​ገ​ባው ኪዳን ይህ ነው።” 28በወ​ን​ጌል በኩል ስለ እና​ንተ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ናቸው፤ በም​ርጫ በኩል ግን ስለ አባ​ቶች ወዳ​ጆች ናቸው። 29በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋና በመ​ጥ​ራቱ ጸጸት የለ​ምና። 30ቀድሞ እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ አል​ታ​ዘ​ዛ​ች​ሁት፥ ዛሬ ግን በእ​ነ​ርሱ አለ​መ​ታ​ዘዝ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ፥ 31እን​ዲ​ሁም እና​ንተ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ምሕ​ረት እነ​ርሱ ምሕ​ረ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ እነ​ርሱ ዛሬ አል​ታ​ዘ​ዙ​ትም። 32እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ይቅር ይለው ዘንድ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ውስጥ ዘግ​ቶ​ታ​ልና። 33#ኢሳ. 55፥8። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም። 34#ኢሳ. 40፥13። “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐሳ​ቡን ማን ያው​ቃል? ወይስ ማን ተማ​ከ​ረው? 35#ኢዮብ 41፥11። ብድ​ሩን ይከ​ፍል ዘንድ ለእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ማን አበ​ደ​ረው?” 36#1ቆሮ. 8፥6። ሁሉ ከእ​ርሱ፥ በእ​ር​ሱና ለእ​ርሱ ነውና፤ ለእ​ር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክብር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in