የሉ​ቃስ ወን​ጌል 21

21
ሁለት መሐ​ለቅ ስለ አገ​ባ​ችው ድሃ ሴት
1በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ መባ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ገቡ ባለ​ጠ​ጎ​ችን አየ። 2አን​ዲት ድሃ መበ​ለ​ትም ሁለት መሐ​ለቅ ስታ​ስ​ገባ አየ። 3እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህቺ ድሃ መበ​ለት ከሁሉ ይልቅ አብ​ዝታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አገ​ባች። 4እነ​ዚህ ሁሉ ከተ​ረ​ፋ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አግ​ብ​ተ​ዋ​ልና፤ ይህቺ ግን ከድ​ህ​ነቷ ያላ​ትን ጥሪ​ቷን ሁሉ አገ​ባች።”
ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ስለ ቤተ መቅ​ደስ መፍ​ረስ
5ስለ ቤተ መቅ​ደ​ስም ድን​ጋዩ ያማረ ነው፥ አሠ​ራ​ሩም ያጌጠ ነው የሚ​ሉት ነበሩ። 6እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ታያ​ላ​ች​ሁን? በእ​ዚህ ቦታ ድን​ጋይ በድ​ን​ጋይ ላይ የማ​ይ​ተ​ው​በ​ትና ሳይ​ፈ​ርስ የማ​ይ​ቀ​ር​በት ዘመን ይመ​ጣል።” 7እነ​ር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ መቼ ይደ​ረ​ጋል? ይህስ የሚ​ሆ​ን​በት ጊዜው፥ ምል​ክ​ቱስ ምን​ድን ነው?” ብለው ጠየ​ቁት። 8እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብዙ​ዎች እኔ ክር​ስ​ቶስ ነኝ፤ ጊዜ​ውም ደር​ሶ​አል እያሉ በስሜ ይመ​ጣ​ሉና እን​ዳ​ያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ት​ላ​ችሁ አት​ሂዱ። 9ጦር​ነ​ት​ንና ጠብን፥ ክር​ክ​ር​ንም በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ አት​ደ​ን​ግጡ፤ አስ​ቀ​ድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፤ ነገር ግን ወዲ​ያው የሚ​ፈ​ጸም አይ​ደ​ለም።”
10እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ይነ​ሣሉ። 11በየ​ሀ​ገሩ ታላቅ የም​ድር መነ​ዋ​ወ​ጥና ራብ፥ በሰ​ውም ላይ በሽ​ታና ፍር​ሀት ይመ​ጣል፤ በሰ​ማ​ይም ታላቅ ምል​ክት ይሆ​ናል። 12ከዚ​ህም ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ይይ​ዙ​አ​ች​ኋል፤ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያስ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገ​ሥ​ታ​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል። 13ይህም በእ​ነ​ርሱ ላይ ምስ​ክር ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል። 14#ሉቃ. 12፥11-12። ዕወቁ፤ የም​ት​ና​ገ​ሩ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ አታ​ስቡ። 15በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ። 16ወላ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ ወዳ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል። 17ሁሉም ስለ ስሜ ይጠ​ሉ​አ​ች​ኋል፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልም። 18ነገር ግን ከራስ ጠጕ​ራ​ችሁ አን​ዲቱ እንኳ አት​ጠ​ፋም። 19በት​ዕ​ግ​ሥ​ታ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን ገን​ዘብ ታደ​ር​ጓ​ታ​ላ​ችሁ።
ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ጥፋት መድ​ረስ
