ኦሪት ዘፍጥረት 6
6
1እንዲህም ሆነ ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው 2የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ። 3እግዚአብሔርም፤ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ። 4በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኂያላን ሆኑ።
5እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፤ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንድ ሆነ አየ። 6እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም አዘነ። 7እግዚአብሔርም፤ የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ስለ ፈጠርኍቸው ተጸጽቼእለሁና አለ። 8ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ። 9የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው። ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ስው ነበረ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረግ። 10ኖኅም ሦስት ልጆችን ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ። 11ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸ ምድርም ግፍን ተሞላች። 12እግዚአብሔርም ምድርን አየ፤ እነሆም ተበላሸች ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና።
13እግዚእብሔርም ኖኅን አለው፤ የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችን እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። 14ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድርግ በውስጥን በውጭም በቅጥራን ለቅልቃት። 15እርስዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፤ ወርድዋ አምሳ ክንድ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። 16ለመርከቢቱ መስኮትን ታድርጋለህ ከቁመትዋም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨርሳት የመርከቢቱንም በር በጎንዋ አድርግ ታችኛውንም ሁለተኛውንም ሦስተኛውንም ደርብ ታደርግላታለህ። 17እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኂን አመጣለሁ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል። 18ቃል ኪዳኔም ከአንተ ጋር አቆማለሁ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ። 19ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለር እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ ተባትና እንስት ይሁን። 20ከወፍ እንደ ወገኑ ከእንስሳም እንደ ወገኑ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንድ ወገኑ በሕይውር ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆን ወደ አንተ ይግቡ። 21ከሚበላውም መብል ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተም ትሰበስባለህ እርሱም ለአንተም ለእነርሱም መብል ይሆናል። 22ኖኅም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ።
Aktuálne označené:
ኦሪት ዘፍጥረት 6: አማ54
Zvýraznenie
Zdieľať
Kopírovať
Chceš mať svoje zvýraznenia uložené vo všetkých zariadeniach? Zaregistruj sa alebo sa prihlás

: