YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ሮሜ ሰዎች 12

12
በክ​ር​ስ​ቶስ ሐዲስ ሕይ​ወት
1ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ውና ቅዱስ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ርቡ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርኅ​ራኄ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ይህም በዕ​ው​ቀት የሚ​ሆን አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ችሁ ነው። 2ይህን ዓለም አት​ም​ሰሉ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም አድሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን መል​ካ​ሙ​ንና እው​ነ​ቱን፥ ፍጹ​ሙ​ንም መር​ምሩ።
3በተ​ሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ሁላ​ች​ሁም እን​ዳ​ት​ታ​በዩ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ራሳ​ች​ሁን ከዝ​ሙት የም​ታ​ነ​ጹ​በ​ትን ዐስቡ እንጂ#“ራሳ​ች​ሁን ከዝ​ሙት የም​ት​ነ​ጹ​በ​ትን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ትዕ​ቢ​ትን አታ​ስቡ፤ ሁሉም እንደ እም​ነቱ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ይኑር። 4በአ​ንዱ ሰው​ነ​ታ​ችን ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎች እን​ዳሉ፥ ሥራ​ቸ​ውም ልዩ ልዩ እንደ ሆነ፥ 5#1ቆሮ. 12፥12። እን​ዲሁ ሁላ​ችን ብዙ​ዎች ስን​ሆን በክ​ር​ስ​ቶስ አንድ አካል ነን፤ እርስ በር​ሳ​ች​ንም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን የሌ​ላው አካ​ሎች ነን፤#“እርስ በር​ሳ​ች​ንም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን የሌ​ላው አካ​ሎች ነን” የሚ​ለው በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ስጦ​ታ​ውም ልዩ ልዩ ነው፤ 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠን ጸጋ መጠን ልዩ ልዩ ስጦታ አለን። ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እንደ እም​ነቱ መጠን ይና​ገር። 7የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ልም በማ​ገ​ል​ገሉ ይትጋ፤ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ርም በማ​ስ​ተ​ማሩ ይትጋ፤ 8#1ቆሮ. 12፥4-11። የሚ​መ​ክ​ርም በመ​ም​ከሩ ይትጋ፤ የሚ​ሰ​ጥም በል​ግ​ስና ይስጥ፤ የሚ​ገ​ዛም በት​ጋት ይግዛ፤ የሚ​መ​ጸ​ው​ትም በደ​ስታ ይመ​ጽ​ውት።
ስለ ልዩ ልዩ በጎ ምግ​ባር
9ፍቅ​ራ​ችሁ ያለ ግብ​ዝ​ነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎ​ው​ንም ያዙ፤ ለጽ​ድቅ አድሉ፤#“ለጽ​ድቅ አድሉ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 10እርስ በር​ሳ​ችሁ በወ​ን​ድ​ማ​ማ​ች​ነት መዋ​ደድ ተዋ​ደዱ፤ የም​ት​ራ​ሩም ሁኑ፤#“የም​ት​ራ​ሩም ሁኑ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። እርስ በር​ሳ​ችሁ ተከ​ባ​በሩ፤ መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም አክ​ብሩ።#“መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም አክ​ብሩ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 11ለሥራ ከመ​ት​ጋት አት​ስ​ነፉ፤ በመ​ን​ፈስ ሕያ​ዋን ሁኑ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፤ 12በተ​ስፋ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከራ ታገሡ፤ ለጸ​ሎት ትጉ። 13በች​ግ​ራ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ተባ​በሩ፤ እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አዘ​ው​ትሩ።
14 # ማቴ. 5፥44፤ ሉቃ. 6፥28። የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አት​ር​ገሙ። 15ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ። 16#ምሳ. 3፥7። እርስ በር​ሳ​ች​ሁም በአ​ንድ ዐሳብ ተስ​ማሙ፤ ትዕ​ቢ​ትን ግን አታ​ስቡ፤ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ው​ንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋ​ቆች ነን አት​በሉ። 17ክፉ ላደ​ረ​ገ​ባ​ች​ሁም ክፉ አት​መ​ል​ሱ​ለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ​ውን ተነ​ጋ​ገሩ። 18ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰ​ላም ኑሩ። 19#ዘዳ. 32፥35። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ራሳ​ችሁ አት​በ​ቀሉ፤ ቍጣን አሳ​ል​ፏት፥ “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔ ብድ​ራ​ትን እከ​ፍ​ላ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና። 20ጠላ​ትህ ቢራብ አብ​ላው፤ ቢጠ​ማም አጠ​ጣው፤ ይህን ብታ​ደ​ርግ የእ​ሳት ፍሕም በራሱ ላይ ትከ​ም​ራ​ለህ። 21ክፉ​ውን በመ​ል​ካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉ​ውን በክፉ ድል አት​ን​ሣው።#ግሪኩ “በክፉ አት​ሸ​ነፍ” ይላል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in