1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ ቅርንጫፎቹም እናንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚያፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉምና።
비교
የዮሐንስ ወንጌል 15:5 살펴보기
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ከአልኖረ ብቻውን ሊያፈራ እንደማይችል እናንተም እንዲሁ በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
የዮሐንስ ወንጌል 15:4 살펴보기
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔም ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የምትሹትን ሁሉ ትለምናላችሁ፤ ይደረግላችሁማል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:7 살펴보기
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ፥ ፍሬም እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር፤ አብንም በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እንዲሰጣችሁ ሾምኋችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:16 살펴보기
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም።
የዮሐንስ ወንጌል 15:13 살펴보기
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:2 살펴보기
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
“እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድቷደዱ የእኔ ትእዛዝ ይህች ናት።
የዮሐንስ ወንጌል 15:12 살펴보기
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ብታፈሩ፥ ደቀ መዛሙርቴም ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:8 살펴보기
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
“እውነተኛ የወይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካዩም አባቴ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 15:1 살펴보기
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጥሉታል፤ ሰብስበውም በእሳት ያቃጥሉታል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:6 살펴보기
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ደስታዬ በእናንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስታችሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገርኋችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:11 살펴보기
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
የምትወዱኝ ብትሆኑ ትእዛዜን ጠብቁ፤ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ፥ በፍቅሩም እንደምኖር እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:10 살펴보기
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እርስ በርሳችሁም እንድቷደዱ ይህን አዝዣችኋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 15:17 살펴보기
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
እናንተስ ከዓለም ብትሆኑ ዓለም በወደዳችሁ ነበር፤ ዓለም ወገኖቹን ይወዳልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ ከዓለም አይደላችሁምና ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:19 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상