የሉቃስ ወንጌል 19
19
ኢየሱስና ዘኬዎስ
1ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ከተማ ገብቶ በዚያ በኩል አልፎ እየሄደ ነበር። 2በዚያም አንድ የቀራጮች አለቃ ዘኬዎስ የሚባል ሀብታም ሰው ነበረ። 3እርሱ ኢየሱስ የቱ እንደ ሆነ ለማየት ይፈልግ ነበር፤ ነገር ግን ቁመቱ አጭር በመሆኑ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሊያየው አልቻለም። 4ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ዘኬዎስ እርሱን ለማየት ብሎ ከሕዝቡ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። 5ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ ቀና ብሎ ተመለከተና ዘኬዎስን፥ “ዘኬዎስ ሆይ! ዛሬ በአንተ ቤት መዋል ይገባኛልና ፈጥነህ ከዛፉ ውረድ” አለው። 6ዘኬዎስም ቶሎ ብሎ ወረደና፥ በደስታ ኢየሱስን በቤቱ ተቀበለው። 7ይህን የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ “ይህ ሰው ወደ ኃጢአተኛ ቤት ሊጋበዝ ገባ!” ብለው በኢየሱስ ላይ አጒረመረሙ።
8ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”
9ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “ይህ ሰው ደግሞ የአብርሃም ዘር ነውና ዛሬ መዳን ለዚህ ቤት ሆኖአል፤ 10የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው።” #ማቴ. 18፥11።
የዐሥሩ አገልጋዮች ምሳሌ
(ማቴ. 25፥14-30)
11ሰዎቹ ይህን በመስማት ላይ ሳሉ ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ደግሞ ነገራቸው፤ እርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ ተቃረበ ሰዎቹ የእግዚአብሔር መንግሥት አሁኑኑ የምትገለጥ መስሎአቸው ነበር። #ማቴ. 25፥14-30። 12ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የንጉሥነትን ሥልጣን ተቀብሎ ለመመለስ ወደ ሩቅ አገር የሄደ አንድ መኰንን ነበረ፤ 13እርሱ ከመሄዱ በፊት ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ጠርቶ ለእያንዳንዱ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና ‘ተመልሼ እስክመጣ ድረስ በዚህ ገንዘብ ነግዱ’ አላቸው። #19፥13 ምናን፦ የክብደት መለኪያ እንዲሁም ገንዘብ ሲሆን የዚህ ገንዘብ የመገበያያ መጠን አንዱ ምናን ለአንድ የቀን ሠራተኛ የሦስት ወር ደመወዝ ያኽል ነው። 14የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለ ነበር፥ ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም ሲሉ እርሱ ከሄደ በኋላ መልእክተኛ ላኩ።
15“ያ ሰው ንጉሥ ሆኖ በተመለሰ ጊዜ በተሰጣቸው ገንዘብ ነግደው ምን ያኽል እንዳተረፉ ለማወቅ፥ ገንዘብ ሰጥቶአቸው የነበሩትን አገልጋዮቹን አስጠራቸው። 16የመጀመሪያው አገልጋይ ቀርቦ፦ ‘ጌታ ሆይ! የሰጠኸኝ አንድ ምናን እነሆ፥ ዐሥር ምናን አትርፎአል’ አለው። 17ጌታውም ‘አንተ መልካም አገልጋይ! ደግ አደረግህ፤ በትንሽ ነገር ስለ ታመንህ እኔ ደግሞ በዐሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ’ አለው። 18ሁለተኛውም አገልጋይ ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! የሰጠኸኝ ምናን እነሆ! አምስት ምናን አትርፎአል’ አለው። 19ጌታውም ይህኛውን ‘አንተንም ደግሞ በአምስት ከተሞች ላይ ሾሜሃለሁ’ አለው።
20“ሌላውም አገልጋይ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ ‘ጌታዬ ሆይ! የሰጠኸኝ ገንዘብ ይኸውልህ፤ በጨርቅ ቋጥሬ አስቀምጬው ነበር። 21ይህንንም ያደረግኹት አንተ ያላስቀመጥከውን የምትወስድ፥ ያልዘራኸውንም የምትሰበስብ፥ ኀይለኛ ሰው መሆንህን ዐውቄ ስለ ፈራሁህ ነው’ አለው። 22ጌታውም ‘አንተ መጥፎ አገልጋይ! በአነጋገርህ እፈርድብሃለሁ፤ እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የምሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆኔን ዐውቀሃል፤ 23ታዲያ ገንዘቤን ትርፍ በሚያስገኝልኝ በባንክ ለምን አላስቀመጥከውም ነበር? እኔ ተመልሼ ስመጣ ከነትርፉ እወስደው ነበር’ አለው። 24ከዚህ በኋላ ጌትዮው፥ በዚያ ቆመው የነበሩትን፦ ‘ምናኑን ከእርሱ ወስዳችሁ ዐሥር ምናን ላለው አገልጋይ ስጡት’ አላቸው። 25እነርሱም ‘ጌታ ሆይ! እርሱ እኮ ዐሥር ምናን አለው!’ አሉት። 26ጌትዮውም ‘ላለው ሁሉ ይበልጥ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል እላችኋለሁ። #ማቴ. 13፥12፤ ማር. 4፥25፤ ሉቃ. 8፥18። 27በእነርሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ግን እዚህ አምጥታችሁ በፊቴ ግደሉአቸው!’ ” አላቸው። 28ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ ጒዞውን ወደ ኢየሩሳሌም በመቀጠል፥ ከደቀ መዛሙርቱ ፊት ፊት ይሄድ ነበር።
የኢየሱስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም መግባት
(ማቴ. 21፥1-11፤ ማር. 11፥1-11፤ ዮሐ. 12፥12-19)
29ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወደሚገኙት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤ 30“በፊታችሁ ወደምትገኘው መንደር ሂዱ፤ እዚያም በደረሳችሁ ጊዜ ገና ማንም ሰው ያልተቀመጠበትን የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ ወዲህ አምጡት። 31ማንም ሰው ‘ለምን ትፈቱታላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ ‘ጌታ ስለሚያስፈልገው ነው’ ብላችሁ መልሱለት።”
32የተላኩትም ሄደው ሁሉም ነገር ልክ ኢየሱስ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት። 33ውርንጫውን በሚፈቱበት ጊዜ ባለቤቶቹ፦ “ስለምን ትፈቱታላችሁ?” አሉአቸው። 34እነርሱም “ለጌታ ስለሚያስፈልገው ነው” አሉ። 35ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ልብሳቸውንም በውርንጫው ጀርባ ላይ አንጥፈው ኢየሱስ እንዲቀመጥበት አደረጉ። 36ኢየሱስ ሲሄድ ሳለ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገዱ ላይ ያነጥፉለት ነበር።
37ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሊደርስ በተቃረበ ጊዜ የደብረ ዘይትን ተራራ ቊልቊል በመውረድ ላይ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ኢየሱስን ይከተሉት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ስላዩአቸው ተአምራት በደስታ ተሞልተው ስለ ነበር ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመሩ። 38እንዲህ ይሉም ነበር፤ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው! ሰላም በሰማይ፥ ክብርም ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን!” #መዝ. 118፥26።
39በሕዝቡ መካከል የነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን “መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ዝም አሰኛቸው!” አሉት።
40ኢየሱስም “እነርሱ እንኳ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ እላችኋለሁ” ሲል መለሰላቸው።
ኢየሱስ ለኢየሩሳሌም ከተማ ማልቀሱ
41ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ቀርቦ፥ ከተማይቱን በተመለከተ ጊዜ፥ አለቀሰላት። 42እንዲህም አለ፤ “አንቺ ለሰላምሽ የሚያስፈልገውን ነገር ምነው ዛሬ ዐውቀሽ ቢሆን ኖሮ! አሁን ግን ይህ ነገር ከዐይንሽ ተሰውሮብሻል፤ 43ጠላቶችሽ በዙሪያሽ ዐጥር ዐጥረውና ከበው፥ በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ቀን ይመጣል። 44አንቺንና በውስጥሽ ያሉትንም ልጆችሽን በመሬት ላይ ጥለው ያወድማሉ፤ ሳይፈርስ የሚቀር አንድ ድንጋይ እንኳ በቦታው አይተዉልሽም፤ ይህም የሚሆነው፥ እግዚአብሔር አንቺን ሊያድን የመጣበትን ጊዜ ባለማወቅሽ ነው።”
ኢየሱስ በቤተ መቅደስ የሚገበያዩትን ማስወጣቱ
(ማቴ. 21፥12-17፤ ማር. 11፥15-19፤ ዮሐ. 2፥13-22)
45ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፥ በዚያ የሚገበያዩትን ሰዎች ማባረር ጀመረ፤ 46እንዲህም አላቸው፦ “ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት።” #ኢሳ. 56፥7፤ ኤር. 7፥11።
47ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር፤ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን፥ ሌሎችም የሕዝብ መሪዎች ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር። #ሉቃ. 21፥37። 48ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት በመፈለግ ልባቸው ተማርኮ ስለ ነበረ ሊገድሉት የፈለጉት ወገኖች ምንም ማድረግ አልቻሉም።
தற்சமயம் தேர்ந்தெடுக்கப்பட்டது:
የሉቃስ ወንጌል 19: አማ05
சிறப்புக்கூறு
பகிர்
நகல்
உங்கள் எல்லா சாதனங்களிலும் உங்கள் சிறப்பம்சங்கள் சேமிக்கப்பட வேண்டுமா? பதிவு செய்யவும் அல்லது உள்நுழையவும்
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: