ኦሪት ዘኊልቊ 33
33
1የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን ልጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ። 2ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ፤ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ። 3በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ። 4በዚያም ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው። 5የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተጕዘው በሱኮት ሰፈሩ። 6ከሱኮትም ተጕዘው በምድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤታም ሰፈሩ። 7ከኤታምም ተጕዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። 8ከፊሀሒሮትም ተጕዘው በባሕሩ ውስጥ ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ። 9ከማራም ተጕዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም አሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ። 10ከኤሊምም ተጕዘው በኤርትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ። 11ከኤርትራም ባሕር ተጕዘው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። 12ከሲን ምድረ በዳም ተጕዘው በራፋቃ ሰፈሩ። 13ከራፋቃም ተጕዘው በኤሉስ ሰፈሩ። 14ከኤሉስም ተጕዘው በራፊዲም ሰፈሩ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። 15ከራፊዲምም ተጕዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። 16ከሲናም ምድረ በዳ ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ። 17ከምኞት መቃብርም ተጕዘው በሐጼሮት ሰፈሩ። 18ከሐጼሮትም ተጕዘው በሪትማ ሰፈሩ። 19ከሪትማም ተጕዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ። 20ከሬሞን ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ። 21ከልብናም ተጕዘው በሪሳ ሰፈሩ። 22ከሪሳም ተጕዘው በቀሄላታ ሰፈሩ። 23ከቀሄላታም ተጕዘው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ። 24ከሻፍር ተራራም ተጕዘው በሐራዳ ሰፈሩ። 25ከሐራዳም ተጕዘው በመቅሄሎት ሰፈሩ። 26ከመቅሄሎትም ተጕዘው በታሐት ሰፈሩ። 27ከታሐትም ተጕዘው በታራ ሰፈሩ። 28ከታራም ተጕዘው በሚትቃ ሰፈሩ። 29ከሚትቃም ተጕዘው በሐሽሞና ሰፈሩ። 30ከሐሽሞናም ተጕዘው በሞሴሮት ሰፈሩ። 31ከሞሴሮትም ተጕዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። 32ከብኔያዕቃንም ተጕዘው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ። 33ከሆርሃጊድጋድም ተጕዘው በዮጥባታ ሰፈሩ። 34ከዮጥባታም ተጕዘው በዔብሮና ሰፈሩ። 35ከዔብሮናም ተጕዘው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። 36ከዔጽዮንጋብርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት። 37ከቃዴስም ተጕዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። 38ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። 39አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር። 40በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ። 41እነርሱም ከሖር ተራራ ተጕዘው በሴልሞና ሰፈሩ። 42ከሴልሞናም ተጕዘው በፉኖን ሰፈሩ። 43ከፋኖንም ተጕዘው በአቦት ሰፈሩ። 44ከአቦትም ተጕዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ። 45ከጋይም ተጕዘው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። 46ከዲቦንጋድም ተጕዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። 47ከዓልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። 48ከዓብሪምም ተራሮች ተጕዘው በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ። 49በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ። 50እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 51ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ 52የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ 53ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም። 54ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። 55የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል። 56እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 33: አማ54
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in