1
ዮሐንስ 6:35
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔም የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም።
Comparar
Explorar ዮሐንስ 6:35
2
ዮሐንስ 6:63
መንፈስ ሕይወትን ይሰጣል፤ ሥጋ ግን ምንም አይጠቅምም። እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስም ሕይወትም ነው፤
Explorar ዮሐንስ 6:63
3
ዮሐንስ 6:27
ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በእርሱ ላይ ዐትሟልና።”
Explorar ዮሐንስ 6:27
4
ዮሐንስ 6:40
የአባቴ ፈቃድ ወልድን አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”
Explorar ዮሐንስ 6:40
5
ዮሐንስ 6:29
ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው።
Explorar ዮሐንስ 6:29
6
ዮሐንስ 6:37
አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤
Explorar ዮሐንስ 6:37
7
ዮሐንስ 6:68
ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤
Explorar ዮሐንስ 6:68
8
ዮሐንስ 6:51
ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው።”
Explorar ዮሐንስ 6:51
9
ዮሐንስ 6:44
የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ማንም ወደ እኔ መምጣት አይችልም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
Explorar ዮሐንስ 6:44
10
ዮሐንስ 6:33
የእግዚአብሔር እንጀራ እርሱ ከሰማይ የሚወርድ፣ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና።”
Explorar ዮሐንስ 6:33
11
ዮሐንስ 6:48
የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።
Explorar ዮሐንስ 6:48
12
ዮሐንስ 6:11-12
ኢየሱስ አምስቱን እንጀራ አንሥቶ አመሰገነ፤ ለተቀመጡትም የሚፈልጉትን ያህል ዐደለ፤ ዓሣውንም እንዲሁ። ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ከተረፈው ቍርስራሽ ምንም እንዳይባክን ሰብስቡ” አላቸው።
Explorar ዮሐንስ 6:11-12
13
ዮሐንስ 6:19-20
አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲመጣ አይተው ደነገጡ። እርሱ ግን፣ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።
Explorar ዮሐንስ 6:19-20
Início
Bíblia
Planos
Vídeos