የሉ​ቃስ ወን​ጌል 19

19
ስለ ቀራጩ ዘኬ​ዎስ
1ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ኢያ​ሪኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር። 2እነሆ፥ የቀ​ራ​ጮች አለቃ ስሙ ዘኬ​ዎስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ባለ​ጸጋ ነበር። 3ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ያየው ዘንድ፥ ማን እንደ ሆነም ያውቅ ዘንድ ይሻ ነበር፤ የሰው ብዛ​ትም ይከ​ለ​ክ​ለው ነበር፤ ቁመቱ አጭር ነበ​ርና። 4ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘን​ድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያች መን​ገድ ያልፍ ዘንድ አለ​ውና። 5ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ​ዚያ በደ​ረሰ ጊዜ አሻ​ቅቦ አየ​ውና፥ “ዘኬ​ዎስ ሆይ፥ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ዛሬ በቤ​ትህ እውል ዘንድ አለ​ኝና” አለው። 6ፈጥ​ኖም ወረደ፤ ደስ እያ​ለ​ውም ወደ ቤቱ ይዞት ገባ። 7ሁሉም አይ​ተው “ወደ ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው ቤት ሊውል ገባ” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ። 8ዘኬ​ዎ​ስም ቆመና ጌታ​ች​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገ​ን​ዘ​ቤን እኩ​ሌታ ለነ​ዳ​ያን እሰ​ጣ​ለሁ፤ የበ​ደ​ል​ሁ​ትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ።” 9ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ዛሬ ለዚህ ቤት ሕይ​ወት ሆነ፤ እርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ ነውና። 10#ማቴ. 18፥11። የሰው ልጅ የጠ​ፋ​ውን ሊፈ​ል​ግና ሊያ​ድን መጥ​ቶ​አ​ልና።”
ዐሥር ምናን ስለ ተቀ​በ​ሉት ሰዎች ምሳሌ
11 # ማቴ. 25፥14-30። ይህ​ንም ሲሰሙ፤ ምሳሌ መስሎ ነገ​ራ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቦ ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወዲ​ያ​ውኑ የም​ት​ገ​ለጥ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። 12እን​ዲ​ህም አለ፥ “አንድ የከ​በረ ሰው መን​ግ​ሥት ይዞ ሊመ​ለስ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ። 13ዐሥ​ሩን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣ​ቸ​ውና፦ እን​ግ​ዲህ እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ነግዱ አላ​ቸው። 14የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ። 15ከዚ​ህም በኋላ፤ መን​ግ​ሥ​ትን ይዞ በተ​መ​ለሰ ጊዜ እንደ አተ​ረፉ ያውቅ ዘንድ ምናን የሰ​ጣ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ቹን እን​ዲ​ያ​መ​ጡ​አ​ቸው አዘዘ። 16አን​ደ​ኛ​ውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምና​ንህ ዐሥር ነበር፤ እነሆ ዐሥር ምናን አት​ር​ፌ​አ​ለሁ አለው። 17ጌታ​ውም፦ መል​ካም፥ አንተ በጎ አገ​ል​ጋይ በጥ​ቂት የታ​መ​ንህ ስለ​ሆ​ንህ በብዙ ላይ እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤#“በብዙ ላይ እሾ​ም​ሃ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። በዐ​ሥሩ ከተ​ሞች ላይ ተሾም አለው። 18ሁለ​ተ​ኛ​ውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምና​ንህ አም​ስት ነበር፤#“ምና​ንህ አም​ስት ነበር” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አም​ስት አት​ር​ፌ​አ​ለሁ አለው። 19እር​ሱ​ንም፦ አን​ተም በአ​ም​ስት ከተ​ሞች ተሾም አለው። 20ሦስ​ተ​ኛ​ውም መጥቶ እን​ዲህ አለው፦ አቤቱ፥ በእኔ ዘንድ የነ​በ​ረ​ቺው ምና​ንህ እነ​ኋት፤ በጨ​ርቅ ጠቅ​ልዬ አኑ​ሬ​አት ነበር። 21አንተ ያላ​ኖ​ር​ኸ​ውን የም​ት​ወ​ስድ፥ ያል​ዘ​ራ​ኸ​ውን የም​ታ​ጭድ፥ ያል​በ​ተ​ን​ኸ​ው​ንም የም​ት​ሰ​በ​ስብ#“ያል​በ​ተ​ን​ኸ​ውን የም​ት​ሰ​በ​ስብ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ ስለ​ማ​ው​ቅህ ፈር​ቼ​ሃ​ለ​ሁና። 22ጌታ​ውም እን​ዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገ​ል​ጋይ፥ እኔ ያላ​ስ​ቀ​መ​ጥ​ሁ​ትን የም​ወ​ስድ፥ ያል​ዘ​ራ​ሁ​ትን የማ​ጭድ፥ ያል​በ​ተ​ን​ሁ​ት​ንም የም​ሰ​በ​ስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለ​ህን? እንደ ቃልህ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ። 23ለምን ገን​ዘ​ቤን ወደ ለዋ​ጮች አላ​ስ​ገ​ባ​ህም? እኔም መጥቼ ከት​ርፉ ጋር በወ​ሰ​ድ​ሁት ነበር። 24ከዚያ የቆ​ሙ​ት​ንም፦ ይህን ምናን ከእ​ርሱ ተቀ​ብ​ላ​ችሁ ዐሥር ምናን ላለው ስጡት አላ​ቸው። 25እነ​ር​ሱም አቤቱ፥ ዐሥር ምናን ያለው አይ​ደ​ለ​ምን? አሉት። 26#ማቴ. 13፥12፤ ማር. 4፥25፤ ሉቃ. 8፥18። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ላለው ሁሉ ይሰ​ጡ​ታል፤ ይጨ​ም​ሩ​ለ​ታ​ልም፤ የሌ​ለ​ውን ግን ያን ያለ​ው​ንም ቢሆን ይወ​ስ​ዱ​በ​ታል። 27ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”
ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ መግ​ባቱ
28ይህ​ንም ተና​ግሮ ወደ ፊት ሄደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወጣ። 29ደብረ ዘይት ወደ​ሚ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ወዳ​ሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታ​ንያ በቀ​ረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ላከ። 30እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በፊ​ታ​ችሁ ወደ አለ​ችው መን​ደር ሂዱ፤ ገብ​ታ​ች​ሁም ሰው ያል​ተ​ቀ​መ​ጠ​በት የታ​ሰረ ውር​ንጫ ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ፈት​ታ​ች​ሁም አም​ጡ​ልኝ። 31ለምን ትፈ​ቱ​ታ​ላ​ችሁ? የሚ​ላ​ችሁ ቢኖር ጌታው ይሻ​ዋል በሉ።” 32የተ​ላ​ኩ​ትም ሄደው እንደ አላ​ቸው አገኙ። 33ውር​ን​ጫ​ው​ንም ሲፈቱ ባለ​ቤ​ቶቹ “ውር​ን​ጫ​ውን ለምን ትፈ​ቱ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው። 34እነ​ር​ሱም “ጌታው ይሻ​ዋል” አሉ። 35ይዘ​ውም ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወሰ​ዱት፤ በው​ር​ን​ጫው ላይም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ጭነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በዚያ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት። 36ሲሄ​ዱም በመ​ን​ገድ ልብ​ሳ​ቸ​ውን አነ​ጠፉ። 37ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት መው​ረ​ጃም በደ​ረሱ ጊዜ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በሙሉ ስለ አዩት ኀይል ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በታ​ላቅ ቃል ያመ​ሰ​ግ​ኑት ዘንድ ጀመሩ። 38#መዝ. 117፥26። እን​ዲህ እያሉ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ ቡሩክ ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ቡሩክ ነው፤#“የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ቡሩክ ነው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ሰላም በም​ድር፥ በአ​ር​ያ​ምም ክብር ይሁን።” 39ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በሕ​ዝቡ መካ​ከል፥ “መም​ህር ሆይ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ገሥ​ጻ​ቸው” ያሉት ነበሩ። 40እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነ​ዚህ ዝም ቢሉ እኒህ ድን​ጋ​ዮች ይጮ​ሀሉ።”
ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥ​ፋት
41በደ​ረሰ ጊዜም ከተ​ማ​ዪ​ቱን አይቶ አለ​ቀ​ሰ​ላት። 42እን​ዲ​ህም አላት፥ “አን​ቺስ ብታ​ውቂ ሰላ​ምሽ ዛሬ ነበረ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን ከዐ​ይ​ኖ​ችሽ ተሰ​ወረ። 43ጠላ​ቶ​ችሽ አን​ቺን የሚ​ከ​ቡ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ይከ​ት​ሙ​ብ​ሻል፤ ያስ​ጨ​ን​ቁ​ሻ​ልም፤ በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ንም ከብ​በው ይይ​ዙ​ሻል። 44አን​ቺን ይጥ​ሉ​ሻል፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ጋር ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ድን​ጋ​ይ​ንም በደ​ን​ጋይ ላይ አይ​ተ​ዉ​ል​ሽም፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ሽን ዘመን አላ​ወ​ቅ​ሽ​ምና።”
ጌታ​ችን ገበ​ያ​ተ​ኞ​ቹን ከቤተ መቅ​ደስ ስለ ማስ​ወ​ጣቱ
45ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ገብቶ በዚያ የሚ​ሸ​ጡ​ት​ንና የሚ​ገ​ዙ​ትን ሁሉ አስ​ወጣ፤ የለ​ዋ​ጮ​ች​ንም መደ​ር​ደ​ሪያ፥ የር​ግብ ሻጮ​ች​ንም ወን​በር ገለ​በጠ።#“የለ​ዋ​ጮ​ች​ንም መደ​ር​ደ​ሪያ የር​ግብ ሻጮ​ንም ወን​በር ገለ​በጠ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 46#ኢሳ. 56፥7፤ ኤር. 7፥11። “ቤቴ የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላል የሚል ጽሑፍ አለ፤ እና​ንተ ግን የሌ​ቦ​ችና የቀ​ማ​ኞች ዋሻ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት” አላ​ቸው። 47#ሉቃ. 21፥37። ዘወ​ት​ርም በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና የሕ​ዝብ ታላ​ላ​ቆ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር። 48ነገር ግን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ትም​ህ​ር​ቱን በመ​ስ​ማት ይመ​ሰጡ ነበ​ርና።

Subratllat

Comparteix

Copia

None

Vols que els teus subratllats es desin a tots els teus dispositius? Registra't o inicia sessió