Logótipo YouVersion
Ícone de pesquisa

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 2

2
1ሰማ​ይና ምድር ዓለ​ማ​ቸ​ውም ሁሉ ተፈ​ጸሙ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሠ​ራ​ውን ሥራ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሠ​ራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰባ​ተ​ኛ​ዋን ቀን ባረ​ካት፤ ቀደ​ሳ​ትም፤ ሊፈ​ጥ​ረው ከጀ​መ​ረው ሥራ ሁሉ በእ​ር​ስዋ ዐር​ፎ​አ​ልና።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን፥ በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ፍጥ​ረት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰ​ማ​ይና የም​ድር የል​ደት መጽ​ሐፍ ነው” ይላል። ይህ ነው። 5የሜዳ ቍጥ​ቋጦ ሁሉ በም​ድር ላይ ከመ​ኖሩ በፊት፥ የሜ​ዳ​ውም ቡቃያ ሁሉ ከመ​ብ​ቀሉ በፊት፥ አዳ​ምም ከመ​ፈ​ጠሩ በፊት፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አዳም ከመ​ፈ​ጠሩ በፊት” አይ​ልም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በም​ድር ላይ አላ​ዘ​ነ​በም ነበር፤ ምድ​ር​ንም የሚ​ሠ​ራ​ባት ሰው አል​ነ​በ​ረም። 6ነገር ግን የውኃ ምንጭ ከም​ድር ይወጣ ነበር፤ የም​ድ​ር​ንም ፊት ሁሉ ያጠጣ ነበር። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ከም​ድር አፈር ፈጠ​ረው፤ በፊ​ቱም የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋ​ስን እፍ አለ​በት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
አዳም በኤ​ዶም ገነት
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በኤ​ዶም በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ ገነ​ትን ተከለ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም ሰው በዚያ አኖ​ረው። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ። 10ወን​ዝም ገነ​ትን ያጠጣ ዘንድ ከኤ​ዶም#በግ​እዙ “ኤዶም” አይ​ልም። ይወጣ ነበር፤ ከዚ​ያም ለዐ​ራት መዓ​ዝን ይከ​ፈል ነበር። 11የአ​ን​ደ​ኛው ወንዝ ስም ኤፌ​ሶን#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. “ፊሶን” ይላል። ነው፤ እር​ሱም ወርቅ የሚ​ገ​ኝ​በ​ትን የኤ​ው​ላጥ ምድ​ርን ይከ​ብ​ባል። 12የዚ​ያ​ችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው። 13በዚ​ያም የሚ​ያ​በራ ዕን​ቍና የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ አለ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እር​ሱም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምድር ሁሉ ይከ​ብ​ባል፤ 14የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ጤግ​ሮስ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሶር ላይ የሚ​ሄድ ነው። አራ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ኤፍ​ራ​ጥስ ነው። 15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ወስዶ ያበ​ጃ​ትም፥ ይጠ​ብ​ቃ​ትም ዘንድ በኤ​ዶም ገነት አኖ​ረው። 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አዳ​ምን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤ 17ነገር ግን መል​ካ​ም​ንና ክፉን ከሚ​ያ​ሳ​የ​ውና ከሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀው ዛፍ አት​ብላ፤ ከእ​ርሱ በበ​ላህ ቀን ሞትን ትሞ​ታ​ለ​ህና።”
18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “ሰው ብቻ​ውን ይኖር ዘንድ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ረ​ዳ​ውን ጓደኛ እን​ፍ​ጠ​ር​ለት እንጂ።” 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንና የሰ​ማይ ወፎ​ችን ሁሉ ደግሞ ከም​ድር ፈጠረ፤ በምን ስም እን​ደ​ሚ​ጠ​ራ​ቸ​ውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመ​ጣ​ቸው፤ አዳ​ምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እን​ደ​ጠ​ራው ስሙ ያው ሆነ። 20አዳ​ምም ለእ​ን​ስ​ሳት ሁሉ፥ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም ሁሉ፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ ስም አወ​ጣ​ላ​ቸው። ነገር ግን ለአ​ዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አል​ተ​ገ​ኘ​ለ​ትም ነበር። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በአ​ዳም ላይ እን​ቅ​ል​ፍን አመጣ፤ አን​ቀ​ላ​ፋም ፤ ከጎ​ኑም አጥ​ን​ቶች አንድ አጥ​ን​ትን ወስዶ ስፍ​ራ​ውን በሥጋ መላው። 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም#ምዕ. 2 ቁ. 4፥ 5፥ 6፥ 7፥ 8፥ 9፥ 10፥ 15፥ 16 ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ” ሲሉ፤ ግእዙ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብቻ ይላል። ከአ​ዳም የወ​ሰ​ዳ​ትን አጥ​ንት ሴት አድ​ርጎ ሠራት፤ ወደ አዳ​ምም አመ​ጣት። 23ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥ​ንት ከአ​ጥ​ንቴ ናት፤ ሥጋ​ዋም ከሥ​ጋዬ ናት፤ እር​ስዋ ከባ​ልዋ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሚስት ትሁ​ነኝ።”#በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “እር​ስዋ ከወ​ንድ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሴት ትባል” ይላል። 24ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ። 25አዳ​ምና ሚስ​ቱም ዕራ​ቁ​ታ​ቸ​ውን ነበሩ፤ አይ​ተ​ፋ​ፈ​ሩም ነበር።

Destaque

Partilhar

Copiar

None

Quer salvar os seus destaques em todos os seus dispositivos? Faça o seu registo ou inicie sessão