ኦሪት ዘፍጥረት 2
2
1ሰማያትና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ እነሆ ተፈጸሙ። 2#ዘፀ. 20፥11፤ ዕብ. 4፥4፤10።እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። 3እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና፥ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም።
የኤደን ገነት እና የነፃ ፈቃድ ፈተና
4ጌታ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን፥ የሰማያትና ምድር ልደት፥ በተፈጠሩበት ጊዜ፥ እንዲህ ነበር። 5የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ ጌታ እግዚአብሔር በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም። 6ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር። 7#ጥበ. 15፥8፤11፤ 1ቆሮ. 15፥45።ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
8ጌታ እግዚአብሔርም፥ በስተ ምሥራቅ፥ በዔድን ገነትን ተከለ፤ የፈጠረውንም ሰው ከዚያ አኖረው። 9#ራእ. 2፥7፤ 22፥2፤14።በዚያም፥ ጌታ እግዚአብሔር ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፥ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። 10ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፥ ይህም ወንዝ ከዔደን ከወጣ በኋላ በአራት ወንዞች ይከፈላል። 11የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፥ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የሐዊላን ምድር ይከብባል፥ 12የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፥ ሉልና የከበረም ድንጋይ በዚያ ይገኛል። 13የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፥ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል። 14የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፥ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። 15ጌታ እግዚአብሔርም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔደን ገነት አኖረው። 16ከዚያም ጌታ እግዚአብሔር ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤ 17ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፥ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
18ጌታ እግዚእብሔርም፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ የምትሆነውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ። 19የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፥ ጌታ እግዚአብሔር፥ ከምድር ፈጠረ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፥ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ። 20አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፥ ነገር ግን አዳም ለእርሱ ሁነኛ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21ጌታ እግዚአብሔርም አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጎኑ አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። 22ከአዳም የወሰዳትንም አጥንት፥ ጌታ እግዚእብሔር፥ ሴት አድርጎ ሠራት፥ ወደ አዳምም አመጣለት። 23አዳምም አለ፥
“ይህች አጥንት ከአጥንቴ የተገኘች ናት፥
ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤
ሴት ተብላ ትጠራ፥
ከወንድ#2፥23 በዕብራይስጥ “ኢሽ” ማለት ወንድ ሲሆን “ኢሻ” ደግሞ ሴት ማለት ነው። የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።
24 #
ማቴ. 19፥5፤ ማር. 10፥7፤8፤ 1ቆሮ. 6፥16፤ ኤፌ. 5፥31። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ። 25አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩምም ነበር።
Atualmente Selecionado:
ኦሪት ዘፍጥረት 2: መቅካእኤ
Destaque
Compartilhar
Copiar
Quer salvar seus destaques em todos os seus dispositivos? Cadastre-se ou faça o login

: