የሉ​ቃስ ወን​ጌል 14

14
ሆዱ የተ​ነ​ፋ​ውን ሰው እንደ ፈወሰ
1ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር። 2እነ​ሆም፥ ሆዱ የተ​ነፋ አንድ ሰው በፊቱ ነበር። 3ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ ሕግ ዐዋ​ቂ​ዎ​ች​ንና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ “በሰ​ን​በት ድውይ መፈ​ወስ ይገ​ባ​ልን? ወይስ አይ​ገ​ባም?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው። 4እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ይዞም ፈወ​ሰ​ውና ሰደ​ደው። 5#ማቴ. 12፥11። “ከእ​ና​ንተ በሬው ወይም አህ​ያው በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ የወ​ደ​ቀ​በት አንድ ሰው ቢኖር ዕለ​ቱን በሰ​ን​በት ቀን ያነ​ሣው የለ​ምን?” አላ​ቸው። 6ስለ​ዚ​ህም ነገር ሊመ​ል​ሱ​ለት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም።
በራ​ስጌ መቀ​መ​ጥን ስለ​ሚ​ወዱ ሰዎች
7በምሳ ላይ ለነ​በ​ሩ​ትም ወደ ላይ​ኛው ወን​በር ሲሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ባያ​ቸው ጊዜ ምሳሌ መስሎ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው። 8እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለምሳ#በግ​ሪኩ “ለሰ​ርግ” ይላል። የጠ​ራህ ሰው ቢኖ​ርና ብት​ሄድ በላ​ይ​ኛው መቀ​መጫ አት​ቀ​መጥ፤ ምና​ል​ባት ከአ​ንተ የሚ​በ​ልጥ ይመጣ ይሆ​ናል። 9በኋላ ያ አን​ተ​ንም እር​ሱ​ንም የጠራ መጥቶ፦ ይህን ቦታ ለእ​ርሱ ተው​ለት ይል​ሃ​ልና፤ ያን​ጊ​ዜም አፍ​ረህ ትመ​ለ​ሳ​ለህ፤ ወደ ዝቅ​ተኛ ቦታም ትወ​ር​ዳ​ለህ። 10የጠ​ራህ ሰው ቢኖ​ርና ብት​ሄድ ግን የጠ​ራህ በመጣ ጊዜ ወዳጄ ወደ ላይ​ኛው መቀ​መጫ ውጣ ይልህ ዘንድ በታ​ች​ኛው መቀ​መጫ ተቀ​መጥ፤ ያን​ጊ​ዜም ከአ​ንተ ጋር ለማ​ዕድ በተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ፊት ክብር ይሆ​ን​ል​ሃል። 11#ማቴ. 23፥12፤ ሉቃ. 18፥14። ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”
12የጠ​ራ​ው​ንም እን​ዲህ አለው፥ “በበ​ዓል ምሳ ወይም ራት በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ወዳ​ጆ​ች​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፥ ዘመ​ዶ​ች​ህ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ህን፥ ባለ​ጸ​ጎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ጥራ፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሩ​ሃ​ልና፤ ብድ​ርም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና። 13ነገር ግን በበ​ዓል ምሳ በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ችን፥ እጅና እግ​ርም የሌ​ላ​ቸ​ውን ጥራ። 14አን​ተም ብፁዕ ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ከ​ፍ​ሉህ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን ጻድ​ቃን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ዋጋ​ህን ታገ​ኛ​ለህ።” 15ለምሳ ከተ​ቀ​መ​ጡ​ትም አንዱ ይህን ሰምቶ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እህል የሚ​በላ ብፁዕ ነው” አለው።
ለምሳ ስለ መጠ​ራት
16ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አንድ ሰው ታላቅ ምሳ#በግ​ሪኩ “ራት” ይላል። አደ​ረ​ገና ብዙ ሰዎ​ችን ጠራ። 17ለምሳ የተ​ጠ​ሩ​በ​ትም ቀን በደ​ረሰ ጊዜ የታ​ደ​ሙ​ትን ይጠ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱም ሄዶ የታ​ደ​ሙ​ትን፦ አሁን ምሳ​ውን ፈጽ​መን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ና​ልና ኑ አላ​ቸው። 18ሁሉም በአ​ንድ ቃል ተባ​ብ​ረው እንቢ አሉ፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው፦ እርሻ ገዝ​ች​አ​ለሁ፤ ሄጄም ላያት እሻ​ለሁ፤ እንቢ እንደ አላ​ልሁ ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው። 19ሁለ​ተ​ኛ​ውም፦ አም​ስት ጥማድ በሬ ገዝ​ቻ​ለሁ፤ ላያ​ቸ​ውና ልፈ​ት​ና​ቸው እሄ​ዳ​ለሁ፤ እንደ መጣሁ፥ እንቢ እንደ አላ​ል​ሁም ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው። 20ሦስ​ተ​ኛ​ውም፦ ሚስት አግ​ብ​ች​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ልመጣ አል​ች​ልም በለው አለው። 21አገ​ል​ጋ​ዩም ተመ​ልሶ ለጌ​ታው ይህ​ንኑ ነገ​ረው፤ ያን​ጊ​ዜም ባለ​ቤቱ ተቈጣ፤ አገ​ል​ጋ​ዩ​ንም፦ ፈጥ​ነህ ወደ አደ​ባ​ባ​ይና ወደ ከተ​ማው ጐዳና ሂድ፤ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ች​ንና አን​ካ​ሶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጣ​ልኝ አለው። 22ከዚ​ህም በኋላ አገ​ል​ጋዩ፦ አቤቱ እንደ አዘ​ዝ​ኸኝ አደ​ረ​ግሁ፤ ገናም ቦታ አለ አለው። 23ጌታ​ውም አገ​ል​ጋ​ዩን፦ ወደ መን​ገ​ዶ​ችና ወደ ከተ​ማው ቅጥር ፈጥ​ነህ ሂድና ቤቴ እን​ዲ​መላ ይገቡ ዘንድ ግድ በላ​ቸው አለው። 24ከእ​ነ​ዚህ ከታ​ደ​ሙት ሰዎች አንዱ ስን​ኳን ማዕ​ዴን#በግ​ሪ​ኩና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ራቴን” ይላል። እን​ደ​ማ​ይ​ቀ​ም​ሳት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።”
ጌታን ስለ መከ​ተል
25ከዚ​ህም በኋላ ብዙ ሰዎች አብ​ረ​ውት ሲሄዱ መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው። 26#ማቴ. 10፥37። “ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ሊከ​ተ​ለ​ኝም የሚ​ወድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን፥ ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና እኅ​ቶ​ቹን፥ የራ​ሱ​ንም ሰው​ነት እንኳ ቢሆን የማ​ይ​ጠላ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም። 27#ማቴ. 10፥38፤ 16፥24፤ ማር. 8፥34፤ ሉቃ. 9፥23። መስ​ቀ​ሉን ተሸ​ክሞ ሊከ​ተ​ለኝ የማ​ይ​መጣ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።”
ቤት ስለ​ሚ​ሠ​ራው ሰው ምሳሌ
28“ከእ​ና​ን​ተም ወገን የግ​ንብ ቤት መሥ​ራት የሚ​ወድ ቢኖር ይጨ​ር​ሰው ዘንድ የሚ​ችል እንደ ሆነ አስ​ቀ​ድሞ ተቀ​ምጦ የሚ​ፈ​ጅ​በ​ትን የማ​ያ​ስብ ማን ነው? 29መሠ​ረ​ቱን ጥሎ መጨ​ረስ ያቃ​ተ​ውም እንደ ሆነ ያዩት ሁሉ፥ 30‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀመረ፤ ግን መጨ​ረስ ተሳ​ነው’ እያሉ ሊዘ​ብ​ቱ​በት ይጀ​ም​ራሉ። 31ንጉ​ሥም ሌላ​ውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ሊሄድ ቢወድ ሁለት እልፍ ይዞ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ውን በአ​ንድ እልፍ ሊዋ​ጋው ይችል እንደ ሆነ አስ​ቀ​ድሞ ተቀ​ምጦ ይመ​ክር የለ​ምን? 32ያለ​ዚያ ግን፥ ገና በሩቁ ሳለ አማ​ላ​ጆች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ ዕርቅ ይለ​ም​ናል። 33እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ዚሁ ከእ​ና​ንተ ወገን ከሁሉ ያል​ወጣ፥ የእ​ርሱ ገን​ዘብ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያል​ተ​ለየ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።
34“ጨው መል​ካም ነው፤ ጨው አልጫ ከሆነ እን​ግ​ዲህ በምን ያጣ​ፍ​ጡ​ታል? 35ለም​ድ​ርም ቢሆን፥ ለፍግ መቆ​ለ​ያም ቢሆን አይ​ረ​ባም፤ ነገር ግን ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”

Subratllat

Comparteix

Copia

None

Vols que els teus subratllats es desin a tots els teus dispositius? Registra't o inicia sessió