1
የዮሐንስ ወንጌል 16:33
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኋችሁ፤ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለሙን ድል ነሥቼዋለሁና።”
비교
የዮሐንስ ወንጌል 16:33 살펴보기
2
የዮሐንስ ወንጌል 16:13
ያ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ እርሱ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 16:13 살펴보기
3
የዮሐንስ ወንጌል 16:24
እስካሁን ምንም በስሜ አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ ለምኑ፤ ታገኙማላችሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 16:24 살펴보기
4
የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8
“እኔ በእውነት የሚሆነውን እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም በመጣ ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአትና ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍርድም ይዘልፈዋል።
የዮሐንስ ወንጌል 16:7-8 살펴보기
5
የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23
እናንተም ዛሬ ታዝናላችሁ፤ እንደገናም አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። ያንጊዜም እኔን የምትለምኑኝ አንዳች የለም፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በስሜ አብን ብትለምኑት ሁሉን ይሰጣችኋል።
የዮሐንስ ወንጌል 16:22-23 살펴보기
6
የዮሐንስ ወንጌል 16:20
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፤ ዓለምም ደስ ይለዋል፤ እናንተ ግን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
የዮሐንስ ወንጌል 16:20 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상