ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 10

10
የኖኅ ልጆች ትው​ልድ
(1ዜ.መ. 1፥5-23)
1የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካ​ምና፥ የያ​ፌት ትው​ልድ ይህ ነው፤ ከጥ​ፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው።
የያ​ፌት ትው​ልድ
2የያ​ፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ይህ​ያን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። 3የጋ​ሜ​ርም ልጆች አስ​ከ​ናዝ፥ ሪፋት፥ ቴር​ጋማ ናቸው። 4የይ​ህ​ያ​ንም ልጆች ኤልሳ፥ ተር​ሴስ፥ ኬቲም፥ ሮድኢ#ዕብ. “ዶዳ​ኒም” ይላል። ናቸው። 5ከእ​ነ​ዚ​ህም የአ​ሕ​ዛብ ደሴ​ቶች ሁሉ በየ​ም​ድ​ራ​ቸው፥ በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው ተከ​ፋ​ፈሉ።
የካም ትው​ልድ
6የካ​ምም ልጆች ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን ናቸው። 7የኩ​ሽም ልጆች ሳባ፥ ኤው​ላጥ፥ ሰብታ፥ ሬጌም፥ ሰበ​ቅታ ናቸው። የሬ​ጌም ልጆ​ችም ሳባ፥ ዮድ​ዳን ናቸው። 8ኩሽም ናም​ሩ​ድን ወለደ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ ኀያል መሆን ጀመረ። 9እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀያል አዳኝ ነበረ፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀያል አዳኝ እንደ ናም​ሩድ ተባለ። 10የግ​ዛ​ቱም መጀ​መ​ሪያ በሰ​ና​ዖር ሀገር ባቢ​ሎን፥ ኦሬክ፥ አር​ካድ፥ ካሌ​ድን ናቸው። 11አሦ​ርም ከዚ​ያች ሀገር ወጣ፤ ነነ​ዌን፥ ረሆ​ቦት የተ​ባ​ለ​ች​ውን ከተማ ካለ​ህን፥ 12በነ​ነ​ዌና በካ​ለህ መካ​ከ​ልም ዳስን#ዕብ. “ሬሴን” ይላል። ሠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቂቱ ከተማ ናት። 13ምስ​ራ​ይ​ምም ሉዲ​ምን፥ ኢኒ​ሜ​ቲ​ምን፥ ላህ​ቢ​ምን፥ ንፍ​ታ​ሌ​ምን፥ ጳጥ​ሮ​ሶ​ኒ​ምን፥ 14ከእ​ነ​ርሱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች የወ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከስ​ሎ​ሂ​ም​ንና ቀፍ​ቶ​ሪ​ም​ንም ወለደ።
15ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥ 16ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ንን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ንን፥ 17ኤዌ​ዎ​ንን፥ አሩ​ቄ​ዎ​ንን፥ ኤሴ​ኒ​ዎ​ንን፥ 18አራ​ዲ​ዎ​ንን፥ ሰማ​ር​ዮ​ንን፥ አማ​ቲ​ንን#ዕብ. ምዕ. 10 ከቍ. 15 እስከ 18 ያለ​ውን በብዙ ቍጥር ይጽ​ፋል። ወለደ። ከዚ​ህም በኋላ የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ነገድ ተበ​ተኑ። 19የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ወሰን ከሲ​ዶን እስከ ጌራ​ራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳ​ማና ወደ ሴባ​ዮም እስከ ላሳ ይደ​ር​ሳል። 20የካም ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸ​ውና በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ም​ድ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።
የሴም ትው​ልድ
21ለሴ​ምም ደግሞ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እር​ሱም የያ​ፌት ታላቅ ወን​ድ​ምና የዔ​ቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆ​ነው ነው። 22የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን።#“ቃይ​ናን” በግ​እዙ እና በዕብ. የለም። 23የአ​ራ​ምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጋቴር፥ ሞሳሕ ናቸው። 24አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን፥ ሳላም ዔቦ​ርን ወለደ። 25ለዔ​ቦ​ርም ሁለት ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘ​መኑ ተከ​ፍ​ላ​ለ​ችና፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ዮቅ​ጣን ነው። 26ዮቅ​ጣ​ንም ኤል​ሞ​ዳ​ድን፥ ሳሌ​ፍ​ንም፥ ሐሰ​ረ​ሞ​ት​ንም፥ ያራ​ሕ​ንም፥ 27ሀዶ​ራ​ም​ንም፥ አዚ​ላ​ንም፥#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “ኤቤል” በዕብ. “አው​ዛል” ይላል። ደቅ​ላ​ንም፥ 28ዖባ​ል​ንም፥ አቤ​ማ​ኤ​ል​ንም፥ ሳባ​ንም፥ 29አፌ​ር​ንም፥ ኤው​ላ​ጥ​ንም፥ ዮባ​ብ​ንም ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ናቸው። 30ስፍ​ራ​ቸ​ውም ከማሲ አን​ስቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥ​ራቅ ተራራ ድረስ ነው። 31የሴም ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸ​ውና በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ም​ድ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።
32የኖኅ የል​ጆቹ ነገ​ዶች እንደ ትው​ል​ዳ​ቸው በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ዚ​ህም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሕዝ​ቦች በም​ድር ላይ ተዘሩ።

های‌لایت

به اشتراک گذاشتن

کپی

None

می خواهید نکات برجسته خود را در همه دستگاه های خود ذخیره کنید؟ برای ورودثبت نام کنید یا اگر ثبت نام کرده اید وارد شوید