1
የሉቃስ ወንጌል 22:42
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“አባት ሆይ! ፈቃድህ ቢሆን ይህን የመከራ ጽዋ ከእኔ አርቅልኝ፤ ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን።”
ႏွိုင္းယွဥ္
የሉቃስ ወንጌል 22:42ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
2
የሉቃስ ወንጌል 22:32
ነገር ግን የአንተ እምነት እንዳይጠፋ እኔ ለአንተ እጸልያለሁ፤ እንደገና በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና።”
የሉቃስ ወንጌል 22:32ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
3
የሉቃስ ወንጌል 22:19
ቀጥሎም ኢየሱስ ኅብስት አንሥቶ ከአመሰገነ በኋላ፤ ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ “እንካችሁ፤ ይህ ለእናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሎ ሰጣቸው።
የሉቃስ ወንጌል 22:19ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
4
የሉቃስ ወንጌል 22:20
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ ሰጣቸውና እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚፈጸም አዲስ ኪዳን ነው።
የሉቃስ ወንጌል 22:20ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
5
የሉቃስ ወንጌል 22:44
ልቡም በጣም ተጨንቆ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ሆኖ ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።
የሉቃስ ወንጌል 22:44ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
6
የሉቃስ ወንጌል 22:26
እናንተ ግን እንደ እነርሱ ልትሆኑ አይገባም፤ ይልቅስ ከእናንተ መካከል ትልቅ የሆነ እንደ ትንሽ ይሁን፤ አለቃ የሆነም እንደ አገልጋይ ይሁን።
የሉቃስ ወንጌል 22:26ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
7
የሉቃስ ወንጌል 22:34
ኢየሱስ ግን “ጴጥሮስ ሆይ! ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ‘አላውቀውም’ ብለህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እልሃለሁ” አለው።
የሉቃስ ወንጌል 22:34ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
ပင္မစာမ်က္ႏွာ
သမၼာက်မ္းစာ
အစီအစဥ္မ်ား
ဗီဒီယိုမ်ား