ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 8

8
የማየ አይኅ መጕ​ደል
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ በመ​ር​ከ​ብም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን አራ​ዊ​ቱን ሁሉ፥ እን​ስ​ሳ​ው​ንም ሁሉ፥ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ነፋ​ስን አመጣ፤ ውኃ​ውም ጐደለ፤ 2የቀ​ላ​ዩም ምን​ጮች፥ የሰ​ማ​ይም መስ​ኮ​ቶች ተደ​ፈኑ፤ ዝና​ብም ከሰ​ማይ ተከ​ለ​ከለ፤ 3ውኃ​ውም ከም​ድር ላይ እያ​ደር እየ​ቀ​ለለ ይሄድ ጀመረ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጐደለ። 4መር​ከ​ቢ​ቱም በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን በአ​ራ​ራት ተራ​ሮች ላይ ተቀ​መ​ጠች። 5ውኃ​ውም እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ወር ድረስ ይጐ​ድል ነበር፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የተ​ራ​ሮቹ ራሶች ተገ​ለጡ።
6ከአ​ርባ ቀን በኋ​ላም ኖኅ የሠ​ራ​ውን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን መስ​ኮት ከፈተ፤ 7ከም​ድ​ርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እን​ደ​ሆነ ያይ ዘንድ ቁራ​ውን ላከው፤ እር​ሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከም​ድር ላይ እስ​ኪ​ደ​ርቅ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሰም። 8ርግ​ብ​ንም ውኃው ከም​ድር ፊት ጐድሎ እንደ ሆነ እን​ድ​ታይ ከእ​ርሱ በኋላ ላካት። 9ነገር ግን ርግብ እግ​ር​ዋን የም​ታ​ሳ​ር​ፍ​በት ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ችም፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ተመ​ለ​ሰች፤ ውኃው በም​ድር ላይ ሁሉ ነበ​ረና፤ እጁን ዘረ​ጋና ተቀ​በ​ላት፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ውስጥ አገ​ባት። 10ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን እን​ደ​ገና ከመ​ር​ከብ ላካት። 11ርግ​ብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ በአ​ፍ​ዋም እነሆ፥ የለ​መ​ለመ የወ​ይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከም​ድር ላይ ውኃው እንደ ጐደለ ዐወቀ። 12ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን ላካት፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ እርሱ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።
13በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስት መቶ አንድ ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ውኃው ከም​ድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅም የሠ​ራ​ትን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን ክዳን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ውኃው ከም​ድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። 14በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ምድር ደረ​ቀች።
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኖኅ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፤ 16“አንተ ሚስ​ት​ህ​ንና ልጆ​ች​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ከመ​ር​ከብ ውጣ። 17ከአ​ንተ ጋር ያሉ​ትን አራ​ዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር አው​ጣ​ቸው፤ በም​ድ​ርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት።”#ዕብ. “በም​ድር ላይ ይር​መ​ስ​መሱ፥ ይዋ​ለዱ፥ በም​ድ​ርም ላይ ይብዙ” ይላል። 18ኖኅም ሚስ​ቱን፥ ልጆ​ቹ​ንና የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ይዞ ወጣ፤ 19አራ​ዊት ሁሉ፥ እን​ስ​ሳም ሁሉ፥ ወፎ​ችም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከመ​ር​ከብ ወጡ።
ኖኅ መሥ​ዋ​ዕት እንደ አቀ​ረበ
20ኖኅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፥ ከን​ጹ​ሕም እን​ስሳ ሁሉ፥ ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችም ሁሉ ወሰደ፤ በመ​ሠ​ው​ያ​ውም ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም። 22በም​ድር ዘመን ሁሉ መዝ​ራ​ትና ማጨድ፥ ብር​ድና ሙቀት፥ በጋና ክረ​ምት፥ ቀንና ሌሊት አያ​ቋ​ር​ጡም።”

اکنون انتخاب شده:

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 8: አማ2000

های‌لایت

به اشتراک گذاشتن

کپی

None

می خواهید نکات برجسته خود را در همه دستگاه های خود ذخیره کنید؟ برای ورودثبت نام کنید یا اگر ثبت نام کرده اید وارد شوید