YouVersion လိုဂို
ရွာရန္ အိုင္ကြန္

ኦሪት ዘፍጥረት 5

5
የአዳም ትውልድ
1 # ዘፍ. 1፥27፤28። የአዳም የዘር ሐረግ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ በእግዚአብሔር አምሳያ አደረገው፤ 2#ማቴ. 19፥4፤ ማር. 10፥6።ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው። 3አዳምም መቶ ሠላሳ ዓመት ሲኖር፥ እሱን የሚመስል፥ አምሳያው የሆነ፥ የልጅ አባት ሆነ፤ ሤት ብሎም ስም አወጣለት። 4ሤትንም ከወለደ በኋላ አዳም ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 5አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
6ሤትም አንድ መቶ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሄኖስንም ወለደ፤ 7ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት ስምንት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 8ሤትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
9ሄኖስም ዘጠና ዓመት ሲሆነው፥ ቃይናንንም ወለደ፥ 10ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 11ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
12ቃይናንም ሰባ ዓመት ሲሆነው፥ መላልኤልን ወለደ፥ 13ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 14ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
15መላልኤልም ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ያሬድንም ወለደ፥ 16መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 17መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
18ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሄኖክንም ወለደ፥ 19ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 20ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
21ሄኖክም ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ማቱሳላንም ወለደ፥ 22ከዚህ በኋላ ሔኖክ ማቱሳለን ወለደ፥ የእግዚአብሔርንም መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤። 23ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። 24#ሲራ. 44፥16፤ 49፥14፤ ዕብ. 11፥5፤ ይሁዳ 1፥14።አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ፥ እግዚአብሔር ወስዶታልና፥ ሄኖክ አልተገኘም።
25ማቱሳላም መቶ ሰማኒያ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ላሜሕንም ወለደ፤ 26ላሜሕን ከወለደ በኋላ ማቱሳላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 27ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
28ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ወንድ ልጅም ወለደ። 29ስሙንም፥ “ጌታ በረገማት ምድር፥ ከሥራችን እና ከእጅ ድካማችን፥ ይህ ያሳርፈናል” ሲል፥ ኖኅ ብሎ ጠራው። 30ኖኅንም ከወለደ በኋላ ላሜሕ አምስት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። 31ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ዓመት ሆነ፥ ሞተም።
32ኖኅም ሴምን፥ ካምን እና ያፌትን ወለደ፤ ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ።

လက္ရွိေရြးခ်ယ္ထားမွု

ኦሪት ዘፍጥረት 5: መቅካእኤ

အေရာင္မွတ္ခ်က္

မၽွေဝရန္

ကူးယူ

None

မိမိစက္ကိရိယာအားလုံးတြင္ မိမိအေရာင္ခ်ယ္ေသာအရာမ်ားကို သိမ္းဆည္းထားလိုပါသလား။ စာရင္းသြင္းပါ (သို႔) အေကာင့္ဝင္လိုက္ပါ