ኦሪት ዘፍጥረት 22
22
ይስሐቅን እንዲሠዋለት እግዚአብሔር አብርሃምን መፈተኑ
1ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ። #ዕብ. 11፥17-19።
2እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው። #2ዜ.መ. 3፥1።
3አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ። 4በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ። 5ከዚህ በኋላ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ ከአህያው ጋር እዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ከሰገድን በኋላ እንመለሳለን” አላቸው።
6አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢለዋውንና እሳቱን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሲሄዱ ሳለ፥ 7ይስሐቅ አብርሃምን “አባባ!” አለው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁ ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እነሆ፥ እሳትና እንጨት ይዘናል፤ ታዲያ ለመሥዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?” በማለት አብርሃምን ጠየቀው።
8አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ለራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።
9እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሠዊያው ላይ አጋደመው። #ያዕ. 2፥21። 10ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንሥቶ እጁን ዘረጋ፤ 11ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው።
አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ።
12መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።”
13አብርሃም ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ ቀንዶቹ በቊጥቋጦ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። 14አብርሃም ያንን ቦታ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ። #22፥14 እግዚአብሔር ያዘጋጃል፦ በዕብራይስጥ “ያህዌ ይርኤ” ሲሆን “እግዚአብሔር ያያል” ማለት ነው።
15የእግዚአብሔር መልአክ ሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራውና እንዲህ አለው፤ 16“እግዚአብሔር ‘ብዙ በረከት እንደምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ’ ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቈጠብክ፥ #ዕብ. 6፥13-14። 17እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነሥተው ከተሞቻቸውን ይይዛሉ። #ዕብ. 11፥12። 18ትእዛዜን ስለ ፈጸምክ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።” #ሐ.ሥ. 3፥25።
19ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ።
የናኮር ዘሮች
20ከዚህ ሁሉ በኋላ ሚልካ ለወንድሙ ለናኮር ልጆች እንደ ወለደችለት አብርሃም ሰማ፤ እነርሱም፥ 21የመጀመሪያው ዑፅ፥ ወንድሙም ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፤ 22ኬሠድ፥ ሐዞ፥ ፊልዳሽ፥ ይድላፍና በቱኤል ናቸው። 23በቱኤል ርብቃን ወለደ፤ ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደችለት። 24ረኡማ የተባለችው የናኮር ቊባት ደግሞ ጤባሕን፥ ገሐምን፥ ተሐሽንና፥ ማዕካን ወለደችለት።
Voafantina amin'izao fotoana izao:
ኦሪት ዘፍጥረት 22: አማ05
Asongadina
Hizara
Dika mitovy
Tianao hovoatahiry amin'ireo fitaovana ampiasainao rehetra ve ireo nasongadina? Hisoratra na Hiditra
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: