1
የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁም ብቷደዱ፥ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ሁሉ ያውቋችኋል።”
Vertaa
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 13:34-35
2
የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15
እንግዲህ እኔ መምህራችሁና ጌታችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኋችሁ እናንተም እንዲሁ የባልጀሮቻችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል። እኔ እንደ አደረግሁላችሁ እናንተም ልታደርጉ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 13:14-15
3
የዮሐንስ ወንጌል 13:7
ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔ የምሠራውን አንተ ዛሬ አታውቅም፤ ኋላ ግን ታስተውለዋለህ” ብሎ መለሰለት።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 13:7
4
የዮሐንስ ወንጌል 13:16
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ የለም፤ ከላከው የሚበልጥ መልእክተኛም የለም።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 13:16
5
የዮሐንስ ወንጌል 13:17
ይህንም ዐውቃችሁ ብትሠሩ ብፁዓን ናችሁ።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 13:17
6
የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5
ራት ከሚበሉበት ተነሥቶ ልብሱን አኖረና ማበሻ ጨርቅ አንሥቶ ወገቡን ታጠቀ። በኵስኵስቱም ውኃ ቀድቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጥብ ጀመር፤ በዚያ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅም አበሰ።
Tutki የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5
Koti
Raamattu
Suunnitelmat
Videot