1
ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፥ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፥ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
Porovnať
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:26-27
2
ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፥ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:28
3
ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:1
4
ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:2
5
ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:3
6
ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:31
7
ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:4
8
ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
እግዚአብሔርም አለ፦ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፥
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:29
9
ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንደኛ ቀን።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:5
10
ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:6
11
ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፥” እንዲሁም ሆነ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:30
12
ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:14
13
ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:11
14
ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፥ እንዲሁም ሆነ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:7
15
ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:12
16
ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:16
17
ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:9-10
18
ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:22
19
ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:24
20
ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።”
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
21
ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
Preskúmať ኦሪት ዘፍጥረት 1:25
Domov
Biblia
Plány
Videá