የሉ​ቃስ ወን​ጌል 16

16
ስለ ዐመ​ፀ​ኛው መጋቢ
1ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መጋቢ የነ​በ​ረው አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ እን​ደ​ሚ​በ​ትን አድ​ር​ገው በእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ሱት። 2ጌታ​ውም ጠርቶ፦ ‘በአ​ንተ ላይ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር ምን​ድን ነው? እን​ግ​ዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልት​ሆን አት​ች​ል​ምና የመ​ጋ​ቢ​ነ​ት​ህን ሂሳብ አስ​ረ​ክ​በኝ’ አለው። 3ያም መጋቢ ዐስቦ እን​ዲህ አለ፦ ‘ምን ላድ​ርግ? አሁን ጌታዬ ከመ​ጋ​ቢ​ነቴ ይሽ​ረ​ኛል፤ ማረስ አል​ች​ልም፤ ለመ​ለ​መ​ንም አፍ​ራ​ለሁ። 4እን​ግ​ዲህ ጌታዬ ከም​ግ​ብ​ናዬ የሻ​ረኝ እንደ ሆነ በቤ​ታ​ቸው ይቀ​በ​ሉኝ ዘንድ የማ​ደ​ር​ገ​ውን እኔ ዐው​ቃ​ለሁ።’ 5ለጌ​ታ​ውም ዕዳ የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ትን ጠራ​ቸው፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም፦ ‘ለጌ​ታዬ የም​ት​ከ​ፍ​ለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እር​ሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ዘይት ነው’ አለው። 6‘እነሆ፥ ደብ​ዳ​ቤህ፤ ተቀ​ም​ጠህ አምሳ ማድጋ አለ​ብኝ ብለህ ፈጥ​ነህ ጻፍ’ አለው። 7ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፦ ‘አን​ተሳ ለጌ​ታዬ የም​ት​ከ​ፍ​ለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እር​ሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብ​ዳ​ቤህ፤ ተቀ​ም​ጠህ ሰማ​ንያ አለ​ብኝ ብለህ ፈጥ​ነህ ጻፍ’ አለው። 8ጌታ​ውም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ከብ​ር​ሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓ​ለ​ማ​ቸው ይራ​ቀ​ቃ​ሉና። 9እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ባለ​ቀ​ባ​ችሁ ጊዜ እነ​ርሱ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው#በግ​ሪኩ “በዘ​ለ​ዓ​ለም ቤቶች” ይላል። ይቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ዘንድ በዐ​መፃ ገን​ዘብ ለእ​ና​ንተ ወዳ​ጆች አድ​ር​ጉ​በት።
10“በጥ​ቂት የሚ​ታ​መን በብዙ ይታ​መ​ናል፤ በጥ​ቂት የሚ​ያ​ም​ፅም በብ​ዙም ቢሆን ያም​ፃል። 11በዐ​መፃ ገን​ዘብ ካል​ታ​መ​ና​ችሁ በእ​ው​ነ​ተ​ኛው ገን​ዘብ ማን ያም​ና​ች​ኋል? 12በሌ​ላ​ውስ ገን​ዘብ ካል​ታ​መ​ና​ችሁ የራ​ሱን#በግ​ሪኩ “የእ​ና​ን​ተን” ይላል። ማን ይሰ​ጣ​ች​ኋል? 13#ማቴ. 6፥24። ለሁ​ለት ጌቶች መገ​ዛት የሚ​ችል አገ​ል​ጋይ የለም፤ ካል​ሆ​ነም አን​ዱን ይወ​ድ​ዳል፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይጠ​ላል፤ ወይም ለአ​ንዱ ይታ​ዘ​ዛል፤ ለሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም እንቢ ይላል፤ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ ገን​ዘብ እየ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መገ​ዛት አት​ች​ሉም።”
14ገን​ዘ​ብን የሚ​ወዱ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይህን ሁሉ ነገር ሰም​ተው ተጠ​ቃ​ቀ​ሱ​በት። 15እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ#በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “የረ​ከሰ” ይላል። ይሆ​ና​ልና።
ስለ ኦሪ​ትና ስለ ነቢ​ያት
16 # ማቴ. 11፥12-13። “ኦሪ​ትም ነቢ​ያ​ትም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ዮሐ​ንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ይሰ​በ​ካል፤ ሁሉም ወደ እር​ስዋ ይጋ​ፋል። 17#ማቴ. 5፥18። ነገር ግን ከኦ​ሪት አን​ዲት ቃል#በግ​ሪኩ “አን​ዲት ነቍጣ” ይላል። ከም​ት​ወ​ድቅ ሰማ​ይና ምድር ቢያ​ልፍ ይቀ​ላል።
