የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 11

11
ስለ አል​ዓ​ዛር
1የማ​ር​ያ​ምና የእ​ኅቷ የማ​ርታ መን​ደር በሚ​ሆን በቢ​ታ​ንያ ስሙ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል የታ​መመ አንድ ሰው ነበር። 2ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር። 3እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ። 4ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሰምቶ እን​ዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይ​ደ​ለም።”
5ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ማር​ታ​ንና እኅ​ቷን ማር​ያ​ምን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ይወ​ዳ​ቸው ነበር። 6እንደ ታመመ በሰማ ጊዜM በነ​በ​ረ​በት ቦታ ሁለት ቀን ቈየ። 7ከዚ​ህም በኋላ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን፥ “ኑ፥ ወደ ይሁዳ ሀገር ደግሞ እን​ሂድ” አላ​ቸው። 8ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ አይ​ሁድ ሊወ​ግ​ሩህ ይሹ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ዛሬ ደግሞ አንተ ወደ​ዚያ ልት​ሄድ ትሻ​ለ​ህን?” አሉት። 9ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይ​ደ​ለ​ምን? በቀን የሚ​ሄድ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ የዚ​ህን ዓለም ብር​ሃን ያያ​ልና። 10በሌ​ሊት የሚ​ሄድ ግን ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል፤ በው​ስጡ የሚ​ያ​የው ብር​ሃን የለ​ምና።” 11ይህ​ንም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ#“ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ነገ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ህም በኋላ፥ “ወዳ​ጃ​ችን አል​ዓ​ዛር ተኝ​ቶ​አል፤ ነገር ግን ላነ​ቃው እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው። 12ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “አቤቱ፥ ከተ​ኛስ ይነ​ቃል፤#“ይነ​ቃል” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ይድ​ና​ልም” አሉት። 13ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስለ ሞቱ ተና​ገረ፤ እነ​ርሱ ግን ስለ እን​ቅ​ልፍ መተ​ኛት መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር። 14ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ገልጦ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አል​ዓ​ዛር ሞተ። 15ታም​ኑም ዘንድ እኔ በዚያ ባለ​መ​ኖሬ ስለ እና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤ ነገር ግን ኑ፥ ወደ እርሱ እን​ሂድ።” 16ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማ​ስም፥ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን ደቀ መዛ​ሙ​ርት፥ “እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ሞት ዘንድ እን​ሂድ” አላ​ቸው።
ጌታ​ችን አል​ዓ​ዛ​ርን ስለ ማስ​ነ​ሣቱ
17ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ቢታ​ንያ ሄደ፤#“ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ቢታ​ንያ ሄደ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ከዚ​ያም በደ​ረሰ ጊዜ ከተ​ቀ​በረ አራት ቀን ሆኖት አገ​ኘው። 18ቢታ​ን​ያም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ አም​ስት ምዕ​ራፍ ያህል ቅርብ ነበ​ረች። 19ከአ​ይ​ሁ​ድም ስለ ወን​ድ​ማ​ቸው ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አ​ቸው ወደ ማር​ያ​ምና ወደ ማርታ የሄዱ ብዙ​ዎች ነበሩ። 20ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ መጣ በሰ​ማች ጊዜ ወጥታ ተቀ​በ​ለ​ችው፤ ማር​ያም ግን በቤት ተቀ​ምጣ ነበር። 21ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር። 22አሁ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ለ​ም​ነ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ሰ​ጥህ አው​ቃ​ለሁ።” 23ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ወን​ድ​ም​ሽስ ይነ​ሣል” አላት። 24ማር​ታም፥ “ሙታን በሚ​ነ​ሡ​ባት በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን እን​ደ​ሚ​ነሣ አው​ቃ​ለሁ” አለ​ችው።
ክር​ስ​ቶስ ትን​ሣ​ኤና ሕይ​ወት ስለ መሆኑ
25ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላት፥ “ትን​ሣ​ኤና ሕይ​ወት እኔ ነኝ፤ የሚ​ያ​ም​ን​ብኝ ቢሞ​ትም ይነ​ሣል። 26ሕያው የሆነ የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ሞ​ትም፤ ይህ​ንስ ታም​ኛ​ለ​ሽን?” 27እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ እኔ አም​ና​ለሁ” አለ​ችው።
ጌታ​ችን ለአ​ል​ዓ​ዛር ስለ ማል​ቀሱ
28ይህ​ንም ብላ ሄደች፤ እኅ​ቷን ማር​ያ​ም​ንም ቀስ ብላ ጠራ​ችና፥ “እነሆ፥ መም​ህ​ራ​ችን መጥቶ ይጠ​ራ​ሻል” አለ​ቻት። 29እር​ስ​ዋም ይህን በሰ​ማች ጊዜ ፈጥና ተነ​ሣች፤ ወደ እር​ሱም ሄደች። 30ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ማርታ በተ​ቀ​በ​ለ​ች​በት ስፍራ ነበረ እንጂ ገና ወደ መን​ደር አል​ገ​ባም ነበር። 31ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አት መጥ​ተው በቤት ከእ​ር​ስዋ ጋር የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም ፈጥና ተነ​ሥታ እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ በዚያ ለወ​ን​ድ​ምዋ ልታ​ለ​ቅስ ወደ መቃ​ብሩ የም​ት​ሄድ መስ​ሎ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አት። 32ማር​ያ​ምም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ አለ​በት ስፍራ ደረ​ሰ​ችና በአ​የ​ችው ጊዜ ከእ​ግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር” አለ​ችው። 33ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እር​ስዋ ስታ​ለ​ቅስ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር የመጡ አይ​ሁ​ድም ሲያ​ለ​ቅሱ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፤ በራ​ሱም ታወከ። 34እር​ሱም፥ “የት ቀበ​ራ​ች​ሁት?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ መጥ​ተህ እይ” አሉት። 35ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ባ​ውን አፈ​ሰሰ። 36አይ​ሁ​ድም፥ “ምን ያህል ይወ​ደው እንደ ነበር እዩ” አሉ። 37ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል፥ “ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ዐይን ያበ​ራው ይህ ሰው ይህስ እን​ዳ​ይ​ሞት ሊያ​ደ​ርግ ባል​ቻ​ለም ነበ​ርን?” ያሉ ነበሩ።
38ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃ​ብ​ሩም ሄደ፤ መቃ​ብ​ሩም ዋሻ ነበር፤ በላ​ዩም ታላቅ ድን​ጋይ ተገ​ጥ​ሞ​በት ነበር። 39ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ድን​ጋ​ዩን አንሡ” አላ​ቸው፤ የሟቹ እኅት ማር​ታም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አራት ቀን ሆኖ​ታ​ልና ፈጽሞ ሸትቶ ይሆ​ናል” አለ​ችው። 40ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ብታ​ም​ናስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ታያ​ለሽ አላ​ል​ሁ​ሽም ነበ​ርን?” አላት። 41ድን​ጋ​ዩ​ንም አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ እን​ዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ። 42እኔም ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ማኝ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክ​ኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ቆመው ስላ​ሉት ሰዎች ይህን እና​ገ​ራ​ለሁ።” 43ይህ​ንም ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸና፥ “አል​ዓ​ዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ። 44ሞቶ የነ​በ​ረ​ውም እንደ ተገ​ነዘ፥ እጁ​ንና እግ​ሩ​ንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰ​በን እንደ ተጠ​ቀ​ለለ ወጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ፍቱ​ትና ተዉት ይሂድ” አላ​ቸው።
45ስለ​ዚህ ከአ​ይ​ሁ​ድም ወደ ማር​ታና ወደ ማር​ያም መጥ​ተው የነ​በሩ ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን አይ​ተው በእ​ርሱ አመኑ። 46ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ሄደው የከ​ሰ​ሱት#“የከ​ሰ​ሱት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።
ስለ አይ​ሁድ ምክር
47የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ጉባ​ኤ​ውን ሰብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአ​ም​ራት ያደ​ር​ጋል፤ ምን እና​ድ​ርግ? 48እን​ዲሁ ብን​ተ​ወ​ውም ሁሉ ያም​ኑ​በ​ታል፤ የሮም ሰዎ​ችም መጥ​ተው ሀገ​ራ​ች​ን​ንና ወገ​ና​ች​ንን ይወ​ስ​ዱ​ብ​ናል።” 49በዚ​ያ​ችም ዓመት የካ​ህ​ናት አለቃ የነ​በ​ረው ስሙ ቀያፋ የተ​ባ​ለው ከእ​ነ​ርሱ አንዱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ን​ተስ ምንም አታ​ው​ቁም። 50ምንም አት​መ​ክ​ሩም፤ ሕዝቡ ሁሉ ከሚ​ጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት ይሻ​ለ​ናል።” 51ይህ​ንም ከልቡ የተ​ና​ገ​ረው አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዚ​ያች ዓመት የካ​ህ​ናት አለቃ ነበ​ርና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ስለ ሕዝብ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ይሞት ዘንድ ስላ​ለው ይህን ትን​ቢት ተና​ገረ። 52ስለ ሕዝብ ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ዘንድ ነው እንጂ። 53ከዚ​ያ​ችም ቀን ጀምሮ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች ሊገ​ድ​ሉት ተማ​ከሩ።
ጌታ​ችን ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትቶ ስለ መሄዱ
54ከዚ​ያም ወዲያ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል በግ​ልጥ አል​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለም​ድረ በዳ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍ​ሬም ወደ​ም​ት​ባል ከተማ ሄደ፤ በዚ​ያም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ተቀ​መጠ።
55የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከበ​ዓሉ አስ​ቀ​ድሞ ራሳ​ቸ​ውን ያነጹ ዘንድ ከየ​ሀ​ገሩ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተው ነበር። 56አይ​ሁ​ድም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይፈ​ል​ጉት ጀመር፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም ቆመው እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ምን ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል? ለበ​ዓል አይ​መጣ ይሆን?” ተባ​ባሉ። 57የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ያለ​በ​ትን የሚ​ያ​ውቅ ቢኖር ይይ​ዙት ዘንድ እን​ዲ​ያ​መ​ለ​ክ​ታ​ቸው አዘዙ።

ప్రస్తుతం ఎంపిక చేయబడింది:

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 11: አማ2000

హైలైట్

షేర్ చేయి

కాపీ

None

మీ పరికరాలన్నింటి వ్యాప్తంగా మీ హైలైట్స్ సేవ్ చేయబడాలనుకుంటున్నారా? సైన్ అప్ చేయండి లేదా సైన్ ఇన్ చేయండి