የሉቃስ ወንጌል 16
16
ስለ ዐመፀኛው መጋቢ
1ጌታችን ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፥ “መጋቢ የነበረው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ገንዘቡን ሁሉ እንደሚበትን አድርገው በእርሱ ዘንድ ከሰሱት። 2ጌታውም ጠርቶ፦ ‘በአንተ ላይ የምሰማው ይህ ነገር ምንድን ነው? እንግዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ’ አለው። 3ያም መጋቢ ዐስቦ እንዲህ አለ፦ ‘ምን ላድርግ? አሁን ጌታዬ ከመጋቢነቴ ይሽረኛል፤ ማረስ አልችልም፤ ለመለመንም አፍራለሁ። 4እንግዲህ ጌታዬ ከምግብናዬ የሻረኝ እንደ ሆነ በቤታቸው ይቀበሉኝ ዘንድ የማደርገውን እኔ ዐውቃለሁ።’ 5ለጌታውም ዕዳ የሚከፍሉትን ጠራቸው፤ የመጀመሪያውንም፦ ‘ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ዘይት ነው’ አለው። 6‘እነሆ፥ ደብዳቤህ፤ ተቀምጠህ አምሳ ማድጋ አለብኝ ብለህ ፈጥነህ ጻፍ’ አለው። 7ሁለተኛውንም፦ ‘አንተሳ ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብዳቤህ፤ ተቀምጠህ ሰማንያ አለብኝ ብለህ ፈጥነህ ጻፍ’ አለው። 8ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመሰገነው፤ ከብርሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓለማቸው ይራቀቃሉና። 9እኔም እላችኋለሁ፦ ባለቀባችሁ ጊዜ እነርሱ በዘለዓለም ቤታቸው#በግሪኩ “በዘለዓለም ቤቶች” ይላል። ይቀበሉአችሁ ዘንድ በዐመፃ ገንዘብ ለእናንተ ወዳጆች አድርጉበት።
10“በጥቂት የሚታመን በብዙ ይታመናል፤ በጥቂት የሚያምፅም በብዙም ቢሆን ያምፃል። 11በዐመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ በእውነተኛው ገንዘብ ማን ያምናችኋል? 12በሌላውስ ገንዘብ ካልታመናችሁ የራሱን#በግሪኩ “የእናንተን” ይላል። ማን ይሰጣችኋል? 13#ማቴ. 6፥24። ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚችል አገልጋይ የለም፤ ካልሆነም አንዱን ይወድዳል፤ ሁለተኛውንም ይጠላል፤ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል፤ ለሁለተኛውም እንቢ ይላል፤ እንዲሁም እናንተ ገንዘብ እየወደዳችሁ ለእግዚአብሔር መገዛት አትችሉም።”
14ገንዘብን የሚወዱ ፈሪሳውያንም ይህን ሁሉ ነገር ሰምተው ተጠቃቀሱበት። 15እርሱም፥ “እናንተስ ለሰው ይምሰል ትመጻደቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ልቡናችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ#በግሪኩ እና በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “የረከሰ” ይላል። ይሆናልና።
ስለ ኦሪትና ስለ ነቢያት
16 #
ማቴ. 11፥12-13። “ኦሪትም ነቢያትም ከጥንት ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ ይጋፋል። 17#ማቴ. 5፥18። ነገር ግን ከኦሪት አንዲት ቃል#በግሪኩ “አንዲት ነቍጣ” ይላል። ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል።
18 #
ማቴ. 5፥32፤ 1ቆሮ. 7፥10-11። “ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባልዋ የፈታትንም የሚያገባ ያመነዝራል።#“ባልዋ የፈታትም ሌላ ወንድ ብታገባ ታመነዝራለች” የሚል ንባብ በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ ይገኛል።
ስለ አንድ ባለጸጋና ስለ አልዓዛር
19“አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅግም ቀጭን ልብስ ይለብስ ነበር፤ ዘወትርም ተድላና ደስታ ያደርግ ነበር። 20በቍስል ሕመም ተይዞ በባለጸጋው ደጅ የወደቀ አልዓዛር የሚባል አንድ ድሃም ነበረ። 21ከባለጸጋው ማዕድ የሚወድቀውንም ፍርፋሪ ሊመገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾችም እየመጡ ቍስሉን ይልሱት ነበር። 22ከዚህም በኋላ ድሃው ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት፤ ባለጸጋውም ደግሞ ሞተ፤ ተቀበረም፤ 23በሲኦልም በሥቃይ ሳለ ዐይኖቹን አንሥቶ አብርሃምን ከሩቅ አየው፤ አልዓዛርንም በአጠገቡ ተቀምጦ አየው። 24‘አባት አብርሃም ሆይ፥ እዘንልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠቃይቻለሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላሴን ያቀዘቅዝልኝ ዘንድ አልዓዛርን ላከው’ ብሎ ተጣራ። 25አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ። 26ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ማለፍ የሚሹ እንዳይችሉ፥ ከእናንተ ወገን የሆኑትም ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል አለ’ 27እርሱም እንዲህ አለው፦ ‘አባት አብርሃም ሆይ፥ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ። 28አምስት ወንድሞች ስለ አሉኝ ይንገራቸው፤ እነርሱም ደግሞ ወደዚች የሥቃይ ቦታ እንዳይመጡ ይስሙ።’#በግሪኩ “ይመስክርላቸው” ይላል። 29አብርሃምም፦ ‘ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው። 30እርሱም፦ ‘የለም፤ አባት አብርሃም ሆይ፥ ከሙታን አንዱ ወደ እነርሱ ካልሄደና ካልነገራቸው ንስሓ አይገቡም’ አለው። 31አብርሃምም፦ ‘ሙሴንና ነቢያትን ካልሰሙማ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ቢኖርም እንኳ አይሰሙትም፤ አያምኑትምም’ አለው።”
Jelenleg kiválasztva:
የሉቃስ ወንጌል 16: አማ2000
Kiemelés
Megosztás
Másolás
Szeretnéd, hogy a kiemeléseid minden eszközödön megjelenjenek? Regisztrálj vagy jelentkezz be

: