1
ሐዋርያት ሥራ 1:8
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
Compara
Explorar ሐዋርያት ሥራ 1:8
2
ሐዋርያት ሥራ 1:7
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜ ወይም ወቅት ማወቁ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤
Explorar ሐዋርያት ሥራ 1:7
3
ሐዋርያት ሥራ 1:4-5
ከእነርሱም ጋር በማእድ ተቀምጦ ሳለ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “ከኢየሩሳሌም አትውጡ፤ ነገር ግን እኔ ስናገር የሰማችሁትን፣ አብ የሰጠውን ተስፋ ጠብቁ፤ ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና፣ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።”
Explorar ሐዋርያት ሥራ 1:4-5
4
ሐዋርያት ሥራ 1:3
ከሕማማቱም በኋላ ራሱ ቀርቦ ሕያው መሆኑን፣ ለእነዚሁ በብዙ ማስረጃ እያረጋገጠላቸው አርባ ቀንም ዐልፎ ዐልፎ እየታያቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገራቸው።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 1:3
5
ሐዋርያት ሥራ 1:9
ይህን ካለ በኋላ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረችው።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 1:9
6
ሐዋርያት ሥራ 1:10-11
እርሱም በሚሄድበት ጊዜ ትኵር ብለው ወደ ሰማይ ሲመለከቱ፣ እነሆ፤ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ፤ እንዲህም አሏቸው፤ “እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል።”
Explorar ሐዋርያት ሥራ 1:10-11
Inici
La Bíblia
Plans
Vídeos