የሉቃስ ወንጌል 20
20
ኢየሱስ በምን ሥልጣን እንደሚሠራ የቀረበለት ጥያቄ
(ማቴ. 21፥23-27፤ ማር. 11፥27-33)
1አንድ ቀንም ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ወንጌልንም ሲሰብክላቸው፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ ቀረቡና 2“እስኪ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን ነው የምታደርገው? ወይንስ ይህን ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ተናገሩት። 3ሲመልስም “እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እስቲ ንገሩኝ፤ 4የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረች ወይስ ከሰዎች?” አላቸው። 5እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ “‘ከሰማይ’ ብንል ‘ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ 6‘ከሰዎች’ ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ በድንጋይ ይወግሩናል፤ ምክንያቱም ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉም ያምኑ ነበርና” አሉ። 7መልሰውም “ከየት እንደሆነ አናውቅም፤” አሉት። 8ኢየሱስም “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ አልነግራችሁም፤” አላቸው።
የወይኑ አትክልት ተከራዮች ምሳሌ
(ማቴ. 21፥33-46፤ ማር. 12፥1-12)
9 #
ኢሳ. 5፥1። ይህንንም ምሳሌ ለሕዝቡ ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ለወይን ጠባቂዎች አከራይቶ ለረጅም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ሄደ። 10ጊዜውም ሲደርስ ከወይኑ አትክልት ፍሬ እንዲሰጡት አንድ አገልጋይ ወደ ተከራዮቹ ላከ፤ ጠባቂዎቹ ግን ደበደቡትና ባዶ እጁን ሰደዱት። 11እንዲሁም ሌላ አገልጋይ ላከ፤ እነርሱም ያን ደግሞ ደበደቡት፥ አዋርደውም ባዶውን ሰደዱት። 12እንደገናም ሦስተኛውን ላከ፤ እነርሱም ይኸኛውን ደግሞ አቁሰለው አስወጡት። 13የወይኑ አትክልት ጌታም ‘ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልካለሁ፤ ምናልባት እርሱን አይተው ያፍሩታል፤’ አለ። 14ተከራዮቹ ግን አይተውት እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ርስቱ ለእኛ እንዲሆን ኑ እንግደለው፤’ አሉ። 15ከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት። እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋቸዋል? 16ይመጣል እነዚህንም ተከራዮች ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።” ይህንንም በሰሙ ጊዜ “ይህስ በጭራሽ አይሁን፤” አሉ። 17#መዝ. 118፥22።እርሱ ግን ወደ እነርሱ ተመልክቶ “እንግዲህ
‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥
እርሱ ነው የማዕዘን ራስ የሆነው፤’
ተብሎ የተጻፈው ምን ማለት ነው? 18በዚያም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል፤ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይጨፈልቀዋል፤” አለ።
ለቄሣር ግብር ስለ መክፈል የቀረበ ጥያቄ
(ማቴ. 22፥15-22፤ ማር. 12፥13-17)
19የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። 20በቅርብ እየተከታተሉትም ለገዢው ግዛትና ሥልጣን አሳልፈው እንዲሰጡት ጻድቃን መስለው በቃሉ የሚያጠምዱትን ሰላዮች ላኩበት። 21እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት “መምህር ሆይ! እውነትን እንደምትናገርና እንደምታስተምር በሰው ፊትም እንደማታደላ እናውቃለን፤ ይልቁንም በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ ታስተምራለህ፤ 22ለቄሣር ግብር እንድንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም?” አሉት። 23እርሱ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ 24“አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ መልኩና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው። ሲመልሱም “የቄሣር ነው” አሉት። 25እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው። 26በሕዝቡም ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ በመልሱም እየተደነቁ ዝም አሉ።
ስለ ትንሣኤ ሙታን የቀረበ ጥያቄ
(ማቴ. 22፥23-33፤ ማር. 12፥18-27)
27 #
የሐዋ. 23፥8። የሙታንን ትንሣኤ የሚክዱ ሰዱቃውያን ቀርበው ጠየቁት፤ 28#ዘዳ. 25፥5።እንዲህም አሉ፤ “መምህር ሆይ! ሙሴ ‘አንድ ሰው ባለትዳር ወንድም ቢኖረውና፥ እርሱም ሳይወልድ ቢሞት፥ ወንድሙ የእርሱን ሚስት አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሎ ጻፈልን። 29እንግዲህ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ 30-31ሁለተኛውም አገባት፤ ሦስተኛውም፤ ሰባተኛውም እንዲሁ፤ ልጅም ሳይተው ሞቱ። 32ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች። 33እንግዲህ ሰባቱ አግብተዋታልና ሴቲቱ በትንሣኤ ከእነርሱ ለማንኛቸው ሚስት ትሆናለች?”
34ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም፤ 35ለሚመጣው ዓለምና ለሙታን ትንሣኤ ተገቢ የሆኑት ግን አያገቡም፤ አይጋቡምም፤ 36እንደ መላእክት ናቸውና፥ ወደ ፊት ሊሞቱም አይችሉም፤ የትንሣኤም ልጆች እንደመሆናቸው መጠን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። 37#ዘፀ. 3፥6።ሙታን እንደሚነሡ ግን ሙሴ እራሱ በቁጥቋጦው ታሪክ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ’ በማለቱ አስታወቀ፤ 38ሁሉም ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።” 39ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው “መምህር ሆይ! መልካም ተናገርህ፤” አሉት። 40ከዚያም ወዲህ ምንም ሊጠይቁት አልደፈሩም።
ስለ መሢሕ የቀረበ ጥያቄ
(ማቴ. 22፥41-46፤ ማር. 12፥35-37)
41እንዲህም አላቸው፥ “መሢሕ የዳዊት ልጅ ነው” እንዴት ይላሉ? 42#መዝ. 109፥1።ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ፦
“ጌታ ጌታዬን እንዲህ አለው፦ በቀኜ ተቀመጥ፥
43ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ” ይላልና፤
44እንግዲህ ዳዊት እራሱ “ጌታ ብሎ ይጠራዋል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል?”
ኢየሱስ ከጻፎች እንዲጠበቁ ሕዝቡን አስጠነቀቀ
(ማቴ. 23፥1-36፤ ማር. 12፥38-40)
45ሕዝቡም ሁሉ እየሰሙት ደቀ መዛሙርቱን 46“ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠንቀቁ፤ 47የመበለቶችን ቤት የሚበሉ፥ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ ናቸው፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ፤” አለ።
Dewis Presennol:
የሉቃስ ወንጌል 20: መቅካእኤ
Uwcholeuo
Rhanna
Copi
Eisiau i'th uchafbwyntiau gael eu cadw ar draws dy holl ddyfeisiau? Cofrestra neu mewngofnoda

: