የዮሐንስ ወንጌል 4
4
ወደ ገሊላ ስለ መሄዱ
1ጌታችን ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርትን እንደ አበዛና እንደሚያጠምቅ ፈሪሳውያን መስማታቸውን ዐወቀ። 2ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ አላጠመቀም። 3የይሁዳንም ምድር ትቶ ዳግመኛ ወደ ገሊላ ሄደ። 4በሰማርያ በኩልም ሲያልፍ ሳለ፥ 5#ዘፍ. 33፥19፤ ኢያ. 24፥32። ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው በወይን ቦታ አቅራቢያ ወደ አለችው ሲካር ወደምትባለው የሰማርያ ከተማ ደረሰ። 6በዚያም የያዕቆብ የውኃ ጕድጓድ ነበረ። ጌታችን ኢየሱስም መንገድ በመሄድ ደክሞ በዚያ ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበር።
ስለ ሳምራዊት ሴት
7እነሆ፥ ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “ውኃ አጠጪኝ” አላት። 8ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና። 9#ዕዝ. 4፥1-5፤ ነህ. 4፥12። ያቺ የሰማርያ ሴትም፥ “አንተ አይሁዳዊ ስትሆን፥ እኔም ሳምራዊት ስሆን እንዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልትጠጣ ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር በሥርዐት#“በሥርዐት” የሚለው በግሪኩ የለም። አይተባበሩም ነበርና። 10ጌታችን ኢየሱስም፥ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጪኝ#በግሪኩ “ውኃ ስጪኝ” ይላል። ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂስ አንቺ ደግሞ በለመንሺው ነበር፤ እርሱም የሕይወትን ውኃ በሰጠሽ ነበር” ብሎ መለሰላት። 11ያቺ ሴትም እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለህም፤ ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? 12ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ አንተ ትበልጣለህን? እርሱም #አንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “ሚስቶቹም” የሚል ይጨምራል። ልጆቹም፥ ከብቶቹም ከእርሱ ጠጥተዋል።” 13ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፥ “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ዳግመኛ ይጠማል። 14እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።” 15ሴቲቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እንዳልጠማ፥ ዳግመኛም ውኃ ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ እባክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለችው።
16ጌታችን ኢየሱስም፥ “ሂደሽ ባልሽን ጥሪና ወደዚህ ነይ” አላት። 17ሴቲቱም፥ “ባል የለኝም” ብላ መለሰችለት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላት፥ “ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ። 18ቀድሞ አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ ዛሬ አብሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይደለም፤ ይህንስ እውነት አልሽ።” 19ሴቲቱም እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ። 20አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ይሰግዱበት ዘንድ የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ።” 21ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ብቻ ለአብ የማይሰግዱበት ሰዓት እንደምትመጣ እመኝኝ። 22እናንተ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ለምናውቀው እንሰግዳለን፤ መድኀኒት ከአይሁድ ወገን ነውና። 23ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ በመንፈስና በእውነት ለአብ የሚሰግዱባት ጊዜ ትመጣለች፤ እርስዋም አሁን ናት። አብ እንዲህ የሚሰግዱለትን ይሻልና። 24እግዚአብሔር መንፈስ ነውና፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ይሰግዱለት ዘንድ ይገባል።” 25ሴቲቱም፥ “ክርስቶስ የሚሉት መሲሕ እንደሚመጣ እናውቃለን፤ እርሱም በሚመጣ ጊዜ ሁሉን ይነግረናል” አለችው። 26ጌታችን ኢየሱስም፥ “የማነጋግርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት።
27በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነጋገር ነበርና ተደነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻለህ? ወይስ ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?” ያለው የለም። 28ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ገባች፤ ለሰዎችም ነገረች። 29“የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክርስቶስ ይሆን?” 30ከከተማም ወጥተው ወደ እርሱ ሄዱ።
31በዚህም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ፥ “መምህር ሆይ፥ እህል ብላ” ብለው ለመኑት። 32ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔ የምበላው እናንተ የማታውቁት ምግብ አለኝ” አላቸው። 33ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው፥ “አንዳች የሚበላው ምግብ ያመጣለት ሰው ይኖር ይሆን?”#አንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “... ወሚመ ዛቲ ብእሲት” የሚል ይጨምራል። ተባባሉ። 34ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው። 35እናንተ እስከ አራት ወር ድረስ መከር ይሆናል የምትሉ አይደለምን? እነሆ፥ እላችኋለሁ፤ ዐይናችሁን አንሡ፤ መከሩም ሊደርስ እንደ ገረጣ ምድሩን ተመልከቱ። 36አጫጅም ዋጋውን ያገኛል፤ የሚዘራና የሚያጭድም በአንድነት ደስ እንዲላቸው ለዘለዓለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል። 37አንዱ ይዘራል፥ ሌላውም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአል። 38እኔም ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ ሌሎች ደከሙ፤ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ።”
ስለ ሳምራውያን
39“የሠራሁትን ሁሉ ነገረኝ” ብላ የመሰከረችው ሴት ስለ ነገረቻቸውም ከዚያች ከሰማርያ ከተማ ብዙዎች አመኑበት። 40ሳምራውያንም ሁሉ ወደ እርሱ መጥተው በእነርሱ ዘንድ እንዲኖር ማለዱት፤ ሁለት ቀንም ያህል በዚያ ተቀመጠ። 41ስለ ቃሉም እጅግ ብዙዎች አመኑበት። 42ሴቲቱንም፥ “እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለም መድኀኒት ክርስቶስ እንደ ሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ በአንቺ ቃል ያመንበት አይደለም” አሏት።
ገሊላውያን እንደ ተቀበሉት።
43ከሁለት ቀንም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ። 44#ማቴ. 13፥57፤ ማር. 6፥4፤ ሉቃ. 4፥24። ነቢይ በገዛ ሀገሩ እንደማይከብር እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ መሰከረ። 45#ዮሐ. 2፥23። ወደ ገሊላም ደግሞ በገባ ጊዜ ገሊላውያን ሁሉ ተቀበሉት፤ እነርሱ ለበዓል ሄደው ስለ ነበር በበዓሉ ቀን በኢየሩሳሌም ያደረገውን ተአምር አይተው ነበርና።
46 #
ዮሐ. 2፥1-11። ጌታችን ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወደ አደረገበት የገሊላ ክፍል ወደምትሆን ወደ ቃና ዳግመኛ ሄደ። በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት የንጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ 47እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበርና ወርዶ ልጁን ያድንለት ዘንድ ለመነው፤ 48ጌታችን ኢየሱስም፥ “ምልክትንና ድንቅ ሥራን ካላያችሁ አታምኑም” አለው። 49ያም የንጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይሞት ፈጥነህ ውረድ” አለው። 50ጌታችን ኢየሱስም፥ “ሂድ፤ ልጅህስ ድኖአል” አለው፤ ያም ሰው፦ ጌታችን ኢየሱስ በነገረው ቃል አምኖ ሄደ። 51ሲወርድም አገልጋዮቹ ተቀበሉትና፥ “ልጅህስ ድኖአል” ብለው ነገሩት። 52የዳነባትን ሰዓቷንም ጠየቃቸው፤ “ትናንትና በሰባት ሰዓት ንዳዱ ተወው” አሉት። 53አባቱም፥ ጌታችን ኢየሱስ፥ “ልጅህ ድኖአል” ባለበት ሰዓት እንደ ሆነች ዐወቀ፤ እርሱም፥ ቤተ ሰቦቹም ሁሉ አመኑ። 54ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደረገው ሁለተኛው ተአምር ይህ ነው።
Atualmente Selecionado:
የዮሐንስ ወንጌል 4: አማ2000
Destaque
Compartilhar
Copiar
Quer salvar seus destaques em todos os seus dispositivos? Cadastre-se ou faça o login

: