1
ሐዋርያት ሥራ 2:38
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኀጢአታችሁም እንዲሰረይላችሁ፣ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
Compara
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:38
2
ሐዋርያት ሥራ 2:42
እነርሱም በሐዋርያት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውንም በመቍረስና በጸሎት ይተጉ ነበር።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:42
3
ሐዋርያት ሥራ 2:4
ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስም እንዲናገሩ በሰጣቸው መጠን በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:4
4
ሐዋርያት ሥራ 2:2-4
ድንገትም እንደ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጥቶ ተቀምጠው የነበሩበትን ቤት እንዳለ ሞላው። የእሳት ምላሶች የሚመስሉም ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ ዐረፉ። ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስም እንዲናገሩ በሰጣቸው መጠን በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:2-4
5
ሐዋርያት ሥራ 2:46-47
በየዕለቱ በቤተ መቅደስ በአንድነት እየተገናኙ፣ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በቀና ልብ ይመገቡ ነበር፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው፤ ጌታም የሚድኑትን በቍጥራቸው ላይ ዕለት በዕለት ይጨምር ነበር።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:46-47
6
ሐዋርያት ሥራ 2:17
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመጨረሻው ቀን፣ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ጕልማሶቻችሁ ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:17
7
ሐዋርያት ሥራ 2:44-45
ያመኑት ሁሉ በአንድነት ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ የጋራ አደረጉ። ሀብታቸውንና ንብረታቸውንም እየሸጡ ለእያንዳንዱ ሰው የሚያስፈልገውን ያህል ይሰጡት ነበር።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:44-45
8
ሐዋርያት ሥራ 2:21
የጌታን ስም፣ የሚጠራ ሁሉ ይድናል።’
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:21
9
ሐዋርያት ሥራ 2:20
ታላቅና ክቡር የሆነው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።
Explorar ሐዋርያት ሥራ 2:20
Inici
La Bíblia
Plans
Vídeos