ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 3

3
የሰው አለ​መ​ታ​ዘዝ
1እባ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ከፈ​ጠ​ራ​ቸው ከም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይልቅ ተን​ኰ​ለኛ ነበር። እባ​ብም ሴቲ​ቱን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ አት​ብሉ ያላ​ችሁ ለም​ን​ድን ነው?” አላት። 2ሴቲ​ቱም ለእ​ባቡ አለ​ችው፥ “በገ​ነት መካ​ከል ካለው ከሚ​ያ​ፈ​ራው ዛፍ ፍሬ እን​በ​ላ​ለን፤ 3ነገር ግን በገ​ነት መካ​ከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ፦ እን​ዳ​ት​ሞቱ ከእ​ርሱ አት​ብሉ፤ አት​ን​ኩ​ትም።” 4እባ​ብም ለሴ​ቲቱ አላት፥ “ሞትን አት​ሞ​ቱም፤ 5ከእ​ር​ስዋ በበ​ላ​ችሁ ቀን፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ እን​ዲ​ከ​ፈቱ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሆኑ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ሚ​ያ​ውቅ ነው እንጂ።” 6ሴቲ​ቱም ዛፉ ለመ​ብ​ላት ያማረ እን​ደ​ሆነ፥ ለዐ​ይ​ንም ለማ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጐ​መጅ፥ መል​ካ​ም​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍ​ሬው ወሰ​ደ​ችና በላች፤ ለባ​ል​ዋም ደግሞ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር በላ። 7የሁ​ለ​ቱም ዐይ​ኖች ተከ​ፈቱ፤ እነ​ር​ሱም ዕራ​ቁ​ታ​ቸ​ውን እንደ ሆኑ ዐወቁ፤ አፈ​ሩም፤#“አፈ​ሩም” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የበ​ለ​ስ​ንም ቅጠ​ሎች ሰፍ​ተው ለእ​ነ​ርሱ ለራ​ሳ​ቸው ግል​ድም አደ​ረጉ። 8እነ​ር​ሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክን ድምፅ በገ​ነት ውስጥ ሲመ​ላ​ለስ ሰሙ፤ አዳ​ምና ሚስ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ም​ላክ ፊት በገ​ነት ዛፎች መካ​ከል ተሸ​ሸጉ።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አዳ​ምን ጠርቶ፥ “አዳም፥ ወዴት አለህ?” አለው። 10አዳ​ምም አለ፥ “በገ​ነት ስት​መ​ላ​ለስ ድም​ፅ​ህን ሰማሁ፤ ዕራ​ቁ​ቴ​ንም ስለ​ሆ​ንሁ ፈራሁ፤ ተሸ​ሸ​ግ​ሁም።” 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ዕራ​ቁ​ት​ህን እን​ደ​ሆ​ንህ ማን ነገ​ረህ? ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ካዘ​ዝ​ሁህ ዛፍ በውኑ በላ​ህን?” 12አዳ​ምም አለ፥ “ከእኔ ጋር እን​ድ​ት​ሆን የሰ​ጠ​ኸኝ ሴት እር​ስዋ ከዛፉ ሰጠ​ች​ኝና በላሁ።” 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሴቲ​ቱን፥ “ይህን ለምን አደ​ረ​ግሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም አለች፥ “እባብ አሳ​ተ​ኝና በላሁ።”
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም እባ​ቡን አለው፥ “ይህን ስላ​ደ​ረ​ግህ ከእ​ን​ስ​ሳት ሁሉ፥ ከም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ ተለ​ይ​ተህ አንተ የተ​ረ​ገ​ምህ ሁን ፤ በደ​ረ​ት​ህና በሆ​ድ​ህም ትሄ​ዳ​ለህ፤ በሕ​ይ​ወ​ት​ህም ዘመን ሁሉ አፈ​ርን ትበ​ላ​ለህ። 15በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።” 16ለሴ​ቲ​ቱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላት፥ “ጭን​ቅ​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፤ በጭ​ንቅ ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ከወ​ለ​ድ​ሽም በኋላ ፈቃ​ድሽ ወደ ባልሽ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም ይገ​ዛ​ሻል።” 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ምን አለው፥ “የሚ​ስ​ት​ህን ቃል ሰም​ተ​ሃ​ልና፥ ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ከአ​ዘ​ዝ​ሁህ ከዚያ ዛፍም በል​ተ​ሃ​ልና ምድር በሥ​ራህ የተ​ረ​ገ​መች ትሁን፤ በሕ​ይ​ወት ዘመ​ን​ህም ሁሉ በድ​ካም ከእ​ር​ስዋ ትበ​ላ​ለህ፤ 18እሾ​ህ​ንና አሜ​ከ​ላን ታበ​ቅ​ል​ብ​ሃ​ለች፤ የም​ድ​ር​ንም ቡቃያ ትበ​ላ​ለህ። 19ወደ ወጣ​ህ​በት መሬት እስ​ክ​ት​መ​ለስ ድረስ በፊ​ትህ ወዝ እን​ጀ​ራ​ህን ትበ​ላ​ለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈ​ርም ትመ​ለ​ሳ​ለ​ህና።” 20አዳ​ምም ለሚ​ስቱ “ሔዋን” ብሎ ስም አወጣ፤ የሕ​ያ​ዋን ሁሉ እናት ናትና። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለአ​ዳ​ምና ለሚ​ስቱ የቁ​ር​በ​ትን ልብስ አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፥ አለ​በ​ሳ​ቸ​ውም።
አዳ​ምና ሔዋን ከገ​ነት እንደ ወጡ
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “እነሆ፥ አዳም መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለማ​ወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁ​ንም እጁን እን​ዳ​ይ​ዘ​ረጋ፥ ደግ​ሞም ከሕ​ይ​ወት ዛፍ ወስዶ እን​ዳ​ይ​በላ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ሆኖ እን​ዳ​ይ​ኖር፥” 23ስለ​ዚህ የተ​ገ​ኘ​ባ​ትን መሬት ያርስ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ደስታ ከሚ​ገ​ኝ​ባት ገነት#ዕብ. “ኤደን ገነት” ይላል። አስ​ወ​ጣው። 24አዳ​ም​ንም አስ​ወ​ጣው፤ ደስታ በሚ​ገ​ኝ​ባት በገ​ነት አን​ጻ​ርም አኖ​ረው፤ ወደ ሕይ​ወት ዛፍ የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም መን​ገድ ለመ​ጠ​በቅ የም​ት​ገ​ለ​ባ​በጥ የነ​በ​ል​ባል ሰይ​ፍን በእ​ጃ​ቸው የያዙ ኪሩ​ቤ​ልን#ዕብ. “ኪሩ​ቤ​ል​ንና ሰይ​ፍን በኤ​ደን ምሥ​ራቅ አስ​ቀ​መጠ” ይላል። አዘ​ዛ​ቸው።

Highlight

Kongsi

Salin

None

Ingin menyimpan sorotan merentas semua peranti anda? Mendaftar atau log masuk