ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 4

4
ቃየ​ልና አቤል
1አዳ​ምም ሚስ​ቱን ሔዋ​ንን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ቃየ​ል​ንም ወለ​ደ​ችው። 2እር​ስ​ዋም “ወንድ ልጅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ኘሁ” አለች። ደግ​ሞም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን ወለ​ደ​ችው። አቤ​ልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየ​ልም ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሆነ። 3ከብዙ ቀን በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ ቃየል ከም​ድር ፍሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ፤ 4አቤ​ልም ደግሞ ከበ​ጎቹ መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንና ከሰ​ቡት አቀ​ረበ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ አቤ​ልና ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ተመ​ለ​ከተ፤ 5ወደ ቃየ​ልና ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተም። ቃየ​ል​ንም እጅግ አሳ​ዘ​ነው፤ ፊቱም ጠቈረ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ቃየ​ልን አለው፥ “ለምን ታዝ​ና​ለህ? ለም​ንስ ፊትህ ጠቈረ? 7በእ​ው​ነት ያመ​ጣ​ህ​ልኝ አይ​ደ​ለም፤ አግ​ባ​ብስ በእ​ው​ነት ታመ​ጣ​ልኝ ዘንድ ነበር። በደ​ልህ፤ እን​ግ​ዲህ ዝም በል፤ የወ​ን​ድ​ምህ መመ​ለ​ሻው ወደ አንተ ነው፤ አን​ተም ትሰ​ለ​ጥ​ን​በ​ታ​ለህ።” 8ቃየ​ልም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን፥ “ና ወደ ሜዳ እን​ሂድ” አለው። በሜ​ዳም ሳሉ ቃየል በወ​ን​ድሙ በአ​ቤል ላይ ተነ​ሣ​በት፤ ገደ​ለ​ውም።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም#ግሪኩ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ” ይላል። ቃየ​ልን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየ​ልም አለ፥ “አላ​ው​ቅም፤ በውኑ የወ​ን​ድሜ ጠባ​ቂው እኔ ነኝን?” 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደ​ረ​ግህ? የወ​ን​ድ​ምህ የአ​ቤል የደሙ ድምፅ ከም​ድር ወደ እኔ ይጮ​ሃል። 11አሁ​ንም የወ​ን​ድ​ም​ህን ደም ከእ​ጅህ ለመ​ቀ​በል አፍ​ዋን በከ​ፈ​ተች በም​ድር ላይ አንተ የተ​ረ​ገ​ምህ ነህ።#ግእዙ “አፍ​ዋን የከ​ፈ​ተች ምድር የተ​ረ​ገ​መች ትሁን” ይላል። 12ምድ​ር​ንም ባረ​ስህ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ኀይ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥ​ህም፤ በም​ድር ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ ትሆ​ና​ለህ።” 13ቃየ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ኀጢ​አቴ ይቅር የማ​ት​ባል ታላቅ ናትን? 14እነሆ፥ ዛሬ ከም​ድር ፊት ከአ​ሳ​ደ​ድ​ኸኝ፥ ከፊ​ትህ እሰ​ወ​ራ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ እሆ​ና​ለሁ፤ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝም ሁሉ ይገ​ድ​ለ​ኛል።” 15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እን​ግ​ዲህ ቃየ​ልን የገ​ደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበ​ቀ​ል​በ​ታል።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃየ​ልን ያገ​ኘው ሁሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ምል​ክት አደ​ረ​ገ​ለት።
የቃ​የል ትው​ልድ
16ቃየ​ልም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ፤ በኤ​ዶም አን​ጻር ባለ​ችው ኖድ በም​ት​ባ​ለው ምድ​ርም ኖረ። 17ቃየ​ልም ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ስ​ችም፤ ሄኖ​ሕ​ንም ወለ​ደች። ከተ​ማም ሠራ፤ የከ​ተ​ማ​ይ​ቱ​ንም ስም በልጁ ስም “ሄኖሕ” አላት። 18ሄኖ​ሕም ጋይ​ዳ​ድን#ዕብ. “ኢራድ” ይላል። ወለደ፤ ጋይ​ዳ​ድም ሜኤ​ልን ወለደ፤ ሜኤ​ልም ማቱ​ሳ​ኤ​ልን ወለደ፤ ማቱ​ሳ​ኤ​ልም ላሜ​ሕን ወለደ። 19ላሜ​ሕም ለራሱ ሁለት ሚስ​ቶ​ችን አገባ፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ስም ሴላ ነበር። 20ዓዳም ዮቤ​ልን ወለ​ደች፤ እር​ሱም በድ​ን​ኳን የሚ​ቀ​መ​ጡት የዘ​ላ​ኖች አባት ነበረ። 21የወ​ን​ድ​ሙም ስም ኢዮ​ቤል ነበር፤ እር​ሱም በገ​ና​ንና መሰ​ን​ቆን አስ​ተ​ማረ። 22ሴላም ደግሞ ቶቤ​ልን ወለ​ደች። እር​ሱም ናስና ብረ​ትን የሚ​ሠራ ሆነ። የእ​ኅ​ቱም ስም ኖሄም ነበረ። 23ላሜ​ሕም ለሚ​ስ​ቶቹ ለዓ​ዳና ለሴላ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የላ​ሜሕ ሚስ​ቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገ​ሬ​ንም አድ​ምጡ፤ እኔ ጐል​ማ​ሳ​ውን ስለ መቍ​ሰሌ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም ስለ መወ​ጋቴ ገድ​የ​ዋ​ለ​ሁና፤ 24ቃየ​ልን ሰባት እጥፍ ይበ​ቀ​ሉ​ታል፤ ላሜ​ሕን ግን ሰባ ጊዜ ሰባት።”
ሴትና ሄኖስ
25አዳ​ምም ዳግ​መኛ ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች። ስሙ​ንም ቃየል በገ​ደ​ለው በአ​ቤል ፈንታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ዘር ተክ​ቶ​ል​ኛል ስትል ሴት አለ​ችው። 26ሴትም ወንድ ልጅ ወለደ። ስሙ​ንም ሄኖስ አለው፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም መጥ​ራት የጀ​መረ ነው።#ዕብ. “በዚ​ያን ጊዜ ሰዎች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም መጥ​ራት ጀመሩ” ይላል።

اکنون انتخاب شده:

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 4: አማ2000

های‌لایت

به اشتراک گذاشتن

کپی

None

می خواهید نکات برجسته خود را در همه دستگاه های خود ذخیره کنید؟ برای ورودثبت نام کنید یا اگر ثبت نام کرده اید وارد شوید