20“ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ጭፍ​ሮች ከብ​በ​ዋት ባያ​ችሁ ጊዜ ጥፋቷ እንደ ደረሰ ዕወቁ። 21ያን​ጊዜ በይ​ሁዳ ያሉ ወደ ተራራ ይሽሹ፤ በመ​ካ​ከ​ልዋ ያሉም ከእ​ር​ስዋ ይውጡ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ያሉም ወደ እር​ስዋ አይ​ግቡ። 22#ሆሴዕ 9፥7። በእ​ር​ስዋ ላይ የተ​ጻ​ፈው ሁሉ ይፈ​ጸም ዘንድ እር​ስ​ዋን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜዋ ነውና። 23ነገር ግን በዚያ ወራት ለፀ​ነ​ሱና ለሚ​ያ​ጠቡ ወዮ​ላ​ቸው፤ በም​ድር ላይ ጽኑ መከራ፥ በዚ​ህም ሕዝብ ላይ መቅ​ሠ​ፍት ይሆ​ና​ልና። 24በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።
ስለ ክር​ስ​ቶስ መም​ጣ​ትና ስለ ምል​ክ​ቶቹ
25 # ኢሳ. 13፥10፤ ሕዝ. 32፥7፤ ኢዩ. 2፥31፤ ራእ. 6፥12-13። “በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ላይ ምል​ክት ይሆ​ናል፤ በም​ድር ላይም አሕ​ዛብ ይጨ​ነ​ቃሉ፤#“ከዋ​ክ​ብ​ትም ከሰ​ማይ ወደ ምድር ይወ​ድ​ቃሉ” የሚል በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ ይገ​ኛል። ከባ​ሕ​ሩና ከሞ​ገዱ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ይሸ​በ​ራሉ። 26በዓ​ለም ላይ ከሚ​መ​ጣው ፍር​ሀ​ትና ሽብር የተ​ነ​ሣም የሰ​ዎች ነፍስ ትዝ​ላ​ለች፤ ያን​ጊዜ የሰ​ማ​ያት ኀይል ይና​ወ​ጣ​ልና። 27#ዳን. 7፥13፤ ራእ. 1፥7። ያን​ጊ​ዜም በሰ​ማይ ደመና፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልና ክብር ሲመጣ የሰ​ውን ልጅ ያዩ​ታል። 28ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅ​ን​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አንሡ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ መጥ​ቶ​አ​ልና።”
29ምሳ​ሌም መስሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በለ​ስ​ንና ዛፎ​ችን ሁሉ እዩ። 30ለም​ል​መ​ውም ያያ​ች​ኋ​ቸው እንደ ሆነ መከር እንደ ደረሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 31እን​ዲሁ እና​ን​ተም ይህ እንደ ሆነ ስታዩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እንደ ደረ​ሰች ዕወቁ። 32እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህ ሁሉ እስ​ኪ​ደ​ረግ ድረስ ይህቺ ትው​ልድ አታ​ል​ፍም። 33ሰማ​ይና ምድር ያል​ፋል፤ ቃሌ ግን አያ​ል​ፍም።
ትም​ህ​ር​ትና ምክር
34“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች። 35በም​ድር በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ላይ እንደ ተዘ​ረ​ጋች ወጥ​መድ ትደ​ር​ሳ​ለ​ችና። 36እን​ግ​ዲህ ከዚህ ከሚ​መ​ጣው ሁሉ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ማም​ለጥ እን​ድ​ት​ችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እን​ድ​ት​ቆሙ ሁል​ጊዜ ትጉ።”
በደ​ብረ ዘይት ስለ ማደሩ
37 # ሉቃ. 19፥47። ቀን ቀን በመ​ቅ​ደስ#በግ​እዙ “በም​ኵ​ራብ” ይላል። ያስ​ተ​ምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚ​ባ​ለው ተራራ ያድር ነበር። 38ሕዝ​ቡም ሁሉ ቃሉን ሊሰሙ እርሱ ወዳ​ለ​በት ወደ መቅ​ደስ ማል​ደው ይሄዱ ነበር።

اکنون انتخاب شده:

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 21: አማ2000

های‌لایت

به اشتراک گذاشتن

کپی

None

می خواهید نکات برجسته خود را در همه دستگاه های خود ذخیره کنید؟ برای ورودثبت نام کنید یا اگر ثبت نام کرده اید وارد شوید