18 # ማቴ. 5፥32፤ 1ቆሮ. 7፥10-11። “ሚስ​ቱን ፈትቶ ሌላ​ዪ​ቱን የሚ​ያ​ገባ ሁሉ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ ባልዋ የፈ​ታ​ት​ንም የሚ​ያ​ገባ ያመ​ነ​ዝ​ራል።#“ባልዋ የፈ​ታ​ትም ሌላ ወንድ ብታ​ገባ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለች” የሚል ንባብ በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ ይገ​ኛል።
ስለ አንድ ባለ​ጸ​ጋና ስለ አል​ዓ​ዛር
19“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር። 20በቍ​ስል ሕመም ተይዞ በባ​ለ​ጸ​ጋው ደጅ የወ​ደቀ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል አንድ ድሃም ነበረ። 21ከባ​ለ​ጸ​ጋው ማዕድ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ው​ንም ፍር​ፋሪ ሊመ​ገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾ​ችም እየ​መጡ ቍስ​ሉን ይል​ሱት ነበር። 22ከዚ​ህም በኋላ ድሃው ሞተ፤ መላ​እ​ክ​ትም ወደ አብ​ር​ሃም አጠ​ገብ ወሰ​ዱት፤ ባለ​ጸ​ጋ​ውም ደግሞ ሞተ፤ ተቀ​በ​ረም፤ 23በሲ​ኦ​ልም በሥ​ቃይ ሳለ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ አብ​ር​ሃ​ምን ከሩቅ አየው፤ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጦ አየው። 24‘አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ እዘ​ን​ልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠ​ቃ​ይ​ቻ​ለ​ሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላ​ሴን ያቀ​ዘ​ቅ​ዝ​ልኝ ዘንድ አል​ዓ​ዛ​ርን ላከው’ ብሎ ተጣራ። 25አብ​ር​ሃም ግን እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕ​ይ​ወ​ትህ ተድ​ላና ደስታ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ በች​ጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እን​ዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድ​ላና ደስታ ያደ​ር​ጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀ​በ​ላ​ለህ። 26ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እና​ንተ ማለፍ የሚሹ እን​ዳ​ይ​ችሉ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የሆ​ኑ​ትም ወደ እኛ እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ታላቅ ገደል አለ’ 27እር​ሱም እን​ዲህ አለው፦ ‘አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ አል​ዓ​ዛ​ርን ወደ አባቴ ቤት እን​ድ​ት​ል​ከው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ። 28አም​ስት ወን​ድ​ሞች ስለ አሉኝ ይን​ገ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ወደ​ዚች የሥ​ቃይ ቦታ እን​ዳ​ይ​መጡ ይስሙ።’#በግ​ሪኩ “ይመ​ስ​ክ​ር​ላ​ቸው” ይላል። 29አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴና ነቢ​ያት አሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱን ይስሙ’ አለው። 30እር​ሱም፦ ‘የለም፤ አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ ከሙ​ታን አንዱ ወደ እነ​ርሱ ካል​ሄ​ደና ካል​ነ​ገ​ራ​ቸው ንስሓ አይ​ገ​ቡም’ አለው። 31አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴ​ንና ነቢ​ያ​ትን ካል​ሰ​ሙማ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነሣ ቢኖ​ርም እንኳ አይ​ሰ​ሙ​ትም፤ አያ​ም​ኑ​ት​ምም’ አለው።”

Kiemelés

Megosztás

Másolás

None

Szeretnéd, hogy a kiemeléseid minden eszközödön megjelenjenek? Regisztrálj vagy jelentkezz be